Written by መታሰቢያ ካሣዬ, AddisAdmassNews.com
የተስተካከለ ቁመናውና የስፖርተኛ አቋሙ የብዙ ሴቶችን ዓይን ይስባል፡፡ ጐተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ ጂምናዚየም ውስጥ ተቀጥሮ ደንበኞቹን ስፖርት ያሰራል፡፡ በተግባቢነቱ፣ በተጨዋችነቱና በሰው አክባሪነቱ ሁሉም ይወዱታል፡፡ ከሥራው ቦታ ሳይርቅ ጎተራ ላንቻ አካባቢ ከግለሰብ በተከራየው አንድ ክፍል ቤት ውስጥ እየኖረ ሳለ ነው ህይወቱን የሚቀይር አንድ አጋጣሚ የተፈጠረው፡፡
ያቺን ዕለት አይረሳትም፡፡ ሴትየዋ ጠና ያሉ ናቸው - ከ50 ዓመት በላይ ይሆናቸዋል፡፡ የተደላደለ ኑሮ እንዳላቸው ሁለመናቸው ይናገራል፡፡ የጂም ደንበኛ ሆነው ሲመዘገቡ ምንም የተለየ ነገር ይፈጠራል ብሎ አላሰበም፡፡ እንደ ሁልጊዜው በፈገግታና በትህትና ተቀብሎ አስተናገዳቸው፡፡
የሴትየዋ የፊት ገፅታ የዕድሜያቸውን መግፋት ቢያጋልጥም በተለያዩ ሜካፖችና ቅባቶች እንዲሁም በዘመናዊ አለባበሣቸው ወጣት ለመምሰል ጥረዋል። እንዲህ ያሉ ወይዘሮዎች በአብዛኛው አንቱ መባልን አጥብቀው እንደሚጠሉ ያውቃል። ለዚህም ነው “አንቺ” እያለ ማናገር የጀመረው። አዲሷ የጂም ተማሪ፣ ወጣቱ ላይ ዓይናቸውን ጥለዋል፡፡ ዘንካታነቱና የስፖርተኛ ቁመናው ማርኳቸዋል፡፡
የለበሰው ቲ-ሸርትና ቁምጣ በጡንቻዎቹ ተወጣጥሯል፡፡ አይናቸውን ከሱ ላይ መንቀል ተሣናቸው፡፡ በስፖርት ሰበብ መቀራረብና መነካካት መኖሩን ደግሞ ወደውታል፡፡ ከወገብሽ ጎንበስ እግርሽን ከፍ ክንድሽን ዘርጋ ከደረትሽ ገፋ እያለ ---የሚሰሩትን እንቅስቃሴ ይነግራቸዋል አንድ ሁለት አንድ ሁለት እያለ፡፡ እሳቸው ግን ብዙም አይሰሙትም፡፡ ሁለመናቸው የሚነቃቃው ቀረብ ብሎ ሲያሰራቸው ነው - ወገባቸውን ደገፍ፣ ክንዳቸውን ያዝ፣ እግራቸውን ሳብ እያደረገ ሲያንቀሳቅሳቸው አንዳች የተለየ ዓለም ውስጥ የገቡ ይመስላቸዋል፡፡ የሰራ አካላቸው ይፍታታል። ፊታቸው ይበራል፡፡ ጨዋታቸው ይደራል፡፡ ለመግባባት ጊዜ አልፈጀባቸውም፡፡ ሲውል ሲያድር መግባባታቸው እየጠነከረ፣ግንኙነታቸው የተለየ መልክ እየያዘ መጣ፡፡
ወጣቱ አሰልጣኝ የሴትየዋን ስሜት ተረድቶታል፡፡ እሳቸው በቀደዱለት ቦይ መፍሰሱን አልጠላውም - የት እንደሚደርስ ባያውቀውም፡፡ ከልጅነት ጀምሮ ከሚያውቀው የድህነት ህይወት ያላቅቀው እንደሆን ማን ያውቃል? ሴትየዋ የስፖርት ሰዓታቸውን ከቀን ወደ ምሽት ሲያዛውሩትም ለምን ብሎ አልጠየቃቸውም፡፡ ልሸኝህ የሚለው ነገር የመጣውም ይሄኔ ነው፡፡ ቤቴ ቅርብ ነው ብሎ መከራከር አልፈለገም፡፡ ወይዘሮዋ ብልሃተኛ ናቸው፡፡ መንገዱን ማርዘምያ መላ አላጡም፡፡ ይሄ ኮረኮንች ነው፣ያኛው እግረኛ ይበዛዋል እያሉ ጨለማ ጨለማውን ዙሪያ ጥምጥም ይዘውት ይሄዳሉ። እንዲያም ሆኖ መድረስ አይቀርም፡፡ “ደህና እደሪ” ብሎ ከመኪና ሲወርድ፣ ጎተት አድርገው ጉንጩን መሳም አስለምደውታል፡፡ መሳሳ
ሙ ከጉንጭ ወደ ከንፈር ለመዝለል ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ መሸኛኘት ብቻ ሳይሆን አብሮ ማምሸትም ተጀምሯል፡፡ እራት ግብዣው ቀልጧል፡፡ ውድ ውድ ስጦታዎች እየጎረፉለት ነው፡፡ ረብጣ ብሮች ሸጎጥ ይደረግለታል።
ወጣቱ እስራው ቦታ ድረስ ሰተት ብሎ የመጣለትን ሲሣይ በደስታና በእልልታ የማይቀበልበት ምክንያት አልታየውም፡፡ መጪውን ያሳምረው እንጂ፡፡ ሴትየዋ በጥቂት ሣምንታት እጃቸው ውስጥ የገባላቸውን ግዳይ፣እያንከበከቡ ወደ መኖርያ ቤታቸው ይወስዱ ጀመር፡፡ አብሮ መዋል አብሮ ማደር መጣ፡፡ የጎመዡበትን ዘንካታ ቁመናና የተደላደለ ሰውነት፣ እንደልባቸው አገኙት፡፡ በፈርጣማ ክንዱ አቅፎ በትኩስ የወጣትነት ትንፋሹ አሞቃቸው፡፡ እርጅና ተባርሮ ወጣትነት ዳግም ተመልሶ የመጣ መሰላቸው፡፡ ዓለማቸውን አዩ፡፡ እሱም የምኞቱን አገኘ፡፡ 300ሺህ ብር አውጥተው የገዙትን አዲስ ሞዴል ያሪስ መኪና በስሙ አዛውረው ሰጡት፡፡ ከኪራይ ቤት አውጥተው በ440ሺህ ብር ኮንዶሚኒየም ገዝተው አስገቡት፡፡ ፍቅራቸው ደራ፡፡
የሴትየዋ ባለቤት ከሁለት አመት በፊት ነው በድንገተኛ ህመም የሞቱት፡፡ ሁለት ልጆቻቸው ያሉት ደግሞ ጣሊያን ነው፡፡ እናም ምንም የሚያሳስባቸውና ነፃነታቸውን የሚጋፋ ነገር አልነበረም፡፡ ወይዘሮዋና ወጣቱ ያለገደብ ደስታቸውን አጣጣሙት፣ አንድም የቀራቸው የመዝናኛ ቦታ የለም - ሁሉንም በየተራ አዳረሱት፡፡ ወጣቱ የጂም አሰልጣኝ ሥራውን ለቆ ወይዘሮዋን መንከባከብ የሙሉ ጊዜ ሥራው አደረገው፡፡ ከእጃቸው የማይለዩት ቦርሳቸው አደረጉት፡፡ በፍቅር ከነፉለት፡፡ የወዳጅ ዘመድ ምክር የሚሰሙበት ጆሮ አልነበራቸውም፡፡ “ኧረ ተይ --- አሁን ይሄ ጎረምሳ ልጅሽ አይሆንም?” የሚሏቸውን ሁሉ ጠሏቸው፡፡ ባስ ሲልም ራቋቸው፡፡ ጓደኞቻቸውንማ ልክ ልካቸውን ይነግሯቸዋል “ምቀኝነት ነው፤ እንዲህ የሚያደርጋችሁ --- ያጣ ወሬ ነው” አፋቸውን ያሲዟቸዋል፡፡
እሱም ታዲያ ከጓደኞቹ የሚያበሽቀው አላጣም “እናትህ ከምትሆን ሴት ጋር ምን ነካህ?” ይሉታል፡፡ እሱም “ምቀኞች! እናንተ ባታገኙ ነው” ይላቸዋል፡፡ የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም እንዲሉ በሴትየዋ ዘንድ ለመወደድና ለመታመን መትጋቱን ቀጥሏል። ብዙም ሳይቆይ የወ/ሮዋን ሱፐር ማርኬት የማስተዳደር ኃላፊነት ተረከበ፡፡ “እሷ የስኬቴ ሰበብ ናት፡፡ ያልኳትን የምታደርግልኝ የጠየኳትን የምትሰጠኝ የፈለኩትን የምታሟላልኝ ዓለሜ ናት፡፡” የሚለው ወጣቱ፤ ከእኔ የሚጠበቀው እሷን መንከባከብና በፍቅር ማጥገብ ብቻ ነው” ይላል፡፡ የቀድሞ ጂም አሰሪ ዛሬ ወጣት አባወራ ሆኗል፡፡ “ሃኒ” እያለ ከሚያቆላምጣቸው ወይዘሮ ጋር በትዳር ተሳስሮ ሲኖር ሁለት ዓመት አስቆጥሯል፡፡
ዛሬ ዛሬ ሹገር ማሚዎች የልጅ ልጆቻቸው የሚሆኑ ለጋ ወጣቶችን በገንዘባቸው አጥምደው፣ የወሲብ እስረኛ የሚያደርጉበት ሁኔታ በከተማችን የተለመደ ተግባር እየሆነ መጥቷል፡፡ ሹገር ማሚዎቹ የኢኮኖሚ አቅማቸው የዳበረ፣ የፈለጉትን ለማድረግ የሚያስችል በቂ ገንዘብ ያላቸው፣ ዕድሜያቸው ከ48-65 ዓመት የሚሆናቸው ሲሆኑ ልጅና ቤት ንብረት ኖሮአቸው ትዳራቸው በሆነ ምክንያት የፈረሰ ወይም ባሎቻቸውን በሞት ያጡ፣ አንዳንድ ጊዜም በትዳር ውስጥ ሆነው ከባሎቻቸው የሚፈልጉትን የወሲብ ደስታ በተለያየ ምክንያት ማግኘት የተሳናቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሹገር ማሚዎች፤ የቡና ቤት ባለቤቶች፣ ልጆቻቸው በውጪ አገር የሚኖሩና የራሳቸው ድርጅት ያላቸው ዘናጭ ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች በአብዛኛው የሚያጠምዱት ዕድሜያቸው ከ23-30 ዓመት የሚሆናቸው ጥሩ ቁመናና ደንዳና ሰውነት ያላቸው፣ ተግባቢና ተጫዋች ወጣት ወንዶችን ነው፡፡ ወጣት ወንዶች፤ ሹገር ማሚዎችን የሚቀርቧቸው ለገንዘባቸው ብለው ነው፡፡ ይሄን ደግሞ ራሳቸው ሹገር ማሚዎቹ ቢያውቁም ሌላ አማራጭ ግን የላቸውም፡፡ በርካታ ወጣት ወንዶችም ለጊዜያዊ ችግራቸው መወጫ እነዚህን ሴቶች የሙጢኝ ብለው ሹገር ቤቢነቱን ያሣምሩታል፡፡
“የተወለድኩት ከድሃ ቤተሰብ ነው፤ትምህርቴን እንኳን በአግባቡ መማር እንዳልችል ድህነቴ ትልቅ እንቅፋት ሆኖብኛል፡፡ ከ10ኛ ክፍል ላይ የተቋረጠው ትምህርቴ እዛው ላይ እንደቆመ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ሥራ የለኝም፡፡ ህይወት ለእኔ አስቸጋሪ ነበረች፡፡ ተምሮ ሥራ ይዞ ይጦረናል ለሚሉት ደካማ ወላጆቼ፣ እኔው ራሴ ተጧሪና ሸክም መሆኔ በጣም ያበሳጨኝ ነበር፡፡ በተፈጥሮ የታደልኩት ጥሩ ቁመናና ደንዳናው ሰውነቴ ችግረኛ መሆኔን እየደበቁልኝ በምቾት የምኖር ያስመስሉኛል፡፡ ሰፈር አካባቢ ቆሞ መዋሉ ሲሰለቸኝ አካባቢያችን በሚገኝ አንድ ትልቅ የሴቶች ፀጉር ቤት አጠገብ የሞባይል ማደሻ ሱቅ ከፍቶ ከሚሰራው ጓደኛዬ ጋ እየሄድኩ መዋል ጀመርኩ፡፡ ይህም ከማሚ ጋር የምትዋወቅበትን አጋጣሚ ፈጠረልኝ፡፡
እውነት ለመናገር እኔ ስተዋወቃት በመጀመሪያ ለእንደዚህ አይነት ጉዳይ አስቤአት ወይንም እሷ አስባኛለች ብዬ አልነበረም፡፡ ፀጉሯን ለመሠራት ወደ ፀጉር ቤቱ በመጣች ጊዜ ሁሉ መኪናዋን የምታቆመው በጓደኛዬ ሞባይል ማደሻ ሱቅ በራፍ ላይ ነበር፡፡ ትውውቃችን እያደገ ሲሄድ ረዘም ላለ ጊዜ አብሮ መጫወትና መነጋገሩን ቀጠልን፡፡ ከፀጉር ቤቱ ተሰርታ ስትወጣ፤ ሻይ እንጠጣ እያለች ይዛኝ መሄድ ሁሉ ጀመረች፡፡ ጓደኛዬ ሁኔታው እንዳላማረውና ሴትየዋ ልታጠምደኝ እንደሆነ ነገረኝ፡፡
አድርጋው ነው፡፡ አብረን ቆይተን ስንለያይ እንደዘበት ጃኬት ኪሴ ውስጥ የምትሸጉጣቸው ረብጣ ብሮች ስንቱን ችግሬን እንደሸፈኑልኝ እኔ ነኝ የማውቀው፡፡ ከጥቂት ቀናት በኋላ ቤቴን ላሳይህ ብላ ይዛኝ ሄደች፡፡ ሳር ቤት አካባቢ ያለው የሴትየዋ ቤት ዘመናዊ ቪላ ነው፡፡ ቤቱ ከባሏ ጋር ፍቺ ሲፈፅሙ የደረሳት እንደሆነ ነገረችኝ፡፡ ከባሏ ጋር የተለያየችው ስሜቷን ሊጠብቅላት ባለመቻሉ እንደሆነም አጫወተችኝ፡፡ ታዛዥ ፍቅረኛዋ ሆንኩ፡፡ የእናትና የልጅ ያህል የተራራቀውን ዕድሜያችንን ዘንግተን አብረን ማበዱን ተያያዝነው፡፡ ቤተሰቦቼን ከድህነት አወጣሁ፡፡ ያማረ ለብሼ ጥሩ መኪና ይዤ ወደአደኩበት ሰፈር ስሄድ መንደርተኛው ሁሉ ያከብረኛል፡፡ ለቤተሰቦቼ ሀብታም ሚስት ማግባቴን ነገርኳቸው እንጂ “ሚስቴን” አላሳየኋቸውም፡፡ በኋላ ላይም ከሴትየዋ ጋር የማደርገው ወሲብ አልጥምህ አለኝ፡፡ በዚህ ላይ በድህነት ዘመኔ አፈቅራት የነበረች ጓደኛ ነበረችኝ፡፡
ከሴትየዋ ጋር ከተዋወቅን ጀምሮ የራቅኋት ቢሆንም አልፎ አልፎ ማስታወሴና መናፈቄ አልቀረም፡፡ ጓደኛዬን ፈልጌ አገኘኋትና ጓደኝነታችንን ቀጠልን፡፡ አሁን ኑሮዩ የተደላደለ ሆነ፡፡ ገንዘብና ድሎትን ከማሚ፣ ፍቅርን ከጓደኛዬ ማግኘት ጀመርኩ፡፡ ይህ ሁኔታዬ ግን ብዙ አልቆየም፡፡ ማሚ ከጓደኛዬ ጋር ያለኝን ግንኙነት ደረሰችበት፡፡ ፀባችን እየከረረ ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ እኔ በቂ ገንዘብና ንብረት ይዤ ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ሹገር ማሚዬ እንደማታስፈልገኝ እርግጠኛ ነበርኩና ሆን ብዬ ፀቡ እንዲከር አድርጌ ተለየኋት፡፡ ራቫ ፎር መኪናዋንና በርካታ መጠን ያለው ገንዘቧን ግን በእጄ ለማድረግ ችያለሁ፡፡”
በትዳር ውስጥ ያሉና በዕድሜ የገፉ ባሎች ያሏቸው ሴቶችም በአብዛኛው ሹገር ማሚነቱን ይከውኑታል፡፡ እነዚህ ሴቶች የትላልቅ ቡና ቤቶች፣ ሆቴሎች፣ ሱፐር ማርኬቶችና ድርጅቶች ባለቤቶች ናቸው፡፡ በድርጅቶቻቸው ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ጥሩ ቁመና ያላቸው፣ ተግባቢ ወጣቶች ሹገር ማሚዎቹ አይን ከገቡ አበቃላቸው፡፡ በገንዘባቸው ሃይል አንበርክከው የወሲብ እስረኞቻቸው ማድረጉን ያውቁበታል፡፡ በራሳቸው ቤት፣ ወይም ቤት ገዝተው አሊያም ተከራይተው ፍላጐታቸውን ሁሉ እያሟሉ የሚያስቀምጧቸው ጐረምሶች፤ ሹገር ማሚዎቹን እንደ ኮረዳ እያሽኮረመሙ የወጣትነት ትኩስ ፍላጐትና ስሜት እንዲሰማቸው ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በአብዛኛው በሹገር ማሚዎች የተያዙ ወንዶች፤ ከ“ሚስቶቻቸው” ጋር አብረው በአደባባይ እንደ ልብ መታየትን አይፈልጉም፡፡ ይህ ደግሞ ሹገር ማሚዎቹ እንደ ፍላጐታቸው በየአደባባዩና በየመዝናኛ ቦታው ከ “ጐረምሳቸው” ጋር በፍቅር ለማበድ እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል፡፡ አብይ ታሪኩ (ስሙ የተቀየረ) ስለ ሹገር ማሚው ሲናገር፤ በተለየዩ መዝናኛ ቦታዎች ላይ ከእኔ ጋር አብሮ መታየት እንዲሁም በየአደባባዩ በማቀፍና በመሣም ፍቅሬን እንድገልፅላት ትፈልጋለች፡፡ ይህ ደግሞ እኔ ፈፅሞ የማልወደውና የማልፈልገው ጉዳይ ነው” ሲል ገልፆታል፡፡ አብዛኛዎቹ ሹገር ማሚዎች፤ ለፍቅረኞቻቸው ፈፅሞ ነፃነትን አይሰጡም፡፡ ከእኔ ከተለየ ሌላ ሴት (ወጣት) “ይጠብሳል” ብለው ስለሚያስቡ የ “ጐረምሶቻቸውን” ውሎ መከታተል ይፈልጋሉ፡፡ አስር ጊዜ እየደወሉ “የት ነህ?” የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውም የተለመደ ነው፡፡ ከወንድ ጓደኞቻቸዉ ጋር እንኳን ቢሆን ለረዥም ጊዜ እየተዝናኑ እንዲቆዩ አይፈቀድላቸውም፡፡ ከሹገር ማሚዎቻቸው ጋር በጊዜ ሂደት ተስማምተው በፍቅር የወደቁ፣ ተጋብተው ህጋዊ ትዳር የመሰረቱም በርካታ ወጣት ወንዶች አሉ፡፡
“ስንጀምር በዚህ መልኩ ግንኙነታችን ይቀጥላል ወይም ዘላቂነት ይኖረዋል ብዬ አልነበረም፡፡ በሂደት ግን በቃ ተመቸችኝ ፤ስንጀምር የነበሩን በርካታ ልዩነቶች እየጠፉ ፍላጐታችን እየተቀራረበ ሄደ፡፡ ታምኚኛለሽ--- ድብን ያለ ፍቅር ያዘኝ፡፡ የእንጋባ ጥያቄውን ያቀረብኩላት እኔ ነኝ፡፡ ከዚህ በኋላ ልጅ የማግኘት ተስፋ እንደሌለኝ ባውቅም ብዙ ስሜት አልሰጠኝም፡፡ የምትወደድ አይነት ሴት ነች፤ ተመችታኛለች፡፡ አሁን እንኳን ከተጋባን ሶስት ዓመት አልፎናል፡፡ የእውነት ነው የምወዳት” ዘውዱ (ስሙ የተቀየረ) ስለ ሹገር ማሚው የተናገረው ነው፡፡
ሹገር ማሚዎች በአብዛኛው የሚጠሉት ነገር ከሹገር ቤቢዎቻቸው ጋር በመዝናኛ ቦታዎች ሲሄዱ “ልጅሽ ነው?” የሚሉ የጓደኞቻቸውን ጥያቄ ነው፡፡ እንዲህ እየተባሉም ቢሆን ሹገር ቤቢዎቻቸው ተለይተዋቸው እንዲቀሩ አይፈልጉም፡፡ ዛሬ ዛሬ በርካታ ወጣቶች፤ ሹገር ማሚዎችን እያሳደዱ መተዋወቅና ማጥመዳቸው የተለመደ ተግባር እየሆነ ነው፡፡ ከሹገር ማሚዎቻቸው የሚያገኙትን ገንዘብ የዕድሜ እኩያዎቻቸውን (ፍቅረኞቻቸውን) ለማዝናናት ይጠቀሙበታል፡፡ በሹገር ማሚዎቹ ለመመረጥና መስፈርቶቻቸውን ለማሟላት ወጣቶቹ ትግል ይዘዋል፡፡ ሹገር ማሚዎቹ በአብዛኛው ሰውነታቸው ደልደል ያለ ተጫዋችና ተግባቢ ወጣት ወንዶችን ለፍቅረኝነት ይፈልጋሉ፡፡ ሹገር ማሚዎቹ እነሱ የሚፈልጉትን አይነት አገልግሎት እየሰጡ አብረዋቸው የሚዘልቁ ወጣቶች የት እንደሚገኙ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ለዚህ ተግባር ተመራጩ ቦታ ጅምናዚየሞች፣ ማሳጅ ቤቶች፣ ሲኒማ ቤቶችና ናይት ክለቦች ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሹገር ማሚዎች በአገናኝ ደላሎች አማካኝነት የፈለጉትን ወጣት ከእጃቸው ለማስገባት አይቸገሩም፡፡ እድሜ ለቴክኖሎጂ! ዛሬ ደግሞ ሹገር ማሚዎች የፈለጉትን አይነት ወጣት የሚያገኙበትና የሚቀጣጠሩበት ድረገፅ ተከፍቶ ሥራውን በስፋት እየሰራ ይገኛል፡፡ Friendfinder:sugermummy tips.com, Adult friend finder seeking arrengment.com የተባሉት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ ዛሬ ዛሬ ከታዋቂ አርቲስቶቻችን መካከል በሹገር ማሚ ወጥመድ ተይዘው ተፈላጊውን አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ወጣቶች እንዳሉም ይነገራል፡፡ ከዕድሜ ጋር ግብግብ የተያያዙት ሹገር ማሚዎች፤ የዕድሜያቸው ጀንበር አዘቅዝቃ ይህቺን አለም ከመሰናበታቸው በፊት ያሻቸውን ለማድረግ፤ የፈለጉትን ለመፈፀም ትግል ይዘዋል፡፡ ወጣት ወንዶቹም (ሹገር ቤቢዎቹ) የኢኮኖሚ ችግራቸውን የሚቀርፉላቸውን ሹገር ማሚዎች ለመንከባከብና ለማስደሰት እየተጉ ይገኛሉ፡፡

No comments:
Post a Comment