Sunday, July 14, 2013

የሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሂጃብ መብት ይከበር በማለት ጥያቄ ያቀረቡ የትግራይ የመጅሊስ አካላት በሽበርተኝነት ተከሰው በእስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው::

by MINILIK SALSAWI » Today, 14:24
በመቀሌ ከተማ የሙስሊም ሴት ተማሪዎች የሂጃብ መብት ይከበር በማለት ጥያቄ ያቀረቡ የክልሉ የመጅሊስ አካላት በሽብረተኛነት ተከሰው በእስራት እንዲቀጡ ተወሰነባቸው::

በትግራይ ክልል በመቀሌ ከተማ የሴት ተማሪዎች የሂጃብ መብት ይከበር የሚል ጥያቄ ያነሱ 3 የክልሉ መጅሊስ አካላቶች በሽብርተኛነት ተወንጅለው ፍርድ ቤቱ በእስራት እንዲቀጡ እንደወሰነባቸው ምንጮች አስታወቁ፡፡

በመቀሌ ከተማ በ መረሲፉል ፓራዳይዝ በሚባል ትምህርት ቤት ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሒጃብ ይልበሱ ኣይልበሱ በሚል በቀን 24/01/2005 በተፈጠረ ውዝግብ ተያይዞ የታሰሩ ሲሆን ፍርድ ቤት በወቅቱ ቀርበው በዋስ የተለቀቁ ሲሆን ጉዳያቸው በቀነ ቀጠሮ ሲንጓተት ከቆየ ቡሃላ የወረዳው ፍርድ ቤት በነፃ እንዳሰናበታቸው ተሰምቷል፡፡

ሆኖም ፀረ ኢስላም አመለካለከት እንዳለው የሚነገርለት የክልሉ ባለስልጣን የሆነው አቶ መሃሪ ፍሰሃ ከ አቃቤ ህጉ ጋር በጋራ በመሆን ይግባኝ የጠየቁባቸው ሲሆን ፍርድ ቤቱም ጉዳያቸውን በድጋሚ በመመልከት በሽብርተኛነት በመወልጀል በእስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በፍርድ ቤቱ ውሳኔም መሰረት፡-

1.አብድል ጀሊል ሰኢድ የትግራይ ክልል ሙስሊም ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር እና የመቀሌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ሂጃብ ይፈቀድ የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው አሸባሪ ተብለው 2 አመት ከ 9 ወር አስራት አንዲቀጡ

2.አቶ መሐመድ ሻፊ ሰኢድ የቀድሞ የትግራይ ክልል አስልምና ጉዳዬች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ እና በአሁኑ የዞን አስፈፃሚ አባል ሲሆን የሂጃብ ይፈቀድ ጥያቄ በማንሳታቸው አሸባሪ ተብለው 1 አመት ከ 9 ወር አስራት እንዲቀጡ

3.አቶ አህመድ ኡመር የመቀሌ ዞን እስልምና ጉዳዬች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ እና አሁኑ የነጃሺ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ ሲሆኑ የሂጃብ ይፈቀድ ጥያቄ በማንሳታቸው አሸባሪ ተብለው በ 1 አመት ከ 9 ወር እስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል፡፤

የከተማዋ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ፍሰሃ በሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ የሚያደርሱት ግፍ እና በደል ሳያንሳቸው የሒጃብ ጥያቄ ባቀረቡ ሙስሊም አመራር አካላትን በሽብርተኛነት በማስወንጀል በእስራት እንዲቀጡ ማድረጉ አሳፋሪ ተግባር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በሽብርተኛነት የተወነጀሉት ሶስቱ አመራሮችም ለፍርድ ቤቱ ይግባኝ ለመጠቅ መዘጋጀታቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

መቼ ይሆን አንቺ ኢትዬጲያ ሙስሊሞች በሰላም የሚኖሩብሽ????

Source http://www.ethiopianreview.com/forum/

No comments: