Tuesday, July 30, 2013

በኢትዮጵያ የሚገኘው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተቋማዊ ብቃት አጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ባለ ጉዳዮች በስፍራው ይገኝ ለነበረው ለኢሳት ዘጋቢ ገለጹ::

ሐምሌ ፳፪(ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለጉዳዮቹ  የከፍተኛው ፍርድ ቤት በደርግ ጊዜ ከነበረው የቀበሌ ፍርድ ሸንጐ ማነሱንና በጥራትም በብቃትም እጅግ መውረዱን ገልጸዋል::

የከፍተኛው ፍርድ ቤት በሚሊዮን የሚቆጠር የገንዘብና የንብረት ክርክሮችን የሚዳኝ ሲሆን አልፎ አልፎ የወንጀል ጉዳዮችን ይመለከታል::

ይህ ፍርድ ቤት የተሟላ የህዝብ መጸዳጃ የሌለውክመሆኑም በላይ መብራት ሲቋረጥ ጀነሬተር ባለመኖሩና የፍርድ ቤቱ የድምጽ ቀረጻ ስለሚስተጎገል ባለጉዳዮችም ለተጨማሪ ቀጠሮ ይዳረጋሉ ።

ባለ ጉዳዮች ከዘረዘሩዋቸው ችግሮች መካከል ማስረጃ ከመሰባሰቡ በፊት በትዛዝ ዉሳኔዎችን መስጠት፣  የፍርድ ቤት እግድ ከተሰጠባቸው በኋላ ጉዳዮ ባልታወቀ ምክንያት እግዱን ማንሳት በዚህም የተነሳ ክስ የቀረበባቸው ግለሰቦች ንብረታችውን ሸጠው እንዲጠፉ ማመቻቸት፣  ክስ ከተከፈተባቸው ፋይሎች ከውስጣቸው ጠቃሚ የሆኑ ፋይሎች እንዲጠፉ ማድረግ፣  በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተቀጥረው ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች በድለላ ስራ ላይ በመሰማረታቸው ና ከዳኞቸ ባላቸው ቀረቤታ የፍርድ ውሳኔ ዎችን እንዲጣመሙ ማግባባት፣  ክስ የቀረበባቸውን ጉዳዩች ዳኞች ባግባቡ አለመረዳትና አለማንበብ ለጉዳዩም በቂ ትኩረት አለመስጠት፣  ክስ የቀረበባቸው ጉዳዩች የገንዘባቸው ልክ ብዙ በሚሆንበት ጊዜ ከግለሰቦች ጋር ለመገናኘት መሞከር ይጥቀሳሉ

በጉዳዪ ዙሪያ አንዳንድ ዳኞችን ለማነጋገር ቢሞከርም እነሱም ከአቅማቸው በላይ የክስ ፋይሎች እንደሚሰጣቸውና በዚህም የተነሳ ጉዳዮችን በንቃት ለመከታተል እንዳቃታቸው በመጥቀስ የፍርድ ቤቱ አስተዳደር ተጨማሪ የሰዉ ሃይል እንዲመድብላቸው ጠይቀዋል::

በሌላ ጉዳይ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄዱ የመሬትና የቤት ሽያጮች ችግር እያጋጠማቸው ነው
አንዳንድ ግለሰቦች መሬትና ቤት ከገዙ በሃላ ሌሎች ግለሰቦች ተመሳሳይ የቤት ካርታ ፕላን በማቅረባቸው በይዞታ ይገባኛል ጥያቄ ለችግር መዳረጋቸውን ገልጸዋል::

ምንቾች አንዳሉት የጸረ ሙስና ኮሚሽን በወቅቱ ማለትም ቤቶችና መረቶች ለሽያጭ በሚቀርቡባቸው ግዜ ጣልቃ መግባት ሲገባው ውሎችና ሽያጮች ከተፈጸሙ በሃላ ንበረቱን ለምርመራ እፈለገዋለው በማለት ገዝዎችን ሲያጉላላ ሻጮች  ገንዘባቸውን ይዘው ይሰወራሉ::

ከጸረ ሙስና በተገኘው መረጃ  ሙሰረት በሺዎች የሚቆጠር የቤቶችና የመሬት ይዞታወች ለምርመራ  እንደሚፈለጉ ታውቋል::

No comments: