Monday, April 7, 2014

የአንባ ገነኖች የስልጣን ጥም አባዜ (ገዛኸኝ አበበ ከኖርዌይ ሌና)

በገዛኸኝ አበበ (ኖርዌይ ሌና)


 ዛሬ በአለማችን ላይ አንባ ገነን መንግስታቶች ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት በላው ሕዝብ ላይ  የሰብሃዊ መብት ረገጣ እስራት እና ግድያ በሕዝባቸው ላይ እንደሚያደርሱ ይታወቃል በተለይም የአፍሪካ መሪዎች እና መንግስታቶች በአንባ ገነንት እና የሕዝባቸውን ሰብሃዊ መብት በመርገጥ ግንባር ቀደም ተጠቃሾች ሲሆኑ ከእነዚህም ውስጥ አገራችን ኢትዮጵያ አንዶ ናት :: በአሁኑ ሰአት በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ አይን ያወጣ የሰበሃዊ መብት ጥሰት በዜጎች ላይ እየፈጸመ እንዳለ ይታወቃል ይህም የወያኔ የዜጎችን የሰብሃዊ መብት መርገጥ እና ሕዝብና እያስፈራሩ ረግጦ መግዛት ከምንም ነገረ የመነጨ ሳይሆን ሕዝቡ ስለ ዜግነት መብቱ እንዳያስብ በታጠቀ ኃይል እያስፈራሩ የሥልጣን እድሜን ለማራዘም ወያኔዎች ያዋጣናል ብለው የመረጡት መንገድ ሲሆን  ዜጎችን መረበሽ፣ መዝረፍ፣ ማሰር እና መግደልን ተያይዘውት ይገኛሉ::

ዜጎችን ማሰቃየት፣ ማሰር እና መግደል የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫና መታወቂያ ሲሆን        አንባ ገነን መንግስታቶች  በሰለም እና በመረጋጋት ሊመሩት እና ሊያስተዳድሩት የበላይ ሆነው የተሾሙለት ሕዝብ ሰበሃዊ መብት በመርገጥ  ግፍና በደል እንደሚፈጽሙባቸው በገሀድ የታወቀ ሲሆን እነዚህ አምባ ገነን መሪዎች ለምንድ ነው ግን ሕዝባቸውን የሚያሰቃዩት፣ የሚያስሩት እና  የሚገደሉት ብለን ማሰባችን እና መጠየቃችን አይቀርም በየትኛውም አለም እንደምናየው አንባ ገነኖች ያለምንም ተቀናቃኝ በስልጣን ዙፋናቸው ላይ ለመቀመጥ ከመሻት የተነሳ  ዜጎቻቸውን  ያሰቃያሉ፣ ያስራሉ፣ይገድላሉ

 በተለይም እኛ ኢትዮጵያኖች በሀገራችን መንግስት በየጊዜው በግፍ ስለሚያሰቃዩት፣ ስለሚታሰሩት እና  ስለሚገደሉት ወገኖቻችን ሁል ጊዜ እንዳለቀስን እና እንደጮህን እንገኛለን::

ምክንያቱም ወያኔ /ኢህአዲግ  ወደ ስልጣን  ከመጣበትና የኢትዮጵያንም ሕዝብ  በሀይል መምራት  ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከሁለት አስርት ከአመታት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል ማጋነን አይሁንብኝም::ይኼው የወያኔ ኢህአዴግ አገዛዝ ሁልጊዜ እንደፈራ ሕዝቡንም እንዳስፈራራ ሁል ጊዜ እንደተረበሸ ሕዝቡንም እንደረበሸ የሚኖር ሲሆን ይህም የወያኔ  ባህሪና መገለጫዎች ናቸው:: ከዚህም የተነሳ ሀገራችን ኢትዮጵያ በወያኔ ኢህአዲግ መንግስት መገዛት ከጀመረችበት ጊዜ  አንስቶ ወያኔ ያሰረው እና የገደለው ሀገሩንም ጥሎ እንዲሰደድ ያደረገው ሕዝብ ቁጥሩ እጅግ ብዙ ሲሆን የዜጎችንም ሰላም በመረበሽ እና በሀገራቸው ተረጋግተው እንዳይቀመጡ በማድረግ ላይ ይገኛል::

 ከዚህ በታች  የአንባ ገነኖችን ማንነት መገለጫ የሆኑትን ነገሩች  በአጭሩ የተወሰኑ ነጥቦችን በማንሳት ለመዳሰስ እሞክራለው

    1,አምባገነኖች ያለ ሕዝብ ፍላጎት ለብዙ አመታት በስልጣን ላይ የመቆየት ማንነት ይታይባቸዋል         (የስልጣን ሱሠኞች) ናቸው ::

  ብዙዎን ጊዜ እንደ  አፍሪካ እና አረብ ሀገራት ያሉ አምባ ገነን  የሀገር መሪዎች ወደ ስልጣን ሲመጡ የሕዝብን ህውቅና አግኝተው ወይም በሕዝብ ድምጽ በምርጫ ተመርጠው ሳይሆን አንድም በመፈንቅለ መንግስት አንድም በጦርነት በሀይል ስልጣንን መቆጣጠር ወይም በዘር ውርስ የስልጣን እርክብክቦሽ አማካይነት መሆኑ ይታወቃል:: ስለሆነም  ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ  ስልጣናቸው ወይም መንግስታቸው በሀገራቸው ዜጎች እውቅና ሲሰጠው አይታይም :: ከዚህም የተነሳ ከሕዝባቸው ጋር አይጥ እና ድመት በመሆን ተፈራርተው ሕዝባቸውን  ሲያስፈራሩና ሲረብሹ ይኖራሉ ::  እንደነዚህ ያሉ ሀገራቶች  በማን አለብኝነት ያለምም ተቀናቃኝ ለብዙ አመታት የስልጣንን ወንበር ተቆጣጥረው ስልጣንንም መከታ በማድረግ የሕዝብን መብት በመርገጥም  ሲኖሩ ይታያሉ:: እነዚህ አንባ ገነን መንግስታቶች በሕዝባቸው ላይ አመኔታ የላቸውም ሕዝቡም በእነሱ ላይ አመኔታ የለውም ስለዚህ ሁል ጊዜ በዜጎቻቸው እንደተረገሙ እነሱም ሁል ጊዜ ዜጎቻቸውን እንደረገሙ ይኖራሉ::እየወለ እየደር ግን የአንባ ገነኖች መጨረሻቸው በሕዝብ ቁጣ ተርፍረክርኮ መውደቅ ነው::

 በግብጽ በቱኒዚያ በየመን እና በሌሎችም ሀገሮች እንዳየነው አንባገነኖች ለብዙ አመታት ስልጣንን በማውረስ እና በመረካከብ ሕዝብን በመጨፍለቅ ሲገዙ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው ለምሳሌ በግብጽ ጀማል ሙባረክ የሚቀጥለው የግብጽ መሪነትን ከአባቱ ለመውረስ እና ለመረከብ በመዘጋጀት እያለ ነበር ድነገት ባልጠበቁት ሰአት የቱኒዚያው ሱናሜ የተነሳው እና ያለሙትን አላማ ሳይተገብሩ በአንባ ገነኖች መገዛት በሰለቸው ሕዝብ ቁጣ እንደ ሰም ቀልጠው የቀሩት:: እነዚህን ሀገሮች እንደ ምሳሌ አነሳው እንጂ እንደነ ምሮኮ እና ኮንጎ የመሳሰሉ አብዛኞች ሀገሮች ስልጣንን በሀይል ወይም በውርስ በማውረስ እና በመረካከብ  ያለ ሕዝብ ፍላጎትና ህውቅና  ለዘመናት በማን አለብኝነት ስልጣንን በግላቻው በመቆጣጠር የሕዝቦችን ሰብሃዊ መብት ሲጨፈልቁ የሚኖሩ ሀገሮችን መጥቀስ ይቻላል::አንባ ገነኖች  እነሱን ከሚመስላቸው ውጭ  ለሌላ የፖለቲካ ፓርቲ ድርጅትም ሆነ ሀገርን ለመምራት አቅምም ሆነ ብቃቱ ላላቸው ሰዎች በማንኛውም መንገድ ቢሆን ስልጣንን ለመልቀቅ ፍቃደኞች ሲሆኑ አይታዩም::

ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ስንመጣ ይህንኑ ነው የምናየው በአሁኑ ሰአት ሀገራችንን ኢትዮጵያን እየመራው ነው የሚለው የወያኔ  መንግስት ስልጣንን በዘር ሲወራረሱ እንደነበሩ  እንደ አንዳንድ አረብ  እና አፍሪካ ሀገራት አንባ ገነን መሪዎች በዘር አይወራረሱ እንጂ   ያለ  ሕዝብ ፍቃድ እና ፍላጎት ውጭ ለዘመናት የስልጣን ወንበሩን በማን አለብኝነት በሀይል ተቆጣጥሮ የዜጎችን ሰብሃዊ መብት እየረገጠ ያለ መንግስት መሆኑ ይታወቃል::አሁን ባለው አካሄድ እና አንዳንድ የወያኔ ባለስልጣኖች  ጊዜ አፋቸው እያመለጣቸው እንደሚናገሩት እነዚህ የስልጣን ጡመኞች የሆኑት የወያኔ ባለስልጣኖች በፈቃዳቸው ስልጣንን ይለቃሉ ተብሎ የማይታሰብ ቢሆንም ድንገት ግን የሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ወያኔ የሚባል የአንባ ገነን የማፊያ ቡድን ዳግመኛ እንዳያንሰራራ በግብጽ ፣ በቱኒዚያ እና በሌሎችም ሀገሮች እንደ ሆነው ሁሉ የአንባ ገነኑን የወያኔን መንግስት  ስርአት ወደ መቃብር ያስገበዋል የሚል ከፍተኛ የሆነ እምነት አለኝ::

የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች ለአስርት ዓመታት በአምባገነን አገዛዝ ተገዝተዋል። እኛ ደግሞ ለአስርት ዓመታት አምባገነን ብቻ ሳይሆን ዘረኛም ጭምር በሆነ የስልጣን ጥም አባዜ በተጠናወጠወ አገዛዝ እየተገዛን ነው። እኛ እየደረሰብን ያለውን ዓይነት አዋራጅ ዘረኝነት እነሱ ላይ አልደረሰባቸውም። አምባነንነት እነሱን አስመርሮ በገዚዎቻቸው ላይ በአንድነት እንዲነሱ አድርጓቸዋል። እኛ ዘንድ ደግሞ አምባገነንነትና ዘረኝነት ተዳብለውብናልና ከእነሱ በላይ አምርረን በህብረት እንነሳለን።

   2,አምባገነኖች በራስ የመተማመን (self confidence)ስለሌላቸው ለሁሉም ሃይል መጠቀም ይወዳሉ።

 አንባ ገነን መንግስታቶች ሕዝብን በአግባቡ መምራት ሕዝብ የሚጠይቀውን ማንኛውንም አይነት ጥያቄ ለመመለስ ፍቃደኛ አይደሉም:: አንባ ገነን መንግስታቱች በነገሱበት ሀገር የመብት የነፃነት የፍትህ ጥያቄ መጠየቅ በፍጹም የማይታሰብ ሲሆን ዛሬ ስንቶች ናቸው መብታቸውን  ስለጠየቁ  ብቻ በአንባገነኖች ጥይት በየሀገሩ እንደ ቅጠል እየረገፉ ያሉት::

እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ነገር የኛዎቹ አንባ ገነኖች (የወያኔ መንግስት)  መጀመሪያውኑ   ወደ ስልጣን ሲመጡ እና  ለዘመናት ከሁለት አስርት አመታት በላይ በስልጣን ላይ  ሲቀመጡ በሕዝብ ፍላጎት እና ነጻ ምርጫ ሳይሆን ሌሎች አንባ ገነን መንግስታቶች እንደሚያደርጉት ሁሉ ሕዝብን እያስፈራሩ እና ሃይልን በመጠቀም የሕዝብን ናጻነትና መብትን በማፈን እንደሆነ ይታወቃል ::  በመሆምኑ የስልጣንን ወንበር ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ መንግስታቸው የሕዝብ ተቀባይነት የለውም:: ስለሆነም   ፈጽመው ተረጋግተው መኖር በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሲገኙ  ሁልጊዜ መንግስታቸው በስጋት ውስጥ ነው :: 

አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት በራሱ የማይተማመንና በስጋት ውስጥ የሚኖር መንግስት  እንደሆነ በቅርቡ  የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሒዩማን ራይትስ ዎች የወያኔን መንግስት አሳፋሪ ድርጊት በመኮነን ያወጣው ሪፖርት አመላካች ነው::እንደ  የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሪፖርት  ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎች ባለሙያዎችን በማነጋገር አዘጋጀሁት ባለውና በተጠናቀቀው  ሳምንት ይፋ ባደረገው  የኢትዮጵያ መንግሥትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈጸመ እንዳለ እና  ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ወይም አገር ውስጥ እንዳይንቀሳቀስ ከታገደ የፖለቲካ ድርጅት ጋር በማንኛውም መንገድ ቅርበት ያላቸው ኢትዮጵያውያኖች በወያኔ መንግስት እንደሚሰለሉ እና እነዚህ ሰዎች የሚያደርጉት የስልክ ንግግር በተለይ ደግሞ ከውጭ አገር የተደወለ ከሆነ ያለ ግለሰቦቹ ፈቃድ ወይም ዕውቅና ተጠልፎ እንደሚቀዳ ሒዩማን ራይትስ ዎች በሪፖርት ላይ ይፋ አድርጎል  ለዚህም የስለላ ተግባሩን ለመፈጸመ  የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ከተለያዩ አገሮች እንዳገኘ፣ሪፖርቱ ጨምሮ ይፋ አድርጓል::

  የወያኔ መንግስት በራስ መተማመን የጎደለው እና በፍርሃት የተሞላ መግስት መሆኑን በአደባባይ ያስመሰከረ አንባ ገነን መንግስት ነው ::መሪዎቹ በጭራሽ በራስ መተማመን ብሎ ነገር ስላልፈጠረባቸው መተማመኛቸው ጠብመንጃ፤በጦሩ ጉያ ተሸጉጠው ሃገርና ሕዝብን ለእልቂት ለረሃብ ለመከራ የሚያበቁበትን ቆመውም ተቀምጠው ተኝተውም ማውጠንጠን ነው፡፡ ይህንንም ስል እንዴው ዝም ብዬ ከመሬት ተነስቼ እንዳይደለ ይታወቅልኝ:: እኔ እስከማቀው ድረስ የወያኔ መንግስት ስልጣኑን ሀ ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንስቱ እስከ አሁን ድረስ ከ22 አመት በላይ መሆኑ ነው አንድም ቀን በሰላም እና በተረጋጋ ሁኔታ የኖረበት እና የኢትዮጵያ ሕዝብንም በሰላም የመራበት ጊዜ የለም ብል የተሳሳትኩኝ አይመስለኝም:: ከዚህ ስጋታቸውም የተነሳ የኢትዮጵያን ሕዝብ አፍነው ይዘውታል::

 ዜጓች ሕገ መንግስታዊ  መብታቸውን ተጠቅመው  የሚደርስባቸው ጭቆናና የሰበሃዊ መብት ጥሰት   በነጻነት መቃወም አልቻሉም :: አንባ ገነኑ ወያኔ ይኼን ያክል ዘመን በስልጣን ላይ ሲቆይ ስልጣኑን መከታ በማድረግ  ስንቶችን ሲገርፍ፣ ሲያስር ፣ ሲያሰቃይ እና ሲገድል እንደኖረ በአደባባይ የተገለጠ ሀቅ ነው::ሕዝብም ስለመብቱ እና ነጻነቱ የጠየቀ ከሆነ ይታሰራል ፣ይገረፋል ይገደላል::

ኢትዮጵያን በዘር ፣ በቋንቋ እና በሃይማኖት ከፋፍሎ የህዝቡን አንድነት ለማጥፋት የሚጥረውን አገዛዝ መቃወም ደግሞ “አሸባሪ’’ የሚል ታርጋ አስለጥፎ ዘብጥያ ያስወረውራል።  ዛሬ የኛዎቹ እነ እስክንድር ነጋ ፣ርዕዮት አለሙ እና ሌሎችም ወጣት ወገኖቻችን በሽበርተኝነት ስም ተወንጅለው በአንባ ገነኖች እስር ቤት ውስጥ ተጥለው እየተሰቃዩ ያሉት የወያኔ መንግስት እንደሚለው ሽብርተኛ  ሳይሆኑ  የነጻነት እና የፍትህ ታጋይ ጀግኖች እንደሆኑ በድፍረት መናገር እችላለው::

በወያኔ አንባ ገነናዊ እኩየ ስራዓት የህግ የበላይነት የለም፤ ዲሞክራሲ ተደፍጥጡዋል፤ የደህንነት ዋስትና የለም፤ ነፃ ፕሬስ ተረት ሆኗል፣ የብዙሃን ፓርቲ ያልምንም እፍረት ተገፍትሮል። የሲቪክና ሙያ ማህበራት የማሽመድመዱ ተግባር ተከናውኗል።ይለቁንም ዘረኞች ግፈኞች፣ ወንጀልኞች፣ አምባገነኖች፣ ሙሰኞች እንዳሻቸው ዛሬም እየፈነጩ፤  በተቃራኒው ደግሞ ለፍትህ ለእኩልነትና፣ለነጻነት ሲሉ ለህሊናቸው፣ የሚታገሉ የሚዋረዱበት፣ የሚሰደዱበትና የሚታስሩበት አገር መሆኑ በጣም ያንገበግባል፣ ያስቆጫል።

ነገርግን አንባ ገነኖች የስልጣን ሃይላቸውን በመጠቀም ማሰር፣ መግደል ሕዝብን ማሰቃየት ከያዛቸው የስልጣን ጥም አባዜ የተነሳ በስልጣን ላይ ረጅም ጌዜ ለመቆየት የሚጠቀሙበት መንገድ ሲሆን ይህም በራስ መተማመን እንደሌላቸው ያሳያል ::ነገር ግን እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን ነገር ይህ አይነት አካሄድ አንባ ገነን መንግስታቶችን የትም ሊያደርሳቸው እንደማይችል ሲሆን አንባ ገነኖችም ይህን ሊገነዘቡትና ሊያውቁት ይገባል ባይ ነኝ ::በርግጥ የታፈኑ ብሶት ገንፍሎ የነጻነት ደማቅ ፀሐይ የምናይበት ጊዜ እንደሚመጣ ቅንጣት ያክል አልጠራጠርም። 

የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት ዜጎች በያገራቸው ፍትህ በመጓደሉ ተማረዋል። እኛ አገር ደግሞ ፍትህ ራስዋ ተዋርዳለች። ፍርድ ቤቶች ማጥቂያዎች ሆነዋል። አገራችን እስር ቤት ሆናለች። አብዮት ከቀሰቀሱት ጎረቤቶቻችን በባሰ እኛ ተበድለናልና  ከእነሱ በባሰ አምርረን ልንነሳና አንባ ገነኖችን ዳግም እንዳይነሱ ልንቀብራቸው ያስፈልጋል።

     3,አምባገነኖች ከሀገር እና ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ያስቀድማሉ (ሙሰኞች ናቸው)

የአንባ ገነኖች ሌላው የባህሪያቸው ዋንኛ መታወቂያቸው ሙሰኝነት ሲሆን ይህንንም ተከትሎ  አገራችንን ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካ  አንባ ገነኖች በስፋት የነገሱባት  ሙሰኝነት እና ሙሰኞች የተንሰራፉበት አህጉር በመሆን ትታወቃለች :: በአፍሪካ ሀገራት የሚነሱ መሪዎች ወደ ስልጣን ከመጡ እና ስልጣን ከያዙ በኋላ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝባቸው ግድ የለሾች ሲሆኑ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝባቸው ግድ የማይላቸው ሆዳሞችና የራሳቸውን ጥቅም ብቻ የሚያሳድዱ ገንዘብ ወዳዱች ናቸው::

 በሀገራችን ኢትዮጵያ በስልጣና ላይ ያለው አምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖች  ከላይ እስከታች በተዘረጋው የወያኔ ስርአት ውስጥ ከቁንጮ ባለስልጣናት እስከታችኛው አገልጋይ ድረስ በሙስናና በሌብነት ያልተዘፈቀ የስርአቱ አገልጋይ ቢፈለግ አይገኝም :: በአሁኑ ሰአት መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አዲስ አበባን ነዋሪ ጨምሮ ሕዝቡ በከፍተኛ የኖሮ ችግር እንዳለ ይታወቃል:: ካለውም ታላቅ የኑሮ ውድነትና የስራ ማጣት ፣ ያለው ብልሹ የመንግስት ፖለቲካዊ አስተዳደር ተደምሮበት ሕዝቡ ሀገሮን ጥሎ ወደ ተለያየ ሀገር እየተሰደደ በተለይም ወጣቶች ወንዶችና ሴቶች እህቶቻችን ሀገራቸውን ጥለው ሲወጡ በየድንበሩ እየሙቱና ወደ ተለያየ ሀረብ ሀገራትም ሄደው ለተለያየ መከራ ስቃይ እና ችግር ሲደርስባቸው እና ዜጓቻችን ሲገደሉ ምንም ግድ የማይሰጣቸው ነገር ግን   እኔ ከሞትኩኝ ሰርዶ አይብቀል እንደሚባለው የወያኔ  አንባ ገነን መሪዎች ሙሰኞች ከኢትዮጵያ ሕዝብ የዘረፉትን  በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ከኢትዮጵያ ህዝብ በማሸሽ በውጪ አገር ባንኮች በማካበት ላይ እንደሚገኙ ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የአገሪቱ ገንዘብ በውጭ ባንኮች መቀመጡን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል ።

በወር ስድስት ሺህ ብር ደሞዝተኛ እንደነበሩ በባለቤታቸው የተነገረላቸው አንባ ገነን የነበሩት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር ሞቹ አቶ መለስ ዜናዊ ሁላችንም እንደምናስታውሰው ከጥቂት ዓመታት በፊት የትንሳኤ ሬድዮ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት የዘረፉ የወያኔ መንግስት ባለስልጣኖችን፥ የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ የዘረፉትን ሀብት መጠንና ገንዘቡን ያስቀመ ጡበትን አገር ጭምር ይፋ አድርጎ እንደነበር አስታውሳለው።  ።  አቶ መለስ ዜናዊ በማሌዥያ በባንክ ፬፪ (አርባ ሁለት) ሚሊዮን ዶላር እንዳስቀመጡ ገልጾ ነበር።ይታያችው እንግዲህ  በተከታዩቻቸውና የአቶ መለስ አፍቃሪ በሆኑ ሰዎች እስከ አሁን ድረስ ሰውየው ስለ ሀገራቸውና ስሉሕዝባቸው ፍቅር የነበራቸው ባለራእይ መሪ እንደነበሩ ሲወደሱ እና ሲዘመርላቸው እንሰማለን እውነታው ግን የሚያሳየው ሌላ ነው አንባ ገነኖች አንድም ቀን የሀገር እና የሕዝባቸው ፍቅር ኖሮቸው አያውቅም እኝው አንባ ገነን የቀድሞ መሪ ሕዝባቸውን ሲያዋርዱና ሲያንቋሽሹ ለሀገራቸውም ቅንጣት ያከል ፍቅር እንደሌላቸው የሚያሳይ ስራ ይሰሩ የነበሩና ጀግኖች አባቶቻችን የታወደቁለትን ባንዲራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንዴ ሲዘቀዝቁት አንዴ ጨርቅ ነው ሲሉት እንደነበር እናስታውሳለን::


 በአሁኑ ሰአት የወያኔ መንግስት ሙስናን ለማጥፋት እየታገለ እንዳለ በተለያዩ መድረኮችና ሚድያዎች ከመግለፅ ኣልፎ። ራሱ የፀረ ሙስና ኮምሽን ብሎ ባደራጀውና  በሚጠራው ተቋም ሙሰኞች ባላቸው ግለ ሰቦች  ላይ ክስ በበመመስረት ወደ ፍርድ ሲያቀርባቸውና እስርቤት ውስጥ ሲያጉራቸው ይስተዋላል፣ ነገር ግን ይህ የወያኔ መሰሪ ተንኮል ሆነ ብሎ ለህዝብና ለኣለም ማህበረሰብ ወያኔ እራሱን የብርሃን መላእክት አድርጎ በማቅረብ ለማታለል ተብሎ እየተሰራበት ያለ ተንኮል ነው:: 

ወያኔ እራሱን ፀረ-ሙስና ድርጅት ለመምሰል ለህዝብና ለኣለም ማህበረሰብ ለማታለል እየተሰራበት ያለ ድብቅ ተንኮል     ነገር ግን ለስርኣቱ ተገዢ ሆነህ እስካገለገልክ ድረስ በአስተሳሰብ የተለየ እስካልሆንክ ሰው ብትገድል እንኳ በእርቅ ነፃ መውጣት ትችላለህ፡፡ስልጣንህን ተገን በማድረግ የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ለመስርቅ ሙሉ ዋስትና እንደሚሰጥህ፣ የፈለከውን ያክል ገንዘብ ብትዘርፍ ዘመነኛ ተብለህ ልትሸለማለህ ትችል እንደሆነ እንጂ ሙሰኛ አያሰኝህም፡፡ ነገር ግን ከእነሱ ትንሽ ለየት ያለ የፖለቲካ ልዩነት ያላቸው እና ለበላይ ኣለቆቻቸው  ያላጎበደዱና ያልተስማሙ ግን ሙስናን ተገን በማድረግ በቁጥጥር ውስጥ እንደሚውሉ ይታወቃል:: ይህም  የወያኔ  ስርአት ምን ያህል አንባ ገነን መሆኑንና ስርኣቱ የስልጣን ጥም አባዜ በተጠናወጣቸው የስልጣን ሙሰኞች  የተሞላ ኣስመሳይ ፀረ ህዝብ ኣሰራር መሆኑንን ያመለክታል::

ሙስና የአንባ ገነን መንግስታቶች መገለጫ ሲሆን የሰሜን አፍሪቃ እና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት የነበሩት አንባ ገነን ሹሞች በሙስና ያካበቱት ሃብት በቢሊዮን ዶላሮች እንደሚገመትና ሕዝቡንም ለአመጽ ያነሳሳው ይኸው የአምባ ገነኖች ከልክ ያለፈ ሙሰኝነትና ሌብነት እንደሆነ ይታወቃል። የእኛ የመጨረሻይቱ ድሃ አገር አንባ ገነን የወያኔ ሹሞችም በሙስና ያካበቱት ሃብት እንደዚያው ነው። እርግጥ ነው በከተሞቻችን ህንፃዎች በርክተዋል ሆኖም ግን የሙሰኞቹ እንጂ የለፍቶ አዳሪዎቹ አይደሉም። በሃብት መበላለጥ የተቆጩት እና በሙስና መብዛት በአንባ ገነንና በስልጣን ሱሰኞች መሪዎቻቸው የተናደዱ የአህጉራችን  የሰሜን አፍሪቃ ዜጎች በገዢዎቻቸው ላይ ተነስተዋል እኛ ደግሞ  ከእነሱ በላይ ተጎድተናልና ከእነሱ በላይ አምርረን ልንነሳ ሙሰኛውን፣ የሀገርና የሕዝብ ፍቅር የሌለው አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ላይ መነሳት ይጠበቅብናል።
   
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
ውድቀት ለአምባገነኖች!!!
gezapower@gmail.com



No comments: