Tuesday, July 2, 2013

በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የቦንድ ምንተፋ በተቃዋሚዎች የድምጽ ማእበል እየታመሰ ነበር

አትላንታ ጆርጂያ፥
ሳዲቅ አህመድ

አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራን የሚያዉለበልቡ ብቻ ሳይሆን የለበሱም ነበሩ።የኢትዮጽያ መንግስት አባይን ለመገደብ በሚል ስም ቦንድን ለመመንተፍ የሚያደርገዉን ሴራ እንቃወማለን አባይ ከመገደቡ በፊት ነጻነት፣ ዲሞክራሲ፣ ፍትህ ለመላዉ ኢትዮጵያን ያሻል በማለት በዘር በሃይማኖት ሳይለያዩ እስከ 200 የሚደርሱ ሰዎች ድምጻቸዉን ያሰማሉ።

Protest in Atlanta, Georgia

ቁጥራቸዉ የተመናመነ ግለሰቦች ሃፍረት በተሞላበት መልኩ ወደ አዳራሹ ቢያመሩም ከመካከላቸዉ አንዳንዶቹ አንዳንዶቹ  በአልሞት ባይ ተጋዳይነት የሟቹን መለስ ዜናዊ ቲሸርት በመልበስ ቢንጎማለሉም በፍርሃት እየነፈሩ መሆናቸዉ ግን ያስታዉቅ ነበር። “ተከብረሽ የኖርሽዉ ባባቶቻን ደም እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይዉደም” በማለት ኅብረ-ዜማን የሚያሰሙት ኢትዮጵያዉያን “ተመልከቱ ኢትዮጵያን አስመልክቶ ዝግጅት ቢያዘጋጁም የኢትዮጵያን ባንዲራን ለማዉለብለብ ግን ፍላጎቱ የላቸዉም! እኛ ግን በአባይ ስም አትነግዱ ስንላችዉ የኢትዮጵያን ባንዲራ እያዉለበለብን ነዉ” ይላሉ።

Ethiopians Protest in Atlanta, Georgia

“እኛ  ኢትዮጵያዉያን ነን ወደ አዳራሹ ለመግባት የዘር መለዮ ሳይሆን  ኢትዮጵያዊ ማንነት ነዉ የሚያሻን” ብሉዉ ለመደራደር ቢሞክሩም አዘጋጆቹ የአባይ ጉዳይ በዘር የተደለደለ እንዲመስል አድርገዉታል። ያም ሆኖ ቁጥራቸው ከሰላሳ የሚያንሱ የቦንድ ተመንታፊዎች በሰአት 400 ዶላር በሚከፈልበት አዳራሽ ዉስጥ ሲገቡ ተስተዉሏል። በአዳራሹ ዉስጥም መዝጋቢ ሰዉ እንደሌለ ፣እንኳን ደህና መጣቹ ባይ እንዳልነበረ አንድ በተክለ ሰዉነቱ የስብሰባዉን አዘጋጆች የዘር መስፍርት የሚያሟላ ልቦናዉ ግን ለኢትዮጵያዊነቱ የጸና ግለሰብ ዉስጥ ገብቶ የታዘበዉን ገልጿል።

Rally in Atlanta, Georgia

በተገቢዉ መልኩ ጥናት ያልተደረገበት አባይን የመገደቡ ሙከራ የዲፕሎማሲና የደህንነንት አደጋ አለዉ፤ ስልጣንን ለማራዘምና አቅጣጫን ለማስቀየር በሚደረግ ደፋ ቀና ነዉ አባይን መገደብ በሚል ስም የኢትዮጵያ መንግስት የሚንቀሳቀሰዉ የሚሉ ተቺዎች ብዙ ናቸዉ። ባንጻሩ አባይ አሁን አይገደብ የሚሉት ፖለቲካውዊ ክፋት የተጠናወታችዉ ናቸዉ በማለት የኢትዮጵያ መንግስት ለማጣጣል ይሞክራል። አንድ የጋራ እዉነታ ግን አለ  በአባይ የመገደብ ጉዳይ ኢትዮጵያዉያን የተለያየ ሃሳብ የላችዉም! ህዝባዊ ዉክልና የሌዉ ህወሃት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ያላዋቂ ሳሚ ምን ይለቀልቃግድቡን   አያርገዉ  ባዮች ቢኖሩ እንጂ…
ጁን 30 በሰዉ ድርቅ የተመታዉ የአትላንታ ጆርጂያ የቦንድ ምንተፋ ሂደት ክዉ ድንግጥም ያለ ነበር።

No comments: