Friday, April 11, 2014

ሰበር ዜና ባህር ዳር ከተማ የሰዎችን ህይወት የነጠቀ ግጭት ተነሳ ተኩሱ አሁንም እንደቀጠለ ነው

April 11/2014

የወያኔ መንግስት ካድሬዎች አሁንም ሕዝቡን ማሸበር ተያይዘውት ይገኛሉ:: የኢትዮጵያ ሕዝ ብ በሀገሩ ላይ መኖር አልቻለም በወያኔ ሰይጣናዊ ስራ ሕዝብ ከቤቱ እየተፈናቀለ በአረመኔዎች ጥይት እየተቆላ ነው :: ዛሬም በባህ ዳር ከተማ በነዋሪው ላይ አሳዛኝ ግፍ እና በደል እየተፈጸመበት ይገኛል::

 በፖሊስና በህብረተሰቡ መካከል በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ስዎች ሞተዋል የቆሰሉም አሉ፡፡ ከፖሊስም እንዲሁ የቆሰሉ አሉ፡፡ ተኩሱ ለተከታታይ ሶስት ሰዓታት የተደረገ ሲሆን ህዝቡ ቤታችን ለአምስትና ስድስት ዓመታት ያህል ሰርተን እየኖርንበት ያለ እና ሌላ ተለዋጭ ቤት የሌለን በመሆኑ ወይ ተለዋጭ ቦታና ቤት ስጡን ወይም ደግሞ አመት ባሉን እባካችሁን እንዋል አታፍርሱብን ሌላ መቀመጫ የለንም ብሎ ሲጮህ ማፍረሱን ቀጠለው በፖሊስ እና ሚሊሻ የታጀበው አፍራሽ ከህዝቡ ጋር ግጭት ጀምሮ…የተኩስ እሩምታ ህዝቡ ላይ መተኮስ በመጀመራቸው ህዝቡም ምላሽ በመስጠት ሲብሰውም ወንጭፍ በመጠቀም ሴቱም ወንዱም አንድ ላይ ሆነው ትንሽ ትልቅ ሳይል ተማምለው በመውጣት ከፖሊስ ጋር ፖሊስ በጥይት ህዝቡም በድንጋይና ባገኘው ሁሉ ተኩስ ሲለዋወጡ ለሶስት ሰዓታት ቆይተዋል፡፡

 በርካቶች ቆስለዋል ከፖሊስም ከህዝቡም፡፡ በኋላም ፖሊስ ህዝቡን ሲያባርር ህዝቡ እደገና ፖሊስን ሲያባርር ከቆዩ በኋላ ህዝብ ፖሊሱን ሁሉ እያባረረ ወደ መሃል ከተማው ቀበሌ አስራ ሶስት ጎፋ አካባቢ ሲደርሱ የመጣው ልዩ ሃይል ህዝቡ ላይ አስለቃሽ ጭስ በመጠቀም ለመበተን ቢሞክሩም ሳይችሉ ቀርተው ህዝቡ በአንድ ሆሆሆ ብሎ በመሄድ ልዩ ሃይሎችንም በድንጋይና ጠርሙስ መቀጥቀጥ ይጀምራል፡፡

 በዚህ ሰዓት የሞቱና የቆሰሉ በርካታ ናቸው ለጊዜው ቁጥራቸው አልደረሰንም ከባህርዳር ያለው ምንጫችን ሲልክልን ለህዝብ እናደርሳለን፡፡ ፖሊስም ግሬደር በመያዝ ችግሩ ወደተፈተረበት አካባቢ በመሄድ አያሌው ጎበዜ የሚባለውን ሰፈር እስከ ቤት እቃዎቻቸው ድረስ ጠራርጎ በማፈራረስ እና በአካባቢው የሚንቀሳቀስን ወጣት በሙሉ ለቃቅመው በማሰር ላይ ሲሆኑ አልፎ አልፎም የተኩስ ድምፅ ይሰማል፡፡

 ፖሊስ ሴቶችንም ወንዶችንም ሽማግሌ ህፃን ሳይል በማሰር ላይ የሚገኝ ሲሆን የአካባቢው ወንዶች የት እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም ሚስቶቻቸው እህት እናቶቻቸው አባት ወንድሞቻቸው በአጠቃላይ እዛ አካባቢ ያለው ሁሉ ወደ እስር ቤት ተግዟል፡፡ ይህ ተኩስ ልውውጥ ላይ እንደ አይን እማኞች ከሆነ ከበርካታ የባህርዳር ቀበሌዎች የተሰባሰበ ህብረተሰብ የሰፈሩን ስዎች ሲያግዝና ፖሊስን አብሮ ሲያባርር ልዩ ሃይልን ሲያባርር እንደነበር ገልፀዋል፡፡

ሌላ ቀበሌዎች ይህን ያደረጉበት ምክንያት ሲገለፅም ነግ በኔ እያሉ እንደሆን ታውቋል፡፡ ለጊዜው የአባቱ ስም ያልታወቀ ጨመረ የተባለ ወጣት ግንባሩ ላይ በጥይት ተመትቶ አስከሬኑ ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ፖሊሶች ቀምተው አስከሬኑን አንሰጥም ማለታቸውም ታውቋል፡፡

 ለጊዜው አሁን ትንሽ ጋብ ያለ ቢሆንም አልፎ አልፎ በዚህ ሰዓትም ተኩስ ድምፅ ይሰማል፡፡ እነዚህ አካባቢዎች እና ቀበሌዎች ለፖሊስ ኢፍታዊ ድርጊት አንገዛም ላቤን ጠብ አድርጌ አፈር ቆፍሬ ደክሜ የሰራሁትን ቤት ሲያሰኝህ እየመጣህ ልታፈርሰው አትችለለም ፈቃድ አውጥቼ ስንት ጊዜ በሙሰኛ ባለስልጣናት ተበዝብዠ የሰራሁትን ቤቴን ሌላ መውደቂያ ሳይኞረኝማ አታፈርሰውም ብለው ለበርካታ አመታት ሲደክሙ ቆዩትን ቤት በሌሊት እንደ ሽፍታ የማፍረሻ ትዕዛዝ ሳያሳዩ ለማፍረስ መሞከር ህገወጥነት ሆኖ እያለ የንፁ ሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስ የመንግስትን ወሮ በላነትና የፖሊስን ደደብነት የሚያሳይ አሮጋንተነት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን የባህርዳር ነዋሪዎች ይሰጣሉ፡፡

 ተጨማሪ ዘገባዎችን እንደደረሱን እናደርሳለን፡፡

ለሞቱት ነፍስ ይማር ለቆሰሉትም ቁስላችሁን ውሻ ቁስል ያድርግላችሁ እንላለን፡፡

ይህ ህገወጥ እርምጃ ህዝብ ላይ የሚፈፅም መንግስትን ምን ይሉታል፡፡

No comments: