Sunday, September 28, 2014

የውጭ ምንዛሬው ዘረፋ በወያኔ ባለስልጣናት እና አጋሮቻቸው ተጧጡፎ ቀጥሏል።

September 28,2014
- ካለምንም ዋስትና በስልክ ትእዛዝ ብቻ ባለስልጣናት በርካታ ዶላሮችን ከባንክ ይወስዳሉ።
- በድንበር አከባቢ የሚገኙ የውጪ ምንዛሬዎች ወያኔዎች ለግል ጥቅማቸው ይከፋፈሉታል።
- የውጪ ምንዛሬው ዘረፋ ከብሄራዊ ባንክ ጀምሮ እስከ ድንበር ከተሞች የባንክ ቅርንጫፎች
ድረስ በሙስና መረብ የተያያዘ የባለስልጣናት ስውር እጆች የተደባለቁበት ነው::
- "የሃገሪቱ ዘለቄታዊ የኢኮኖሚ ጥቅሞች በባዶ ካዝናዎች ተተክተዋል።" የብሄራዊ ባንክ ባለሙያዎች
ከባንኮች አከባቢ የሚወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት በላኪነት ስራ ላይ በብዛት ተሰማርተው የሚገኙት የገዢው መደብ ባለስልጣናት እና ዘመድ አዝማዶቻቸው እንዲሁም በጥቅም ትሥሥር ላይ የተለጠፉ አቆርቋዥ ነጋዴዎች ንግድን ሽፋን በማድረግ ሃገሪቷን በማራቆት ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ::አንዳንድ ባለስልጣናት ደሞ እንደ ቻይና ህንድ እና ቱርክ ከመሳሰሉ ከውጪ አገር ዜጎች ጋር የውስጥ ሽርክና በመፍጠር በጥቅም ትሥሥር ከመሬት ጀምሮ እስከ ማንኛውም ማተሪያሎች ከቀረጥ ነጻ ወደ ሃገር ውስጥ ሲገቡ በኢንቨስትመንት ስም ከሚመሰረተው ድርጅት ጋር የማይገናኙ ውድ እቃዎች ሳይቀሩ ገብተው ሃገሪቷ ማግኘት የሚገባትን እንዳታገኝ ባለስልጣናት ጋሬጣ ሆነዋል::
እንደባንክ ባለሙያዎች መረጃ ከሆነ የወያኔ ባለስልጣናት ቤተሰቦች እና ዘመድ አዝማዶች በላኪነት ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኙ በግልጽ የሚታወቅ ሲሆን ገንዘብን ምንም አይነት ዋስትና ሳያሲዙ በአነስተኛ ወለድ እየወሰዱ የማይከፍሉ እና ሰነድ የሚያስጠፉ እንዲሁም ያለምንም ቀረጥ እና ታክስ ወደ ውጭ ሃገር ምርቶችን በመላክ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ወደ ሃገር ቤት ከማምጣት ይልቅ በተለያዩ የአውሮፓ እና የኢሲያ ሃገራት ባንኮች ይዶሉታል:: የባለስልጣናት ቀጭን የስልክ ትእዛዝ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ዶላሮች ኢሮዎች እና ፓውንዶች ከባንክ ይወሰዳሉ።
ብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬን ለመሸጥ እና ለመግዛት ዋጋ ቢወስንም የግል ባንኮች ግን የውጭ ምንዛሬ መግዣ ዋጋን ወደጎን በመተው ከወያኔ የላኪ ድርጅቶች የውጭ ምንዛሬ በመሸጫ ዋጋ እንዲሸምቱ ሲደረግ በዝምታ ታልፈዋል:: አንዳንድ ላኪዎች ከመንግስት ባንኮች የሚያገኙትን የውጭ ምንዛሬ በተዘዋዋሪ ለግል ባንኮች ሲቸበችቡ እየታየ በዝምታ እየታለፈ ነው::በመተማ በሞያሌ በመልካ ጀብዱ በኩምሩክ በሁመራ በሃርትሼክ ወዘተ በኢትዮጵያ ዙሪያ ገባ የድንበር ከተሞች ላይ በከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የተሰማሩት በአብዛኛው የወያኔ አባላት እና የአከባቢ ባለስልጣናት ካድረዎች ከሚወጡ የሃገር ውስጥ ምርቶች የሚገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለግል ጥቅማቸው እንደሚያውሉት ታውቋል::ይህም ጉዳይ በከፍተኛ ደረጃ ከብሄራዊ ባንክ ጀምሮ እስከ ድንበር ከተሞች የባንክ ቅርንጫፎች ድረስ በሙስና መረብ የተያያዘ የባለስልጣናት ስውር እጆች የተደባለቁበት ነው::
መሰረታዊ ለሆኑ የገቢ እቃዎች የጠፋው የውጭ ምንዛሬ በባለስልጣናት ሲዘረፍ ለሃገሪቱ የፖለቲካ ፍጆታ የመከላከያ እና የደህንነት መዋቅሮች ሲመደብ ማየት በህዝብ ጉሮሮ ላይ ቆሞ ስልጣንን በማስረዘም ሃገርን እየገደሉ መሆኑ በአደባባይ እያየነው ያለነው ሃቅ ነው:;የብሄራዊ ባንክ ከጊዜው የገዢ መደቦች ጋር በማበር የሃገርን ሀለቄታዊ የኢኮኖሚ ጥቅሞች አሳልፎ እየሰጠ ከባንክ አሰራር ውጭ ከፖለቲካው ጋር ግንኙነት ያሌላቸው አስመጪ ነጋዴዎች ማግኘት ያለባቸውን የውጭ ምንዛሬ ባለማግኘታቸው በሰላሳ እና አርባ ፐርሰንት ጭማሪ ምንዛሬዎችን በመግዛት ጋሬጣ የተፈጠረባቸው ሲሆን ይህ ሁሉ የገዢው መደብ አባላት የፈጠሩት የውጭ ምንዛሬ ዘረፋ በሃገሪቷ ላይ የኑሮ ውድነት እንዲሰራፋ አድርጎታል::
ሚኒሊክ ሳልሳዊ

No comments: