Tuesday, April 1, 2014

ዶክተር ዳኛቸው አሰፋን ከዩኒቨርስቲ ለማባረር የተሰራው ሴራ ከሸፈ::


ኑሯቸውን ከመሰረቱባት አሜሪካ ጓዛቸውን ጠቅልለው አገራቸው በ1997 ግድም የገቡት ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ላለፉት ሰባት አመታት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ዶክተሩ በአደባባይ ሀሳባቸውን መግለጽ በመጀመራቸውና ተማሪዎቻቸውም በሀሳብ ላይ ተመስርተው ሀሳባቸውን እንዲገልጹ ማደፋፈር መጀመራቸው በገዢው ፓርቲ ሰዎች በስጋት እንዲታዩ አድርጓቸዋል፡፡
ዳኛቸው የቀድሞዋ የትምህርት ሚኒስትር ገነት ዘውዴ የቅርብ ዘመድ በመሆናቸውም‹‹የራሳችን ሰው እንዴት በአደባባይ ይተቸናል››የሚል ክፉ መንፈስ የተጠናወታቸው ለኢህአዴግ ቅርበት አለን የሚሉ ካድሬዎች ዶክተሩን ከዩኒቨርስቲው ለማስወጣት የተለያዩ ሴራዎችን በመጎንጎን ላይ ታች ሲሉ ቆይተዋል፡፡
የፍልስፍና ምሁሩ የአመት እረፍታቸውን አጠናቅቀው በቅርቡ ወደ ስራ ገበታቸው እንደተመለሱ ዩኒቨርስቲው የቅጥር ኮንትራታቸውን ለማደስ መዝገብ ቤት የሚገኘውን መረጃቸውን ፈልጎ በማጣቱ ኮንትራታቸውን ለማደስ መቸገሩን ያረዳቸዋል፡፡
አስተማሪነትን ለእንጀራ የማይፈልጉት ዳኛቸው በሰሙት ነገር ሳይደናገጡ በየመዝገብ ቤቱ መረጃቸውን ማፈላለጉን ይያያዙታል፡፡አራት መዝገብ ቤት የጠፋው ፋይል ዛሬ ከመዝገብ ቤት ውጪ በአንድ ሰው አማካኝነት በመገኘቱም የመምህሩ የቅጥር ኮንትራት እንዲታደስ ትዕዛዝ ተላልፏል፡፡
ለዳኛቸው ቅርበት ያላቸው ምንጮቼ እንደነገሩኝ ከሆነ‹‹ዛሬ የድል ቀኔ ነው››በማለት ዶክተሩ ለወዳጆቻቸው ተናግረዋል፡፡

No comments: