April 26, 2014
በተመሳሳይ በክርስቲያኖች በተለይም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ያለውን ጣልቃ ገብነትም በተመሳሳይ ሲቃወም ቆይቷል፡፡ ለአብነት ያህል በዋልድባ ገዳም ላይ የተወሰደውን ህገ ወጥ ተግባር በግልጽ ተቃውሟል፡፡ በአሁኑ ወቅትም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በተለይም በማህበረ ቅዱሳን ላይ ጫና እየተደረገ እንደሚገኝ መረጃዎች እየጠቆሙ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በማህበሩ ላይ ሊደረግ የታሰበው ሴራ እየተከታተለ ይገኛል፡፡ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንም ሆነ በማህበሩ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫናም በጽኑ ይቃወማል፡፡
ውድ የሁለቱም እምነት ተከታዮች፡- ሰማያዊ ፓርቲ ህወሓት/ኢህአዴግ የሚያደርገውን ጫና እና ጣልቃ ገብነት በጽኑ እየተቃወመ፣ ማንኛውም በሐይማኖታችሁ ላይ የሚደረግን ጫና በግልጽ እንድትቃወሙ ጥሪ ያቀርባል፡፡ የሁለቱም የእምነት መጽሃፍቶች በአንዳችን ላይ የሚደርሰው ግፍ በሌላኛው ላይም እንዳይሆን መፈለግ እንዳለብን እንደሚገልጹት የእናንተ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነትና ጫናም በመቃወም ለመርህ እንድትቆሙ ማሳሰብ ይፈልጋል፡፡

ሃይማኖት ለአንድ ማህበረሰብ ማንነት መሰረት እንደመሆኑ በአገር ግንባታ ቀላል የማይባል ሚና እንዳለው እናምናለን፡፡ ኢትዮጵያውያን ሐይማኖታች ሳይገድበን ተረዳድተን፣ ተባብረንና ተፈቃቅረን ኖረናል፡፡ ለዚህ አብሮ መኖርና መቻቻልም ሃይማኖታችን የራሱ የሆነ ሚና እንዳለው እናምናለን፡፡ ገዥው ፓርቲ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ብቻ ሳይሆን አንድ ሐይማኖት ውስጥ የሚገኙትን የአገራችን ዜጎች በጠላትና በወዳጅነት በመከፋፈል ኢትዮጵያውያን እርስ በእርሳቸው እንዲጠራጠሩ፣ ግጭት ውስጥ እንዲገቡና ሃይማኖታቸውን በነጻነት እንዳይከተሉ እያደረገ ነው፡፡ ይህም ለቀጣይ የአገራችን ሁኔታ አሉታዊ አስተዋጽኦው የጎላ በመሆኑ ፓርቲያችን በጽናት ይቃወማል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በዚህ ጽኑ አቋሙ አግባብ ያልሆኑ የተለያዩ ስሞች ተሰትቶታል፡፡ አመራሮቹና አባላቱም ታስረዋል፡፡ ተደብድበዋል፡፡ ከተነጠቁት መብቶች መካከል ይህን የእምነት ነጻነት መብት እንዲከበር የሚጠይቁ ጥያቄ ባነሳበት በአሁኑ ወቅት እንኳ ከ50 በላይ የፓርቲው አመራሮችና አባላት ማጎሪያ ቤት ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያውያን መብት ይከበር ዘንድ የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈልም ቁርጠኛ መሆናችንን መግለጽ እንወዳለን፡፡
ገዥው ፓርቲ በሃይማኖታችን ላይ ጣልቃ በመግባት የዜጎቻችን አንዱንና ዋነኛውን መብት ቀምቷል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ይህን የኢትዮጵያውያን መብት ለማስመለስ ሚያዝያ 19 ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡ በመሆኑም ይህን የተቀማችሁትን መብት ለማስመለስ በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ እንድትሳተፉ ጥሪውን ያቀርብላችኋል፡፡
ኑ ራሳችን ነጻ በማውጣት የአገራችን እጣ ፋንታ እንወስን!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ይኑር!
No comments:
Post a Comment