Tuesday, October 1, 2013

ሰው ለሰው እና አስናቀ ትንቅንቅ ውስጥ ገቡ።አስናቀ በቁጥጥር ስር

Oktober 1/2013

የሰውለሰው የቴሌቪዥን ድራማ ተውኔት በመንግስት ሃይሎች ትእዛዝ መሰረት ትንቅንቅ ውስጥ መግባታቸውን እና መንግስት በአቶ አስናቀ ገጸባህርይ መላቅጡ እንደጠፋው እና ትክክለኛውን የመንግስትን ገጸባህርይ የሚተረጉም እንደ ሆነና መንግስትም ይህንን ባህርይው ለህዝብ ይፋ መገለጹ ስላለወደደው ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጦ ምርምር እንዲደረግበት አዞአል ።

እንደ መንግስት ሃይሎች ትእዛዝ መሰረት ከሆነ አስናቀ በቁጥጥር ስር ውሎ በፖሊስ ምርመራ እንዲደረግበት የታዘዘ ስለሆነ   ሌሎች ገጸባህርያቶች እንዲቀጥሉ ታዟል  የዚህም ድራማ ጊዜ አጭር እንዲሆነ ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፎአል ደራሲዎቹም የስድስት ወር ጊዜ ገደብ ጠይቀዋል  ።

ይህ ከሆነ የፊልሙ መቼቱም ሆነ ሴራው ምን እንደሆነ እና ትርጉም አልባ ሊሆን የሚችል እንደሆነ ለማወቅ እና ለመገንዘብ አያዳግትም ::ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰው ለሰው ድራማ ከአረብ አገር ተከታታይ ድራማ ላይ የተቀዳ ነው በሚል ከፍተኛ ትችት እንደደረሰበት እና ፊልሙ የተቀዳበትን ዋነና የፊልም ስራ ምን እንደነበር በመግለጽ በተለያዩ መገናኛ ብዙሃኖች የቀረበ ከመሆኑም በላይ አስደንጋጭ የሆነ የሰው ልጆችን የስራ ፈጠራ ስርቆት ነው በሚል ሲተች መቆየቱ ይታወሳል። አንዳንድ መረጃ መረቦች በሰው ለሰው ድራማ መቋረጥ አስመልክቶ ከጻፉት መካከል ተስፋዬ ገብረአብ እንዲህ ሲል አቅርቦታል ሙሉውን እናስነብባችኋለን


አበበ ባልቻ እንደ አዜብ መስፍን

 
 “ሰው ለሰው” የተባለው ተወዳጅ ተከታታይ ድራማ ይቋረጥ ዘንድ ታዞአል። የተሰጠው ምክንያት፣ የአበበ ባልቻ (አስናቀ) ገፀባህርይ ከህግ በላይ መሆኑ እየበረታ መሄዱ ነው ተብሎአል። አስናቀ (አበበ ባልቻ) ህወሃትን ወክሎ እስከተጫወተ ድረስ የግድ ከህግ በላይ ሆኖ መቀጠል አለበት። ስለዚህ የድራማው ደራስያን ምንም ስህተት አልሰሩም። ያለውን ተጨባጭ እውነታ ነው ያንፀባረቁት። ሕወሓት ራሱን ማየት ደብሮት ይሆን?
 
ደራስያኑ የታዘዙት አስናቀን በቁጥጥር ስር አውለው ድራማውን እንዲጨርሱት ነው። ይሄ ግን ሊሆን አይችልም። ከእውነታው ጋር ይቃረናል። ምናልባት አበበ ባልቻ (አስናቀ) አዜብ መስፍንን ብቻ ወክሎ እየተጫወተ ነው ከተባለ ግን ያስኬዳል። ሆኖም አበበ ባልቻ ድራማው ላይ በቁጥጥር ስር ከዋለ በገሃዱ አለም አዜብም መታሰር አለባት።

የድራማው ደራስያን ድራማውን ለመቋጨት የስድስት ወራት ጊዜ ጠይቀዋል። የሃይለማርያም መንግስት ምላሽ እየተጠበቀ ነው።   በሌላም በኩል የወያኔው ቀንደና መል እክተኛ እየተባለ የሚጠራው Fitsum Berhane ፍጹም ብርሃኔ በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዲህ ሲል አስፍሯል
ፖሊስ ሰለሰው ድራማ ላይ "የኣስናቀ" ገፀ ባሀርይ በሕግ ቁጥጥር ስር ውሎ ድራማው እንዲጠናቀቅ ኣዘዘ፡፡
ፌዴራል ፖሊስ በኣስናቀ ገፀ ባህርይ በሸቀ መሰለኝ፡፡

No comments: