Wednesday, April 9, 2014

አቡጊዳ – የመኢአዱ ሊቀመንበር ከአንድነት ጋር ዉህደቱ እንደሚፈጸም ያላቸውን ሙሉ ተስፋ ገለጹ

April8/2014

«በቅርቡ ከአንድነት ለደሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ጋር ለመዋሃድ ጥረት እያደረጋችሁ ነው ያላችሁት። ሂደቱ ምን ላይ ይገኛል ? » በሚል ከአዉስትራሊያ ከሚገኝ ኤስ፣ብ.ሲ ራዲዮ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት የመኢአድ ሊቀመነበር አቶ አበባዉ መሃሪ በአንድነት እና በመኢአድ መካከል ያሉ ልዩነቶች ከባድ እንዳልሆኑ በመግልጽ ፓርቲዎቹ ዉህደት እንደሚፈጽሙ ያላቸውን ሙሉ ተስፋ ገልጸዋል። «ተበታትነን ገዢዉን ፓርቲ ለማሽነፍ ከአብድ ነው» ያሉት አቶ አበባዉ ዉህደቱ የዜጎችን እና የሕዝቡን ሞራል የሚያሰንሳና የሚቀስቀስ፣ ለሕዥቡ አለኝታ የሚሆን ወሳኝ ነገር እንደሆነ የገለጹት አቶ አበባዉ እንደ መኢአድ ሊቀመነበር «ተንበርክኬም ቢሆን እነርሱን (አንድነቶችን) ለመቀበል ዝግጁ ነኝ» ብለዋል።
በቅርቡ የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ « The negotiation for merger of UDJ and AEUP has so far failed because of differences on the question of chairmanship and because of the number of representation on the merger general assembly» በማልት የሰጡት አስተያየት በተመለከተ ለተጠየቁት ምላሽ የሰጡት የመኢአዱ ሊቀመነበር ፣ የዶር ነጋሶን አስተያየት «ትክክል ያልሆነ» ብለዉታል። የዉህዱ ፓርቲ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ ከሁለቱም ድርጅቶች እኩል ፣ እኩል እንዲሆን እና የዉህዱ ፓርቲ ሊቀመንበር፣ 2፣ ሶስት እጮዎች ቀርበው፣ በጠቅላላ ጉባኤዉ ዴሞክራቲካሊ እንዲመረጥ ስምምነት እንደተደረሰም አስረድተዋል።
አቶ አበባዉ መኢአድ ከአንድነት ጋር የቅድመ ዉህደት ፊርማ ከመፈረሙ በፊት ከመድረክ መዉጣት እንዳለበት ይናገራሉ። በዋናነትም ወደፊት መግፋት ያልተቻለዉ በዚህ የመድረክ ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ።
የዉህዱ ፓርቲ ሲመሰረት መኢአድ እና አንድነት እንደ ድርጅት የሚከስሙ እንደሆነ የሚናገሩት የአንድነት አመራሮች፣ በሕግን በአሰራርም ዉህዱ ፓርቲ የመድረክ አባል ሊሆን አይችልም ሲሉ ፣ በአቶ አበባዉ የቀረበዉን መከራከሪያ አይቀበሉትም። የአንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ባዘዘው መሰረት ከመኢአድ ሆነ ሌሎች ድርጅቶች አግር ዉህደት ተፈጠረ አልተፈጠረ፣ የመድረክ ነገር እልባት እንደምያገኝ የሚገልጹት የአንድነት አመራሮች፣ ምክር ቤቱ በሌሎች አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ጊዜ እየወሰደ በመሆኑ እንጂ በመድረክ ላይ ዉሳኔ በቅርቡ እንደሚሰጥ ይናገራሉ።
ከአንድነት አካባቢ ቅርበት ያላቸው ወገኖች እንደሚናገሩት፣ ምክር ቤቱ በኦፈሴል አንድነት ከመድረክ እንዲወጣ ዉሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። የመድረክ አባል ድርጅቶች አንድነት ከመድረክ ዉጭ በመንቀሳቀሱ ፣ ይቅርታ እስኪጠይቅ ድረስ፣ እንዲታገድ መወሰናቸው ይታወቃል። የአንድነት አመራር አባላት የመድረክን የ’እገዳ ደብዳበ ዉድ ያደረጉት ሲሆን፣ እንደ አንድነት እንቅስቃሴያቸውን እየቀጠሉ እንደሆነ የሚያሳዩ ዘገባዎች እየተነበቡ ነው። መድረኩ እገዳ ካደረገ በኋላ በባህር ዳር፣ በደሴ ታላላ ቅሰላምዊ ስለፎች የተደረጉ ሲሆን፣ ከጥቂት ቀናት በኋላ በአዲስ አበባ የ «እሪታ ድምጽ» በሚል ሰልፍ ይደረጋል ተብሎ ይጠብቃል። በመቀጠልም በአዋሳ፣ በመቀሌ፣ ድሬደዋ፣ አዳማ በመሳሰሉት የሚሊዮኖች ድምጽ በሚል መርህ አገረ ሰፊ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ በስፋት እየተዘገበ ነው።
በመኢአድ ጉዳይ ያነጋገርናቸው አንድ ከፍተኛ የአንድነትይ አመራር አባል፣ «በመግለጫ ከሰጥጠነው ዉጭ የምንለው የለም» ይላሉ። «ከመኢአድ ጋር ዉህደቱ እንዲጠናቀቅ፣ ፋላጎቱ አለን። ለአመታት የደከምንበትና የተነጋገርንበት ጉዳይ ነዉ። ነገር ግን በአንድ እጅ አይጨበጨብም» ያሉት የአመራ አባሉ መኢአዶች ዝግጁ በሆኑ ጊዜ ዉህደቱን ለማጠናቀቅ በራቸው ክፍት እንደሆነ አስረድተዋል።
አቶ አበባዉ በተናገሩት ላይ አስተያየት የሰጡን አንድ የፖለቲክ ተንታኝ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ዉህደቱ እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን ተስፋ ይጋራሉ። «መድረክ ችግር መሆን አልነበረበትም። ለምን በዉህደቱ ሂደት አንድነት ስለሚፈርስ። ነገር ግን መኢአዶች እንደ ችግር ካዩት፣ አንድነት እንደተባለው፣ ከመድረክ በይፋ ሲወጣ ፣ አቶ አበባዉ ዋና ችግራችን ያሉት ጉዳይ በይፋ መልስ ያገኛል። ያኔ ደግሞ ሌላ ጥያቄ ይዘው ካልመጡ» ሲሉም የመኢአድ እና አንድነት ዉህደት እንደሞተ ተደርጎ የሚናፈሰውን ጨለምተኛ ፕሮፖጋንዳ አጣጥለዉታል።
አቶ አበባዉ መሃሪ በ የሰጡትን ቃለ ምልልስ ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ !

No comments: