Tuesday, September 30, 2014

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ጨምሮ በርከት ያሉ የአረና አባላት የነበሩ አንድነትን ተቀላቀሉ

September 29,2014
ፍኖተ ነፃነት
110468445_1563151703908775_2362047875547912265_n. መምህር ታደሰ ቢተውልኝ የዓረና ማ/ኮሚቴ ነበር
2. መምህር ገብሩ ሳሙኤል የዓረና ቁጥጥ ኮሚሸን አባል ነበር
3. ኦቶ ሺሻይ አዘናው የዓረና ማ/ኮሚቴ አባል ነበር
4. አቶ አስገደ ገ/ስላሴ የዓረና ሥራ አስፈፃሚ አባል ነበር
5. ኢንጂነር ዓብደልወሃብ ቡሽራ ማ/ኮሚቴ ነበር
6. ወ/ት ዘቢብ ተሰማ ማ/ኮሚቴ ነበር
7. አቶ ሰለሞን አባይ
8. ይልማ ይኮኖ እና ሌሎች የአረና አባላት ነበሩ በትናንትናው ዕለት አንድነት ፓርቲን በይፋ የተቀላቀሉ ሲሆን፤ የመቀሌ አንድነት ዞን ባዘጋጀው የእንኩዋን ደህና መጣችሁ ፕሮግራም ላይ የአንድነት ብሄራዊ ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ ፀጋይ አላምረው፣ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባላት አቶ አሻግሬ መሸሻ እና አስራት አብርሃም ከአዲስ አበባ በእንግድነት ተገኝተዋል።
በዚህ ወቅት ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከዓረና ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በተቻለ መጠን ሰላማዊና በመደጋገፍ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ ማንም ሰው የፈለገውን ፓርቲ መልቀቅም ሆነ መቀላቀል መብቱ ቢሆንም ከአላስፈላጊ ሰጣ ገባ መጠንቀቅ እንደሚስፈልግ መተማመን ላይ ተደርሰዋል።
ትግሉ መተጋገዝና መተባበር ግድ የሚል በመሆኑ እንደከአሁን በፊቱ በዓረና ካሉት ጓዶች ጋር በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግኑኝነት ይኖረን ዘንድ በጣም አስፈላጊ ነው። ምንም ጥርጥር በሌለው ሁኔታ ነገር ተመልሰን የምንገናኝ፤ አንድ ሆን የምንቀጥል በመሆኑ፤ ከሁለቱም ወገን አብሮ የመስራቱ ጉዳይ መታሰብና መግባባት አስፈላጊ ነው።

No comments: