Monday, December 26, 2016

የወያኔ አስተዳደር በአለም እጅግ አደገኛ ከሚባሉት 19 አገሮች ተርታ ተመደበ

Desember 26,2016
ዘርይሁን ሹመቴ
በለንደን የሚገኘው ሌጋተም ኢንስቲትዩት (Legatum Institute) በሚያደርገው አመታዊ የጥናትና የምርምር ፕሮግራሙ በአለማችን የሚገኙ እጅግ ሃብታምና ለኑሮ አመቺ አገሮችን እንዲሁም በተቃራኒው እጅግ አደገኛ የሆኑትንም ዝርዝር ይፋ ያደርጓል።
ይህ ተቋም ዘጠኝ (9) ቁልፍ መስፈርቶችን በመጠቀም በ2016 እኤአ የአገራትን ብልጽግና እና ለኑሮ ተሰማሚነታቸውን በጥናትና ምርምር በተደገፈ ሁኔታ አቅርቧል። እነዚህ መስፈርቶች የሚያካትቱት የኢኮኖሚ ጥራትን፣ የንግድ አከባቢን፣ አስተዳደርን፣ ትምህርትን፣ ጤናን፣ ደህንነትና ጸጥታን፣ የግለሰብ ነጻነትን፣ ማህበራዊ ሃብትን እንዲሁም ተፈጥሮአዊ አካባቢን እንደሆነ ተቋሙ አስፍሯል።
ሰሜን ኮሪያና በጦርነት የምትታመሰው ሶሪያ መረጃ ለመሰብሰብ እጅግ አስቸጋሪ ስለሆኑ ይህ ተቋም በጥናቱና ምርምሩ ለማካተት እንዳልቻለ ገልጿል። በአጠቃላይ 149 አገራት በዚህ ጥናት እንደተካተቱ ተገልጿል።
በወያኔ አስተዳደር የምትገኘው ኢትዮጵያም በዚሁ የጥናትና የምርምር ተቋም አመዳደብ መሰረት በጣም አደገኛ፣ እጅግ ደሃ፣ ደስታ የራቃትና ለጤናም አደገኛ ከሚባሉት አገሮች መካከል 19ኛውን ደረጃ ይዛ ትገኛለች። እንደ ጥናቱ ተቋም መሰረት ኢትዮጵያ በተወሰኑ መስፈርቶች መሻሻል ብታሳይም በትምህርት በኩል እጅግ ዝቅተኛ ውጤት ማስመዝገቧን አስፍሯል። በተጨማሪም በስራ ፈጠራና ለስራ አመቺ ሁኔታን በማቅረብም ዝቅተኛ ውጤት አስመዝግባለች።
የመን፣ አፍጋኒስታንና ሴንትራል አፍሪቃ ሪፐፕሊክ በዚሁ ጥናት ተቋም መሰረት ለመኖር እጅግ አስቸጋሪና አደገኛ ከሚባሉት አገሮች ከ1 እስከ3ኛ ያለውን ደረጃ በቅደም ተከተል ይዘዋል። በ2014 እኤአ በኢቦላ በሽታ ከሺህ በላይ ህዝቧን ያጣችው ላይቤሪያ በዚሁ በሽታ ምክንያት ከኢትዮጵያ አንድ ደረጃ ዝቅ ብላ 18ኛ ላይ ትገኛለች።

Monday, December 12, 2016

ወያኔ የመከላከያ ሰራዊቱ ወደ አርበኞች ግንቦት 7 እየተቀላቀሉ መሆኑን አመነ ።

Desember 12,2016
(ዘርይሁን ሹመቴ)
የወያኔን አገዛዝ በመክዳት ወደ ትጥቅ ትግሉ እየተቀላቀሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። በቅርቡ በሰሜን ጎንደር ለነጻነት እየተዋደቁ ያሉትን ጀግኖች የአማራ ተወላጆችን ለመጨረስ ወያኔ ከላካቸው ወታደሮች አብዛኞቹ ወደ አርበኞች ግንቦት ግንባር መቀላቀላቸው ይታወቃል። በቆራጥነት ቤተሰባቸውን ጥለው በየጫካው የሽምቅ ውጊያ በማድረግ ወያኔን እያርበደበዱ ያሉትን የአማራ ታጋዮችን ትጥቅ ለማስፈታት የሚልካቸው ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ወያኔን እራሱን ለመውጋት ከህዝቡ ጎን ለመቆም ግንባሩን ተቀላቅለዋል።
አገዛዙ የአርበኞች ግንቦት ሰርጎ ገቦች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ያዝከዎቸው ከማለት በስተቀር ከመከላከያ ሰራዊት እየከዱ አርበኞች ግንቦት 7ን ስለሚቀላቀሉ ሰራዊት መግለጫ ሲሰጥ አይሰማም። በብዛት ኤርትራ የሰለጠኑና የሰፈሩ ብሎ ወያኔ የሚፈርጃቸው የአርበኞች ግንቦት ወታደሮች በተቃራኒው በመላ ኢትዮጵያ በተለያየ መልኩ በጥልቀት ገብተው ራስ ምታት እየሆኑበትና የነጻነት ትግሉን እዚያው አገር ውስጥ እያደረጉ እንደሚገኙ ወያኔ ራሱ ለመካድ አዳጋች ደረጃ ላይ ደርሷል። በቅርቡም በሰሜን ጎንደር ህዝቡን በማነሳሳት በማደራጀት እንዲሁም ወታደራዊ እርምጃ ሲወስዱ በቁጥጥር ስር አዋልኩዋቸው ባላቸው የአርበኞች ግንቦት ና የኦነግ አባላት ላይ ክስ መስርቻለው በማለት አገዛዙ በርግጥም የትጥቅ ትግሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ እንደሆነ ማመን ችሏል።
በመከላከያ ሰራዊት ውስጥም ሳይቀር የአርበኞች ግንቦት አባላት ሰርገው ገብተውብኛል በማለት የተለያዩ ክሶችን አሁን አሁን እያቀረበ የሚገኘው የህውሃት አገዛዛ ከዚህ ቀደም ይህን በይፋ ለማመን ተቸግሮ እንደነበር ይታወቃል። የአርበኞች ግንቦት ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተደጋጋሚ ለመከላከያ ሰራዊቱ የወያኔ መጠቀሚያ ከመሆን የህዝብ አጋርነትን እንዲያሳይና ግንባሩን ተቀላቅሎ በአገዛዙ ላይ አፈ ሙዙን እንዲያዞር ያደረጉት ጥሪ በብዙ ለሚቆጠሩ ወታደሮች መክዳትና ወደ ነጻነት ጉዞው መቀላቀል አስተዋጾ አድርጋል።
አገዛዙ በአቃቢ ህጉ በኩል የአርበኞች ግንቦት የአገር ውስጥ አባላት በተንቀሳቃሽ ስልክና በፌስቡክ በመጠቀም አዳዲስ አባላትን በደብረ ዘይትና በተለያዩ የመከላከያ ሠራዊት እየመለመሉ እንደሚገኙ ደርሸበታለው በማለት ባሳለፍነው አርብ ክስ መስርቷል። ከዚህ በተጨማሪም የአርበኞች ግንቦት የአገር ውስጥ እንቅስቃሴ መረቡን በማስፋት በመረጃና ደኅንነት መስሪያ ቤትም ውስጥም ዘልቆ እንደገባ ክሱ ያመለክታል። በዚሁ እለት በቀረበው ችሎት ወያኔ ከአርበኞች ግንቦት ጋር በመተባበር ሲሰሩ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም ወደ ክስ አቅርቢያለው ብሏል።በአጠቃላይ ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትግል በርግጥም በኤርትራ ምድር ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑንና የህዝቡ እምቢተኛነት የነጻነት ታጋዮችን እንቅስቃሴ ወደ ፊት እየመራው እንደሆነ አገዛዙ በአቃቤ ህጉ ያቀረባቸው ክሶች ማመሳከሪያ ሆነዋል።

Saturday, December 10, 2016

የአውሮጳ ህብረት አባል በሆኑት ክብርት አና ጎመስ ላይ ህወት የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመረ

Desember 10,2016
በምርጫ 97 ወቅት የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን በመምራት ኢትዮጵያ ቆይተው ከተመለሱ ወዲህ የህወሃት አገዛዝ በዘጎቹ ላይ የሚፈጽማቸውን የሰባአዊ መብት ጥሰቶች እየተከታተሉ በማጋለጥ  የታወቁትን  የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ አባል ክብርት አና ጎመዝ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚያሰሙት ድምጽ እንዲያቆሙ ለመጠየቅ የህወሃት አገዛዝ በቅጥረኝነት ያሰማራቸው አባላቱና ደጋፊዎቹ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሎአል
የህወሃት የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ጋር በቅርበት እንደሚሠራ የሚታወቀው አይጋ ፎረም የተባለው ድረ ገጽ ላይ አባላትና ደጋፊዎች እንዲፈርሙት ተለጥፎ ያለው የተቃውሞ ፊርማ ደብዳቤ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው  ክብርት አና ጎመስ ባለፈው ወር መጀመሪያ ሳምንት ላይ ብራስልስ በሚገኘው የአውሮጳ ፓርላማ ጽቤት ስብሰባ ላይ ተሳትፈው ወደ አገራቸው ሲመለሱ በህወሃት ደህንነቶች ተይዘው እስር ቤት የተወረወሩት ዶክተር መረራ ጉድናን ለማስፈታት ህብረቱ ጠንካራ አቋም በኢትዮጵያ ላይ እንዲወስድ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ አዘጋጀተዋል  ። ክብርት አና ጎመስ የአውሮጳ ህበረት በህወሃት መራሹ አገዛዝ ላይ ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ከማዘጋጀታቸው በተጨማሪ ለህብረቱ የውጪ ግንኙነት ሃላፊ ለሆኑት ለማዳም ፌደሪካ ሞርጋሪኒ ባለፈው ሳምንት በጻፉት ደብዳቤ ላ፤ ዶ/ር መረራ ጉዲና የታሠሩት በርሳቸው መሪነት የአውሮጳ ህበረት በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚፈጸመው የሰባዊ መብት ጥሰት ለመስማትና አገራችን ውስጥ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ እምቢተኝነት ወዴት እንደሚያመራ ለመገምገም  አዘጋጅቶት በነበረው ስብሰባ ላይ መሳተፍቸው እንደወንጀል ተቆጥሮ ነው ማለታቸው ህወሃትን ክፉኛ አስቆጥቶታል። ክብርት አና ጎመስ ባልደረባቸው ለሆኑት ኢጣሊያዊቷ የህብረቱ የውጪ ግንኙነት ሃላፊ በጻፉት ደብዳቤ  ዶ/ር መረራ ጉዲና በህወሃት አገዛዝ ሽብርተኛ ተብሎ ከተፈረጀውና ህብረቱ አዘጋጅቶት በነበረው በዚያ ስብሰባ ላይ ከተገኙት ሌላው እንግዳ የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ጎን ለጎ ተቀምጦ መታየታቸው ብቻ እንደወንጀለኛ እንዳስቆጠራቸው ይህም ኢትዮጵያ ወስጥ የዜጎች ነጻነትና ሃሳብን የመግለጽ መብት ምን ያህል የከፋ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ አመልካች ነው ብለው መግለጻቸው ህወሃትንና ደጋፊዎቹን እጅግ ያናደደና የተቃውሞ ፊርማ እስከማሰባሰብ  ያደረሰ እንደሆነ በተቃውሞ ደብደቤው ላይ ተገልጾአ።
በዚህም የተነሳ ክብርት አና ጎመስ በኢትዮጵያ ጉዳይ ውስጥ እጃቸውን ከማስገባት እንዲቆጠቡ  ለመጠየቅ በህወሃት መሪነት የተጀመረው ፊሪማ የማሰባሰብ ዘመቻ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሚገኝባቸው አገሮች በሙሉ ውስጥ ለውስጥ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ሆኖም በርካታ ትኩረት ለማግኘት ያልቻለና በራሱ በህወሃት አባላትና ደጋፊዎች ዘንድ ሳይቀር እንደ ትልቅ ተስፋ መቁረጥ እርምጃ እንደታየ ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰ ከደረሰ መረጃ ለማወቅ ተችሎአል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በብድርና በተለያየ መንገድ ከአለም አቀፍ ህብረተሰብ የሚያገኘውን ገንዘብ ለገጽታ ግንባታ አገልግሎት በማዋል በጣም ውድ ገንዘብ በመክፈል ትላልቅ የሎቢ ተቋሞችን ቀጥሮ ሲያሰራ እንደኖረ ይታወቃል። ካለፈው እንድ መት ወዲህ በመላው አገሪቱ በተለይም በኦሮሚያ፤ በኮንሶና  በአማራ ክልሎች ተቃውሞን ለማፈን ሲል እየተወሰደ ባለው የሃይል እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጽሃን ዜጎች በግፍ መጨፍጨፋቸውና በሺዎች የሚቆጠሩት በጅምላ መታሠራቸው የአገዛዙን ፍጹም አምባገነንነትና አውሬነት ባህሪ ለአለም ህዝብ ያጋለጠ በመሆኑ  ተቀጥረው ይሠሩ የነበሩ የሎቢ ተቋሞች ሊያስተባብሉትና ሊሸፋፍኑለት ከሚችሉት በላይ እንደሆነባቸው በአሜሪካና በአውሮጳ ለህወሃት ተቀጥረው ከሚሠሩ እነዚሁ የሎቢ ድርጅቶች አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።