Monday, July 22, 2013

የእናት ጡት ነካሾቹ ህወሃት ና ጀሌወቹ

 ከዛሬ 21 ዓመት በፊት በኢትዮጵያ ህዝቦች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ስልጣን የተቆናጠጠው ህወሃት/ወያኔ ገና ከጅምሩ የሃገርና የህዝብ ሃብትና ንብረት መዝረፍና ማውደም መለያ ባህሪው የሆነው የእናት ጡት ነካሹ ህወሃት በሆድ አደር ጀሌዎቹ ተባባሪነት እንሆ ለ21 ዓመታት የሃገራችንን ቁሳዊይና አካላዊ ሃብቶች እያራቆታት ይገኛል::

  ህወሃት/ወያኔ በ 17 አመታት የጫካ የሽፍትነት ዘመኑ በቀመረው ፀረ-ኢትዮጵያ የጫካ ሕጉ በትግል ጎራ ሳይቀር አብረወት ሲቆስሉና ሲዋደቁ ከነበሩት እውነተኛ ታጋዮች መካከል፣ በሃገራቸው አንድነትና ልኡላዊነት ላይ ጽኑ እምነት የነበራቸውን፣የኢትዮጵያ ህዝብ የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትንና ዴሞክራሲ ስርአት በኢትዮጵያ መገንባት አለበት የሚል አቋም ያላቸውን እና የህዝብ ወገናዊነት የነበራቸን በየጊዜው በማሶገድ ፀረ-ኢትዮጵያ አቋም ያላቸው ሃይሎች ተሰባስበው ና ተማምለው እንሆ ዛሬ በአዝማቹ ህወሃት እና ከየብሄር ድርጅቱ ተወክለናል ባዮቹ ጀሌዎች በዚህ ትውልድ ላይም ለዜጎች መብትና ነጻነት የሚታገሉትን፣ በጹሁፍ ላይ የሰፈረው ሕገ መንግስት በተግባር ሊተገበር ይገባል የሚል ጥያቄ የሚያነሱ አካላትን፣ የህዝብ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ምላሽ ሊያገኝ ይገባል በማለትጥያቄ የሚያነሱ የህብረተሰብ ክፍልን፣በሃይማኖታችን ጣልቃ አይገባብን፣በሃገራችን ሁላችንም እኩል ልንስተናገድ ይገባናል፣የሠብአዊ መብት ሊከበር ይገባል፣ የመሰብሰብና የመደራጀት መብታችን ሊገደብ አይገባውም ወዘተ በማለት ጥያቄ የሚያነሱ የህብረተሰብ ክፍሎችን አሸባሪ ፣ነውጠኛ፣ ሙሰኛ፣ የአመለካከት ችግር ያለበት ወዘተ በሚሉት ተለጣፊ ቃላቶቹ በመጠቀም ትውልዱን በመግደል፣ በማሰር፣ ከሃገር በማባረር እያመከነው ይገ ኛል::

    የዛሬ የእናት ጡት ነካሾቹ ህወሃት ማ! ያ- ን- ዬ በታጋይ ስም በሚሉበት በዚያን ዘመን ደጉ ያገሬ ሰው የውስጥ የልባቸውን መርዝ ሳይረዳ የተባለለት ዴሞክራሲ ከፊቱ እየታየው ለተራበው በማጉረስ ፣ለተጠማው በማጠጣት፣መንገድ ለጠፋው መንገድ በማሳየት፣የተመታን ሸሽጎ ሂዎት በማትረፍ፣ገደል ፈንቅሎ መንገድ በመስራት፣ጅረት ጫካውን በማሻገር ፣ስንቅ ቋጥራ/ሮ/ ይቅናችሁ ብላ /ሎ/ ለመረቀ እናት/አባት፣እህት/ወንድም ህወሃት/ወያኔ በሃብት ላይ ሃብት አካብተው በዘረፉት ሃብት ደንዝዘው የህዝብን ጥያቄ ወደጎን ትተው ያ ሂዎታቸውን የታደጋቸውና ለድል ያበቃቸውን ህዝብ በፀረ-ዴሞክራሲ ህጋቸው መፈናፈኛ አሳጥተውታል ፥ ህዝቡይህንን ብሶቱን በንጉርጉሮ እንዲህ ሲገልጸው ይደመጣል::

 እሾህ ብቻ ሆኗል እግሬን ብዳብሰው
እንዴት መራመጃ መሄጃ ያጣል ሰው::

 ወ--ገ--ን በዚያን ዘመንታጋይ አይራብም ብላ ፈትፍታ ያጎረሰች እናት በኖረችበት ቀዬ /ቦታ/ ያረገዘችውን ልጅ እንኳን ሳትወልድ ቤንሻንጉል ጉምዝ አገርሽ አይደለም በሚል ከቤቷ ተፈናቅላ /ተገፍትራ /ጫካ ስትወልድ ዝምእንበል?

- የሃገር አለኝታ የሆነው አርሶ አደሩ ያ ትልቅ ሰው በግዳጅ ከ ቤንችማጅዞን ውጣ ሲባል ቤንችማጅዞን ሃገሬ ካልሆነማ ! ቀን ይሰጠኝ ሃብትና ንብረቴን ሰብስቤ እወጣለሁ ብሎ እጁን ዘርግቶ ሲማፀን እጣ ፋንታው ዱላ ሲሆን ምን እንፍጠር ? ምንእንበል ?

በሃገራችንና በህዝባችን ላይከግዜ ወደ ግዜ እየተባባሰ የመጣውን የሰብአዊ መብትጥሰት፣ እየደረሰ ያለውን የሃገር ውድመትእና የሕዝባችንን ሰቆቃ ለመታደግ ይህንን እኩይ ስርዓት ማሶገድ አማራጭ የሌለው ተግባር ነው::

 በመሆኑም በየትኛውም ቦታ የምንገኝ የህዝባችን ሰቆቃና ስቃይ የሚቆረቁረን ኢትዮጵያዊ ሁሉ ልብ ለልብ ተገናኝተን ይህን ፀረ-ዴሞክራሲና ፀረ-ህዝባዊነት የተንሰራፋበትን ስርአት ሁለገብ ትግል ለማድረግ እንነሳ
ሁላችንም ለሃገራችን የድርሻችንን እናበርክት!

አዘጋጅ ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
by maleda times

No comments: