Sunday, January 5, 2014

የሕወሓት አትኩሮት ስልጣን በማስረዘም ላይ ነው እንጂ በዜጎች ደህንነት ላይ አይደለም ::

January4/2014

ሁላችንም በያለንበት የሕወሓትን ስውር እጆች ልናጋልጥ ይገባል::
ዜጎች በየትኛውን የውጭም ይሁን የአገር ውስጥ በባለስልጣናት የሚደርስባቸው መከራና ግፍ መንግስት የለም ወይ ያሰኛል:: እኛ እየተናገርን ያለነው ስለ ፖለቲከ ተቃዋሚዎች ሳይሆን ስለዜጎች ነው:: ስለፖለቲካ ተቃዋሚዎች ራሳቸው እየደሰኮሩት ነው ዜጎች ግን የመኖር የመስራት የማምለክ መብታቸው ሊከበር ይገባል:: ህግ ሲከበር ስልጣን ይረዝማል:: ህግ ሲከበር ዜጎች ሰላም ያገኛሉ:: ኢኮኖሚው ቢዋዥቅ እንኳን ሰላም ካለ ብልሃቱ አይጠፋም::

ሕወሃት መራሹ ኢህኣዴግ ስልጣኑን ለማስረዘም የሚጠቀምበት ስልት የተበላበት እና ያረጀ መሆኑ እሙን ነው::ዜጎች በሃገራቸው መኖር ካልቻሉ ለመኖር ሲሉ የሚፈጥሩት ፍትጊያ ባለስልጣናቱን ከጨዋታ ውጪ አድርጎ በህዝብ እንዲበሉ ያደርጋቸዋል::ዜጎች በገዛ አገራቸው ዛሬም እየተፈናቀሉ ነው::በአለም ላይ ታይቶ የማይታወቅ የፌዴራሊዝም ከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ በዚህ በሰለጠነ ዘመን ተቀባይነት የሌለው እና ለራስ ጦስ የሚሆን እንደሆነ ወያኔዎች ሊረዱት ይገባል:: እንደጫካ የተለመደው ማፊያዊ መሹለኩለክ የትም የማያደርስ አደጋ የሚያስከትል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል::
ሕወሓት ስሟንም ሙዷንም ትቀይርልን::በቃ ነቅተናል!!! ከሕወሓት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::
ትላንት ዛሬም ነገም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በህገወጥ መንገድ ቢሞት ቢገደል ቢታነቅ ቢታፈን ቢታሰር እና ከነዚህ ነገሮች ጋር በተያያዘ ከሕወሃት ውጭ ማንም ይህን የሚፈጽም የለም :: ይህንን ደሞ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠንቅቆ አውቆታል:: በቃ ነቅተናል!! ከህወሃት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::

በአለማቀፍ ደረጃ ከአሸባሪ ድርጅቶች እኩል ስሟ ሰፍሮ የሚገኘው ሕወሓት በኢትዮጵያ እና በዜጎቿ ላይ በግልጽ እና በድብቅ የተለያዩ ማፊያዊ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው::ሕወሓት በተለያዩ የደህንነት መዋቅሯ አማካኝነት ራሷ ከፈጠረቻቸው ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጀምሮ እስከ ተራ ዜጎች ድረስ በስውር እጆቿ በልታቸዋለች:: በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች በተለያየ ጊዜ ቦምቦችን በማፈንዳት በተቃዋሚዎች ላይ ሰበብ ለመፍጠር ሞክራለች:: በእነዚህ ፍንዳታዎች ያለቁትን ዜጎች አስቧቸው:: ........ኦነግ ሻእቢያ አልሸባብ ቅንጅት አክራሪ ...ምናምን ቢባል ማንም የሚያምን የለም ::አሁንም ያልተነቃ የሚመስላቸው እነዚህ ሰው በላዎች የጫካ ማፊያዊ ድርጊታቸውን እየፈጸሙ ይገኛሉ..በቃ ነቅተናል!!! ከሕወሓት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::

ስለዚህ በቃ ነቅተናል ልንል ይገባል:: ሁላችንም በያለንበት የሕወሓትን ስውር እጆች ልናጋልጥ ይገባል:: ሕወሓትን የምንመክረው ግን አመድ ከመሆንሽ በፊት ስምሽን እና ሙድሽን ቀይሪልን ነው::
በቃ ነቅተናል!!! ከሕወሓት ውጭ ማንም ወንጀለኛ የለም::


ሚኒሊክ ሳልሳዊ


No comments: