Friday, April 25, 2014

[የሳዑዲ ጉዳይ] የዜጎቻቸውን ክብር እና የሃገራቸውን በጎ ገጽታ በማጉደፍ ስራ ላይ የተጠመዱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ዲፕሎማቶች

April 25/2014

በሳውዲ አረቢያ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንገስት ዲፕሎማቶች ሪያድ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ስም በከፈቱት የፌስ ቡክ ገጽ ሰሞኑንን አንዲት ኢትዮጵያዊት አሰሪዎን በሰቃቂ ሁኔታ በመጥረቢያ ፈልጣ ገደለች በሚል ጥቂት የሳውዲ መገናኛ ብዙሃኖች ሲያሰሙ የከረሙትን የተለመደ የቁራ ጩሀት በማስተጋባት የህዝብ እና የሃገራቸውን በጎ ገጽታ በማጠልሸት ስራ ላይ ተጠምደው መክረማቸውን ምንጮች ከሪያድ ገለጹ፡፤ ይህ ኢትዮጵያውያኑን በአውሬነት የመፈረጅ ዘመቻ የተለመደ እና ቀደም ብሎ ሪያድ ከተማ ውስጥ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ የጅምላ ግድያ እና ድብደባ ከመፈጸሙ በፊት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ የግል ሚዲያዎች በሃሰት ኢትዮጵያውያኑን ሲወነጅሉ እንደ ነበር የሚናገሩ የአይን እማኞች ሰሞኑን ሳውዲ ውስጥ በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተው አረብ ኒውስ http://www.arabnews.com/news/554481 የተባለ ጋዜጣ ሳውዲ አረቢያ ጣይፈ ከተማ አንዲት ኢትዮጵያዊት የ50 አመት የልጆች እናት የሆነች አዛውንት በመጥረቢያ ፈልጣ ገደለች የሚል ዜና መዘገቡን ተከትሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች እና አንዳንድ ሃላፊነት የማይሰማቸው ምስለኔዎች ነገሩን በማጋነን በተለያዩ ሶሻል ሚዲያ ገጾቻቸው ላይhttps://www.facebook.com/ethiopian.embassy.5 በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ከጋዜጣው በላይ እንደ ገደል ማሚቱ በማስተጋባት እያሰሙን ያለው መረን የለቀቀ ዘግናኝ ወሬ ከሃገራዊ ከህደት ተለይቶ እንደማይታይ ይናገራሉ፡፤

ሰሞኑን እራሱን አረብ ኒውስ እያለለ የሚጠራው ይህ ጋዜጣ ሳውዲ አረቢያ ጣይፍ ከተማ በስተደቡብ 130 ኪ/ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ መንደር ውስጥ በአንድ ኢትዮጵያዊት ተፈጸመ ብሎ የተዘገበውን አስቃቂ ወንጀል ለኢትዮጵያውያን ክበር ተቆርቋሪ የሆኑ ወገኖች ቦታው ድረስ ሄደው ጉዳዩን ለማጣራት ባደረጉት ሙከራ በተጠቀሰው አካባቢ የሚኖሩ ወገኖች እየተነገረ ያለውን ነገር እንደማንኛውም ሰው በወሬ ደረጃ ከመስማት ውጭ መንደራቸው ውስጥ እንደዚህ አይነት ወንጀል መፈጸሙን ምንም እንደማያውቁ እንዳረጋገጡላቸው ጠቅሰው የጋዜጣው ዘገባ ከተለመደው በሬ ወለደ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደማያልፍ ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል።

በተለይ ይህንን ወሬ የሚያራግቡ አንዳንድ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ የማይታይባቸው የዲፕሎማቱ ግብረ አበረ አበሮች የ50 አመቷ እማወራ በጸሎት ላይ ሳለች የተገደለቸው የክርስትና እምነት ተከታይ በሆነች ኢትዮጵያዊት መሆኗን በግል የማህበራዊ ገጾቻቸው የሌሎችን ቀልብ ለመሳብ የሚዘግቡትን አካላት የሚቃወሙ ኢትዮጵያውያን እነዚህ ግለሰቦች በመሃከላችን አለመተማመንን ለመፍጠር እየፈጸሙ ያለው ድብቅ አጀንዳ ሰሞኑን የአረብ ሚዲያዎች በወገኖቻችን ላይ እያሰራጩ ካለው ጥላቻ የማይለይ እና የብዙሃኑን ህይወት በአዲስ መልክ አደጋ ላይ ለመጣል ከሚቆፈር ጉድጓድ በመሆኑ ዲፕሎማቱ እና ጀሌዎቻቸው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከወዲሁ ሃይ ሊባሉ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል።

ጅዳ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በበኩላቸው በዲፕሎማቱ ተፈፀመ በተባለው ነገር አዝነው በአረብ ኒውስ ስለተዘገብው ዜና ዲፕሎማቱ የቱንም ያህል መርጃ ባይኖራቸው እንኳን ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ደህነት ሲባል ኤምባሲው በስፋት የተወራውን ወንጀል አጣርቶ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ በማፈላለግ የህዝብን ደህነት እና የሃገሪቱን በጎ ገጻታ ማስጠበቅ ይገባቸው እንደነበር ገልጸው በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት እንዲሉ ዲፕሎማቱ ኢትዮጵያውያንን ጭራቅ አድርገው ለመሳል ከሚዳክሩ የአረብ ጋዜጣች ያገኙትን መረጃ ተቀብለው ህዝብን ያስተምራል በሚል አስፋሪ ተሞክሮ በኤንባሲው ስም በከፈቱት ድህረ ገጽ እያስተጋቡ ያለው ጩሀት ወደፊት በታሪክም በህግም እንደ ሚያስጠይቃቸው ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በመዲናይቱ ሪያድ አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ የ 9 አመት የአሰሪዎን ልጅ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለች አስመስለው አንዳንድ የአረብ ጋዜጦች የኢትዮጵያውያንን ክበር እና የሃገራችንን በጎ ገጽታ በሚነካ መልኩ ለመዘገብ ያደረጉት ጥረት እንዳልተሳክ የሚገልጹ ወገኖች የሳውዲ ፖሊስ ነፍሰ ገዳይ ብሎ በቁጥጥር ስር ባዋላት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ላይ ባደረገው ምርመራ የህጻኗ አሞሞት ከቤት ሰራተኘዋ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌው መሆኑን በማረጋገጥ ኢትዮጵያዊቷ የቤት ሰራተኛ በነጻ ማሰናበቷ ይታወሳል።

በሪያድ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ዲፕሎማቶች በኢትዮጵያ ኤምባሲ ስም በከፈቱት ሶሻል ሚዲያ በማርኛ ለጠፉ ስለተባለው ኢትዮጵያውያንን የሚወነጅል አስቃቂ ዜና ማብራሪያ ለመጠየቅ ያደረኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም ።
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

No comments: