Wednesday, April 23, 2014

በቅስቀሳ ላይ የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ

April 23/2014
የሰማያዊ ፓርቲ ሚያዚያ 19 ቀን በአዲስ አበባ ለጠራው ሰልፍ፣ ቅስቀሳ ያደረጉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ በፌስ ቡክ ገጹ ገለጸ።
በአዲስ አበባ አስተዳደር አካባቢ ከተገኙ ምንጮቻችን በደረሰን ዘገባ መሰረት፣ የአዲስ አበባ አስተዳደር ከደህንነት ሃላፊዎች ፣ ሚያዚያ 19 ቀን ለሰማያዊ እንዲፈቀድ መመሪያ መስጠታቸውን በመግለጽ ፣ «እስከ አሁን የሰማያዊ ፓርቲ፣ ለሚያዚያ 19 ቀን ሰልፍ የእውቅና ደብዳቤ ገና በእጁ ያልያዘ ቢሆንም ፣ በአስተዳደሩና በደህንነት ሃላፊዎች መካከል የተፈጠረው ዉዝግብ ነገሩን በሌላ አቅጣጫ ካልወሰደው በስተቀር፣ ሰማያዊ የእውቅና ደብዳቤ በጥቂት ቀናት ዉስጥ ያገኛል ተብሎ ይጠብቃል» ስንል መዘገባችን ይታወቃል።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ለጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዛሬ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በርካታ አባሎቻቸው እንደታሰሩ ገልጸው፣ ከአስተዳደሩ እውቅና ገና እንዳላገኙም ተናገረዋል። በአዲስ አበባ አስተዳደር አካባቢ ያለውን ሁኔታ ለማጥራት ያደረግነው ሙከራ እስከአሁን አልተሳካም።
የታሰሩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሚከተሉት ናቸው ፡
ቂርቆስ ፖሊስ መምሪያ /6ኛ ፖሊስ ጣቢያ/
1. መርከቡ ሀይሌ
2. ሰለሞን ፈጠነ
3. ዘሪሁን ተሰፋዬ
4. አናኒያ ኢሳያስ
5. ፋሲካ ቦንገር
6. ጀሚል ሽኩር
7. ሰይፈ ፀጋዬ
ጉለሌ ፖሊስ መምሪያ
1. የሽዋሰ አሰፋ
2. እመቤት ግርማ
3. ዮናስ ከድር
4. እየሩሳሌም ተሰፋው
5. አበራ ኃ/ማርያም
6. አበበ መከተ

No comments: