Thursday, April 24, 2014

አንድነት ፓርቲ የሚሊዮኖች ድምፅ ቁጥር 3 ንቅናቄ ዝግጅት እንዲጀመር ወሰነ!! የሚሊዮኖች ድምፅ

April 24/2014

ንቅናቄው የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃና ፍትሐዊ ምርጫ (Millions of Voices for Free & Fair Election) የሚል መሪ ቃል ይኖረዋል፡፡
ከህዝብ ግንኙነት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ማክሰኞ ዕለት የአንድነት ስራ አስፈፃሚ አስቸኳይ ስብሰባ ካደረገ በኋላ ትግሉን ወደ ህዝቡ ማውረድና ህዝቡ የትግሉ ባለቤት እንዲሆን ለማስቻል የተጀመረው ንቅናቄ ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ተወያየ፡፡
ስራ አስፈፃሚው ወቅቱ 24 ሰዓት የሚሰራበት መሆኑን በማመን በሰላማዊ መንገድ ህዝቡን ያሳተፈ ትግል አቀጣጥሎ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻልና ለውጥ ማምጣት ከሚቻልባቸው መንገዶች አንዱ ሕዝባዊ ንቅናቄ መፍጠር እንደሆነ በማመን ከፍተኛ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
ከውይይቱ በኋላም በቅርቡ ይፋ የተደረገው የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት በተቀመጠው ዕቅድ መሰረት ከተጠናቀቀ በኋላ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃና ፍትሐዊ ምርጫ (Millions of Voices for Free & Fair Election) በሚል መሪ ቃል እንዲቀጥል፤ ምርጫውን መሰረት ያደረገ ሕዝባዊ ንቅናቄ እንዲጀመርና ለዚህ ሰፊ ዘመቻም ዝግጅት እንዲደረግ መወሰኑን እንዲሁም ይህንን ንቅናቄ የሚመራ ግብረ-ኃይል የሚቋቋምበት ሁኔታ በፍጥነት እንዲመቻች በሚል ከስምምነት መደረሱን መረጃ ያመለክታል፡:

No comments: