Wednesday, April 9, 2014

ከምዕራብ ሸዋ ተፈናቅለው በፌዴሬሽኑ አፈ ጉባዔ አግባቢነት የተመለሱት ዜጎች መሬታቸውን በሃይል ተነጠቁ ወልድያ ከተማ ከ50 በላይ የሚሆን አባዎራዎች እስከ ቤተሰባቸው ጎዳና ላይ ወድቀዋል፡፡

April 9/2014

ከሰላሳ የማያንሱ የምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ ባጅላ ዳሌ ቀበሌ ገ/ማህበር ነዋሪዎች ‹‹ ወደ ክልላችሁ ተመለሱ ›› ተብለው መሬታቸውን ለመነጠቅ መቃረባቸውን ለማመልከት አዲስ አበባ በመምጣት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተ/ብርሃንን ካናገሩ በኋላ አፈ ጉባኤው ‹‹ወደ ቀዬአችሁ ተመለሱ እኔ ችግሩ እንዲፈታላችሁ አደርጋለሁ››በማለታቸው ገበሬዎቹ ወደ አምቦ መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡
ወደ አምቦ የተመለሱትን ገበሬዎች የዞኑ ሃላፊዎችና የኦህዴድ ካድሬዎች ‹‹አዲስ አበባ በመሄድ ገመናችንን አጋለጣችሁ››በማለት ሲዝቱባቸው መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ከትናንት ጀምሮም የታጠቁ ሚሊሻዎችን በማስከተል የቀበሌ ገ/ማህበሩ አመራሮች‹‹መሬታችንን ለቃችሁ ወደ መጣችሁበት ክልል ተመለሱ ››በማለታቸውና ገበሬዎቹ ‹‹ አንለቅም ከዚህ ውጪ አገር የለንም›› ቢሉም በመሳሪያ በማስፈራራት ከአካባቢው እንዲርቁ በማድረግ መሬቱን ለሚፈልጓቸው ሰዎች ማከፋፈላቸውንና ሊደበድቡንና ሊገድሉን ይችላሉ ብለው የሰጉ ገበሬዎችም ልጆቻቸውንና ባለቤቶቻቸውን በመያዝ ጫካ መደበቃቸውን በስልክ ከስፍራው ያናገርኳቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡ገበሬዎቹ ከዛሬ ሀያ ዓመት በፊት ከጎንደር አካባቢ ተፈናቅለው አሁን ለስደት በተዳረጉበት አካባቢ የሰፈሩ ነበሩ፡፡
ገበሬዎቹ ለአቤቱታ አዲስ አበባ መጥተው በነበረበት ወቅት ለምን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር ሄዳችሁ ተብለው መታሰራቸው አይዘነጋም፡፡
ወልድያ ከተማ ከ50 በላይ የሚሆን አባዎራዎች እስከ ቤተሰባቸው ጎዳና ላይ ወድቀዋል፡፡
የሚኖሩበት ቤት ለባለሀብት በኢንቨስትመንት ስም ለወያኔ ባለሀብት በመሰጠቱ በ 24 ሰዓት ውስጥ ካልወጣችሁ ትታሰራላችሁ ሲባሉ የት እንውደቅ ሌላ አማራጭ የቀበሌ ቤት ወይም ቦታ ይሰጠን ብለው ቢጠይቁም በወያኔ የፌደራል ፖሊስ ተይዘው ፖሊስ ጣቢያ ታስረዋል፡፡ ቤተሰቦቻቸውም ጎዳና ላይ ወድቀዋል፡፡
የከተማው ከንቲባ አቶ ፀሐዩ መንገሻ፣ የዞን ብአደን ሀላፊ አቶ አበባው ሲሳይ እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሀላፊዎች ሲጠየቁ ይህ ጉዳይ ከአቅማችን በላይ ሲለሆን አይመለከተንም ማለታቸው ህብረተሰቡን አስቀይሞታል፡፡ ስለጉዳዩ ማጣራት የፈለገ ሰው ወልድያ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እየደወለ መጠየቅ የሚችል መሆኑን ከስፍራው መረጃ ደርሶናል፡፡ ስለዚህ ይህን ስብዓዊ መብት ረገጣ አስመልክቶ ግለሰቦችን በማነጋገር መረጃውን ለ ኢሳትና ቪኦኤ እንድትልኩ እናሳስባለን፡፡

No comments: