Monday, July 8, 2013

የሰሜን ጎንደር የአንድነት ሰብሳቢ ህገወጥ እስር ተፈፀመባቸው

የሰሜን ጎንደር የአንደነት አመራሮችን ማሰር ቀጥሏል ዛሬ ዞኑ የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ አለላቸው አታለለ ህገወጥ እስር ተፈፅሞባቸዋል፡፡ የክልሉ መንግስት በሚፈፅመው ህገወጥ እስርና እንግልት አንድነት ሰላማዊ ሰልፉን እንደማያስሰርዘው ገልጧል፡፡

አንድነት በጎንደር የጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማደናቀፍ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የክልሉ መንግስት የሰሜን ጎንደር አንድነት የፓርቲውን አመራሮች የማሰር ዘመቻ ጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት ዛሬ አቶ አለላቸው አታለለ በህገወጥ መንገድ ታስረዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፉን በመንግስት ህገወጥ እርምጃ እንደማይቀለበስ አስታውቋል፡፡ ፓርቲው የጀመረውን ህዝባዊ ንቅናቄ አጠናክሮ እንደሚቀጥልና ከፍተኛ አመራሮቹም በንቅናቄው ላይ ግምባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን የሚመጣውን መስዋዕትነት ከህዝቡ ጋር በመሆን ለመቀበል መዘጋጀታቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡፡

No comments: