Monday, July 22, 2013

የሳኡዲ መንግስት ኢትዮጵያን ሰራተኞችን አልፈልግም አለ፣ብዙ ኢትዮጵያውያኖች በፖሊስ ጣቢያ ማቆያ ቦታ ታግተዋል !

በዚህ ባሳለፍነው ሁለት ሳምንት የ6 አመት እድሜ ያላት የሴርያን ዜግነት እና እንዲሁም የሳኡዲ ዜግነት ያላት የ 10 አመት ታዳጊ ልጃገረድ በኢትዮጵያን የቤት ውስጥ ሰራተኞች ተገድለው መቀበራቸውን ባለፈው ሳምንት መዘገባችን ይታወሳል እንዲሁም የሳኡዲ መንግስት ኢትዮጵያን ሰራተኞችን አልፈልግም እያለ እንደሆነ ማተታችንን እየጠቆምን ዛሬም ቁርጥ ያለውን አቋም አሳውቆአል ።

በዛሬው እለት የመረጃ ማእከላችን ባገኘው መረጃ መሰረት የሳኡዲ መንግስት  ኢትዮጵያኖች ሰራተኞችን ከአሁን በሁዋላ ወደ ሃገሩ ለማስገባት ፍቃደኛ እንዳልሆነ ጠቁሞአል ።በከፍተኛ ደረጃ በወንጀል የተጠመዱ ናቸው ሲልም የወቀሰ ሲሆን ዜጎቼ ያለምንም ምክንያት ወደ ሞት እንዲሄዱብም አልፈልግም የደህንነታቸውንም ጥበቃ ለማድረግ ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ማስቀረቱ ተገቢ ነው ሲል ገልጦአል ።

 የሰራተኞች ጉዳይ ሚንስትር በአፍሪካ የቤት ውስጥ ሰራተኞች ላይ የሚሰጠውን ቪሳ እንዲቆይ እና በወንጀል ስራቸው ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቆአል ይህም ከሆነበት እለት ጀምሮ ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ወደ ሃገሯ ማስገባት እንደማትፈቅድ የሳኡዲ መንግስት አስተዳደር የሰራተኞች ሚንስትር አስታውቃለች ።በሃገር ውስጥ ገቡ የተባሉት እና ስራ ያልጀመሩትን ኢትዮጵያውያኖችም በፖሊስ ጣቢያ እስር ቤት የማቆያ ቦታ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻቸው ዲፖርት ተደርገው ወደ ሃገራቸው እንዲገቡ ጥያቄ በማቅረባቸው ወደ ሃገራቸው የሚላኩበት ቀን እስከሚቆረጥበት ቀን ድረስ በፖሊስ ጣቢያ ሊቆዩ እንደሚችሉ የፖሊስ ኮማንደር የሆኑት ኮሎኔል አብዱል ራህማን ጁሪያድ አሳውቀዋል።

ምክትል የሰራተኞች ጉዳይ ሚንስትሩ ደግሞ ሙፋር ቢን ሰአድ አል አቅባኒ እንዳሉት ከሆነ በየ እለቱ ከሁለት መቶ ኢትዮጵያኖች በላይ በሃገራቸው እንደሚገቡ ተናግረው እነሱንም በፖሊስ ጣቢያው ማቆያ እንዳስቀመጡአቸው የተናገሩ ሲሆን ለዚህ መፍትሄው ምን እንደሆነ ለማወቅ አስቸጋሪ ነው ሲሉ ተናግረዋል ከዚያም ውጭ ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ሰራተኞችን ዲፖርት ለማድረግ ዝግጅት ላይ ሲሆኑ እነዚህ በአንድ ግሩፕ ሆነው ይመለሳሉ ተብለው የተወሰነላቸው ናቸው ሲሉ ለመገናኛ ብዙሃኖች አስታውቀዋል ።በሌላም በኩል የቪሳ እና ዶክመንቴሽን እንዲሁም ፓስፖርት ዲፓርትመንት ቃላቀባይ የሆኑት አህመድ አል ለሃዲን ማንኛውንም ኢትዮጵያዊ ከተሰጠው የጊዜ ገደብ ውጭ ልናዎይ አንፈልግም በአሁን ሰአት ስራቸውን መቀጠል እና መቆየት የሚፈልጉትን የኢትዮጵያን ዜግነት ያላቸውን በሙሉ የስራ ፈቃዳቸውን ልናድስላቸው አንፈልግም ብለዋል።

ማንኛውም ዜጋ ወደ ሳኡዲ ለመኖር የሰበአዊ ዜግነት ሊኖረው ይገባል ሲሉም አክለው ጠቁመዋል ።ለመረጃው ማለዳ ታይምስ ከአፍሪካ ኢንተሊጀንሲ ጋር በመተባበር ያቀረበው ሪፖርት ነው ።ሙሉ ዘገባውን በአፍሪካ ኢንተሊጀንስ ሚድያ ያገኙታል ።

by maleda times

No comments: