Wednesday, July 10, 2013

በኢትዮጵያ የ35 ሀገራት አምባሳደሮች የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን ጠርተው አነጋገሩ

ሐምሌ ፫( ሦስት )ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና :-በአሜሪካን ኤምባሲ በተካሄደው የአምባሳደሮቹ ስብሰባ ላይ በቅርቡ የተመሰረተውንና በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች የተገኙበትን ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ የቻለውን ሰማያዊ ፓርቲን ብቻ ጠርተው አነጋግረዋል።

በተለምዶ ‘‘የኢትዮጵያ ለጋሾች ቡድን’’ የሚል መጠሪያ ያለውና የአሜሪካንን ጨምሮ በርካታ የአውሮፓ ሀገራት አምባሳደሮች በአባልነት የሚገኙበት የለጋሾች ቡድን በተለያዩ ጊዜያት በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱ ከፍተኛ የተቃዋሚ አመራሮች ጋር በሀገሪቱ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የሚያወያዩ ሲሆን  የአምባሳደሮቹ ቡድን ትናንት በአሜሪካ ኤምባሲ ባካሄደው ስብሰባ ላይ ሰማያዊ ፓርቲ
በተለየ ሁኔታ መጋበዙን የፓርቲው  ሊቀመንበር  ገልፀዋል።

ኢንጂነር ይልቃል በፓርቲው የፖለቲካ መርሀ ግብሮች እና በአገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለ1 ሰአት ከ30 ደቂቃ  ያክል ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል

No comments: