Wednesday, April 23, 2014

በጎንደር 30 ሺህ ቤቶች እንደሚፈርሱ ታወቀ – ‹‹በከተማዋ ውጥረት ነግሷል››

April 23/2014

ጎንደር፡- በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች የተገነቡባቸው ሶስት ሰፈሮች ሊፈርሱ መሆኑን በስፍራው የሚገኙ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች አስታወቁ፡፡ በከተማዋ ቀበሌ 18 ከተመሰረቱ ከ7 አመት በላይ የሆናቸው አርማጭሆ፣ ገንፎ ቁጭና ህዳሴ የተባሉ ሰፈሮች ውስጥ የተገነቡ ከ30 ሺህ የሚልቁ ቤቶችን እንዲያፈርሱ ለነዋሪዎች ትዕዛዝ በተሰጠበት ስብሰባ የተካፈሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

በስብሰባው ላይ ነዋሪዎቹ፣ ‹‹ህገ ወጥ ከሆነ ያኔ ሕገ ወጥ ነው ልትሉን ይገባ ነበር፡፡ ህገ ወጥ ነው ከተባለስ ይህ ሁሉ ዜጋ በርካታ ገንዘብ አፍስሶ ቤት ከሰራና ለ7 አመት ከኖረ በኋላ ህጋዊ ማድረግ አይቻልም ነበር? ይህም ካልሆነ ተለዋጭ ቦታ ተሰጥቶንና ሰፊ ጊዜና ተለዋጭ ጊዜ ተሰጥቶን
እንጂ በድንገት ተነሱ ልትሉን አይገባም›› የሚል መከራከሪያ ማንሳታቸው ታውቋል፡፡ በተጨማሪም፣ ‹‹እኛ የራሳችን አገርና ቦታ ላይ የምንገኝ ዜጎች ነን፡፡ ቤታችንን የሰራነው ማንም ሳያግዘን በራሳችን ጥረት ነው፡፡ የኤርትራ፣ የሱዳን፣ የሶማሊያ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ሲገቡ የሚገባቸው ነገሮች ይሰጣቸዋል፡፡ እኛ ግን ያለምንም ቅድመ ዝግጅት፣ ካሳና ተለዋጭ ታ ሳይሰጠን ቤታችሁን አፍርሱ መባላችን ዜግነታችንም ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው›› ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡

የከተማዋ ባለስልጣናት በበኩላቸው፣ ‹‹መንግስት ህገ ወጥ ነው ብሎ የሚያምነውን ሁሉ ማፍረስ መብቱ ው፡፡ አይደለም ጎንደር አዲስ አበባ ውስጥም ቤት ይፈርስባቸዋል፡፡›› በሚል ለማሳመን ሞክረዋል፡፡ ‹‹በዚህ ጊዜ ውስጥ ልጆቻችን ይዘን የት ልንሄድ ነው… ሽማግሌዎችስ የት ይደርሳሉ?›› የሚሉ ሌሎች አንገብጋቢ ጥያቄዎችን አንስተው አጥጋቢ ልስ ያላገኙት ነዋሪዎቹ ከባለስልጣናቱ ጋር ባለመስማማታቸው አብዛኛዎቹ ‹‹ማፍረስ ከተፈለገ እናንተው አፍርሱት እንጂ እኛ አናፈርስም፡፡›› በሚል ስብሰባውን አቋርጠው መውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ነዋሪዎቹ እስከ ሚያዚያ 7 አፍርሱ፣ ካለፈረሳችሁ እኛው ስለምናፈርሰው እቃችሁን አውጡ ቢባሉም አሁንም ድረስ በአቋማቸው ጸንተው የሚመጣውን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ምንጮቻችን ጨምረው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ህዝቡ በክረምት ተፈናቅሎ የት ይደርሳል በሚልና እንዲፈርስ በሚፈልጉት

የከተማው ባለስልጣናት መካከል ውጥረት መንገሱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተጨማሪም ህዝብን አሳምጻችኋል የተባሉ 12 ሰዎች መታሰራቸውና ከጎንደር በተጨማሪ ቆላ ድባና ሌሎች ከተሞችም ቤቶች እንዲፈርሱ ትዕዛዝ መሰጠቱን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በተመሳሳይ ከሰሞኑ በባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎችን ከማፈናቀል ሂደት ጋር በተገናኘ ህዝብና ፖሊስ በመጋጨታቸው የሰው ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

No comments: