Friday, July 26, 2013

አንድነትን ለመቃወም ኢህአዴግ ያዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ባለስልጣናቱን ከፋፈለ

በደቡብ ወሎ ዞን ኩታ በር ወረዳ ነዋሪዎች አንድነት ፓርቲ ሐምሌ 7 ቀን 2005ዓ.ም. በደሴ ከተማ ያደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያወግዙ በከፍተኛ ጫና እና ማስገደድ ጥረት ቢያደርግም የጠበቀውን ያህል ሰው እንዳልወጣለት ምንጮቻችን ከስፍራው ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡
 
ኢህአዴግ ትናንት ሐምሌ 17 ቀን 2005ዓ.ም. ጠዋት በኩታ በር አንድነትን በሰላማዊ ሰልፍ እንዲቃወሙ የአስገዳጅ ጥሪ የተደረገላቸው አብዛኞቹ ነዋሪዎች ባለመሳተፋቸው ኢህአዴግ የወረዳውንና የዞኑን የኢህአዴግ ካድሬዎችና አመራሮችን በግምገማ እያስጨነቀ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ 

በጥቂት ሰዎች ተደረገው ሰልፍ ላይም ተሳታፊዎች በተለይ የአንድነት ፓርቲ ስምን እየጠቀሱ እንዲያወግዙ ቢነገራቸውም በሰልፉ ፊት ለፊት ያሉ ተሳታፊዎች ብቻ ስም እየጠሩ ሲያወግዙ እንደነበር በሰለፈፉ ላይ የተገኙ ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡ ይህም የወረዳውንና የዞኑን ባለሰልጣናት መከፋፈሉ ተጠቁሟል፡፡ ስለጉዳዩ የወረዳውን ኃላፊዎች ለማናገር ብንሞክርም ተንቀሳቃሽ ስልካቸውን ባለማንሳታቸው አልተሳካም፡፡

No comments: