Friday, April 4, 2014

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከሕገ ወጥ ተግባሩ ታቀበ – ሰልፉ በሌላ ቀን እንዲደረግም ጠየቀ

April 4/2014
የአዲስ አበባ አስተዳደር መጋቢት 26 ቀን ለአንድነት ፓርቲ በላከው ደብዳቤ ፣ አንድነት መጋቢት 28 ቀን ሊያደርግ ያሰበዉ ሰላማዊ ሰልፍ ፣ ለሌላ ጊዜ እንዲተላለፍ ጠየቀ። ሰልፉ በታሰበበት ቀን ሌሎች ዝግጅቶች እንዳሉ የገለጸዉ የአስተዳደሩ ደብዳቤ «ተጨማሪ መስመርና ቦታ በመጥቀስ (ሰልፉን) የምታካሂዱበትን ሌላ ቀን ጭምር እንድታሳዉቁን እንገልጻለን» ሲል አስተዳደር ሕግና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ምላሽ ሰጧል።
በመጋቢት 28 ቀን ምን አይነት ሌላ ዝግጅት በአዲስ አበባ እንዳለ ለማወቅ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
አስተዳደሩ አሁን የላከው ደብዳቤ ሶስተኛ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የላካቸው ሁለት ደብዳቤዎች ሕገ መንግስቱን የሚጻረሩ ፣ ደንብን ስርዓትን ያልተከተሉ በመሆናቸው የአንድነት ፓርቲ እንደማይቀበላቸው ማሳወቁ ይታወሳል።«ለሕገ ወጥ እርምጃ ተባባሪ» አንሆንም ያለው አንድነት፣ አባላቱና ደጋፊዎቹ ትልናት መጋቢት 25 ቀን በአዲስ አበባ አራቱም ማእዘናት በራሪ ወረቀቶች ሲያሰራጩ እንደነበረ ይታወቃል።
የአንድነይ ፓርቲ አመራሮች ለአስተዳደር ምላሽ ለመስጠት ስብሰባ ላይ ሲሆኑ፣ ሕጉን ተከትሎ የቀረበ ደብዳቤ በመሆኑ፣ የአስተዳደሩ ጥያቀ በመቀበል የሰልፉን ቀን ይለዉጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።፡
በዚህ ጉዳይ ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ተንታኝ ፣ የመጀመሪያዎቹ ሁለት ሕገ ወጥ ደብዳቤ የጻፉትን ባለስልጣናት በሕጝ መጠየቅ እንዳለባቸው ገለጸው፣ የአንድነት ፓርቲ ሕግ ወጥ ደብዳቤዎችን ዉድቅ አደርጎ አባላቱ በድፍረት መቀስቀሳቸዉን፣ አንዳንዶቹም መአትሰራቸውን አድንቀዋል። «አንድነት ቀኑን የሚያራዝመው ከሆነ፣ የበለጠ ለቅስቀሳ ጊዜ ያገኛል» ያሉት እኝሁ ተንታኝ ፣ የአስተዳደሩን ደብዳቤ ድርብ ድርል ብልዉታል።
በተያያዘ ዜናም ሌላው በመጋቢት 28 ቀን ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀዉ የደሴ ሰልፍ የቅስቀሳ ዘመቻ በተጧጧፈ ሁኔታ እየተቀጣጠለ እንደሆነ ከስፍራዉ የደረሰን ዘገባ ይጠቁማል።

No comments: