Saturday, September 20, 2014

በሰሞኑ የኢህአዴግ ስልጠና ላይ የመምህራኑ ምላሽ

September 20,2014
ከመስከረም 5,2007 አ.ም ጀምሮ መንግስት የአቅም ግንባታ እያለ የጠራው ስልጠና እየተካሄደ ይገኛል:: ገዢው ፓርቲ ስልጣን ከያዘበት 1983 አ.ም ጀምሮ የተለያዩ ስልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን የዘንድሮውም ከበፊቶቹ ምንም የተለየ ሀሳብ ያለተነሳበት እና ድግግሞሽ የበዛበት ብሎም ገዢው ፓርቲ ለኢትዮጵያዊነት እና ለመምህርነት ሙያ ያለውን አይን ያወጣ ጥላቻ ያሳየበት ነበር::

18ስልጠናው እንደተጀመረ መምህራኑን የማሰልጠን ድፍረቱን እና እድሉን ያገኙት አቶ ኤፍሬም ግዛው የተሰኙ የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ናቸው:: አቶ ኤፍሬም በንግግራቸው ወቅት በተደጋጋሚ ሀገሪቷ ከየትኛውም ዘመን በተለየ በኢኮኖሚያዊ እድገቱ እና ሰላም በማረጋገጡ ዘንድ ስኬታማ መሆን እንደቻለች ለማስረዳት ሞክረዋል::

እንደ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እምነት ከሆነ የኢህአዴግ ትልቁ ችግር እራሱን ሞቶ ከተቀበረው የደርግ ስርአት ጋር እያነጻጸረ ህዝቡን ለመሸወድ የሚያደርገው ቀቢጸ ተስፋ ነው:: እድገት ውድድር መሆኑን እናምናለን ሆኖም ይህ ስርአት መወዳደር ካለበት ባላፉት 24 አመታት በእነጋና ቦትስዋና እና ደቡብ አፍሪካ ከታዩት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገቶች ጋር እንጂ ከሞተ ስርአት ጋር ሊሆን አይገባውም:: ሌላው የሰላም ጉዳይ ሰላም አንድ አይነት ትርጓሜ የለውም የጥይት ድምጽ ወይም የቦንብ ፍንዳታ አለመስማት ብቻውን ሰላም አለ ሊያስብል የሚችልበት ምንም አይነት መርህ አይኖርም::


ማሰብ ለቻለ እና ህሊና ላለው ሰው አዛውንቶች እና ህጻናት ጎዳና ወድቀው መመልከት ሰላምን ይነሳል, በሀገራቸው መኖር ስላልቻሉ በስደት አለም የበረሀው ሙቀት የባህር ራት የሆኑት ኢትዮጵያዊያንን ጉዳይ መስማትም ሰላምን ይነሳል, አንድ የሚበላው ያጣ ህጻን ከውሻ ጋር ተሻምቶ ሲመገብ መመልከትም ሰላምን ይነሳል:: በአጠቃላይ በግልጽ የጥይት ድምስ አለመስማት እንደስኬት ልንቆጥረው የሚገባ አይደለም ድምጽ ሳይሰማ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ጊዜ ይቁጠራቸው:: ው ግለሰብ ናቸው::

እኚህ ግለሰብ በተደጋጋሚ ነፍጠኛ, ጠባብ ትምክህተኛ እና ጨለምተኛ በማለት መምህራኑን ብሎም ሰፊውን የሀገራችንን ህዝብ ሲሳደቡ ውለው ከርመዋል ነገር ግን እንደ የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ እምነት ከሆነ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ያለው ብቸኛው ነፍጠኛ, ጠባብ ትምክህተኛ እና ጨለምተኛ ለእኔ ብቻ ተዉት እያለ ያለው ኢህአዴግ ብቻ እና ብቻ ነው::
ከዚህ ስልጠና ለመታዘብ እንደቻልነው ገዢው ፓርቲ ትልቅ የተማሩ ሰዎች እጥረት አለበት ይህንንም እራሱ ኢህአዴግ ሆን ብሎ ያደረገው በመሆኑ እነደ መምህር የዚህችን ሀገር የነገ እጣ ፋንታ ስንመለከት ያስፈራል::


በመጨረሻ እ|ኛ መምህራን ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ ጥሪውን እያስተላለፈ ሌሎች አካላትም ከመምህራኑ ጊዜያዊ ኮሚቴ ጋር ይቆሙ ዘንድ ጥሪውን ያቀርባል::
ድል ለመምህራን
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
የኢትዮጵያ መምህራን ድምፅ ይሰማ ጊዜያዊ ኮሚቴ
መስከረም 10,2007 አ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

No comments: