Friday, September 26, 2014

ጋዜጠኛ ውብሸት መንግስት ለተሰደዱ ጋዜጠኞች ዋስትና እሰጣለሁ ማለቱ ማታለያ መሆኑን ተናገረ

Photo: ጋዜጠኛ ውብሸት መንግስት ለተሰደዱ ጋዜጠኞች ዋስትና እሰጣለሁ ማለቱ ማታለያ መሆኑን ተናገረ

በሽብር ስም ጥፋተኛ ተብሎ በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሰሞኑን መንግስት ከሀገር የተሰደዱ ጋዜጠኞች ወደሀገራቸው ቢመለሱ እንደማይከሳቸው በማስታወቅ፣ ለዚህም ዋስትና እሰጣለሁ ማለቱ ማታለያ መሆኑን በእስር ቤት ተገኝቶ ጋዜጠኛውን ለጎበኘው የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ተናግሯል፡፡ 

አምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ መከሰሳቸውን ተከትሎ ሀገር ጥለው የተሰደዱ ጋዜጠኞች በሚሰሩበት ተቋማት ላይ የቀረበው ክስ የማይመለከታቸው በመሆኑ ወደሀገራቸው ተመልሰው በሙያቸው ሰርተው መኖር እንደሚችሉ፣ ለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ዋስትና እንደሚሰጥ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እውነቱ ብላታ ማስታወቃቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ‹‹ጋዜጠኞች አልተከሰሱም፤ ወደፊትም አይከሰሱምም›› ሲሉ ገልጸው ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ‹‹የመንግስትን ዋስትና መተማመን አይቻልም፤ የስርዓቱን ባህርይ ጠንቅቀን እናውቀዋለን፤ ዋስትና እሰጣለሁ ማለቱ ማታለያ ነው፡፡ በግሌ የሙያ አጋሮቼ ሀገር ቤት ሆነው የሚወዱትን ሙያ ቢሰሩ ደስ እሰኛለሁ፡፡ ሆኖም ግን ይህን መንግስት ማመን ከባድ ነው›› ብሏል፡፡ 

በተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የሚገኙ ጋዜጠኞችና ጦማርያን ለእስር የተዳረጉት ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር በተያያዘ መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል ያለው ጋዜጠኛ ውብሸት፣ የተሰደዱት ጋዜጠኞች ዋስትና አግኝተናል ብለው ቢመለሱ እንኳ የሙያ አጋሮቻቸው በእስር ለምን ይማቅቃሉ ብለው መጠየቅ እንደሚኖርባቸው አስተያየቱን ገልጹዋል፡፡ 

‹‹ኢህአዴግ የተሰደዱትን ዋስትና እሰጣለሁ ሲል አንድ ቁማር መጫወት ፈልጎ ነው፡፡ ይህም የተሰደዱትን አልከሰስሁም በማለት እናንተ ወንጀል አልሰራችሁም፤ በተለያዩ እስር ቤቶች ያሰርኳቸው ግን ወንጀል ስለፈጸሙ ነው የሚለውን ማስረገጥ በመፈለግ ነው፡፡ እኛ ወንጀል ሰርተን አይደለም የታሰርነው፡፡ ርዕዮት ዓለሙ ህክምና እንኳ እያገኘች አይደለም፡፡ ታዲያ መንግስት ዋስትና እሰጣለሁ ሲል ይህን ሁሉ ግፍ ይዘነጉታል ብሎ ነው እንዴ?›› ሲል ጠይቋል፡፡ 

እንዲሁ እንደ ቀላል ነገር ለተሰደዱ ጋዜጠኞች ዋስትና እሰጣለሁ ማለት ሌላ በተግባር እየተፈጸመ ያለውን ግፍ አይደብቅም ያለው ጋዜጠኛ ውብሸት፣ መንግስት ተራ ጨዋታውን ትቶ ወደልቦናው እንዲመለስ ጠይቋል፡፡ ‹‹ስርዓቱን 23 ዓመት አውቀነዋል፡፡ መታለል አይኖርብንም›› ብሏል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከቃሊቲ፡፡September 26,2014
በሽብር ስም ጥፋተኛ ተብሎ በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ሰሞኑን መንግስት ከሀገር የተሰደዱ ጋዜጠኞች ወደሀገራቸው ቢመለሱ እንደማይከሳቸው በማስታወቅ፣ ለዚህም ዋስትና እሰጣለሁ ማለቱ ማታለያ መሆኑን በእስር ቤት ተገኝቶ ጋዜጠኛውን ለጎበኘው የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጠኛ ተናግሯል፡

አምስት መጽሔቶች እና አንድ ጋዜጣ መከሰሳቸውን ተከትሎ ሀገር ጥለው የተሰደዱ ጋዜጠኞች በሚሰሩበት ተቋማት ላይ የቀረበው ክስ የማይመለከታቸው በመሆኑ ወደሀገራቸው ተመልሰው በሙያቸው ሰርተው መኖር እንደሚችሉ፣ ለዚህም የኢትዮጵያ መንግስት ዋስትና እንደሚሰጥ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እውነቱ ብላታ ማስታወቃቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ‹‹ጋዜጠኞች አልተከሰሱም፤ ወደፊትም አይከሰሱምም›› ሲሉ ገልጸው ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ‹‹የመንግስትን ዋስትና መተማመን አይቻልም፤ የስርዓቱን ባህርይ ጠንቅቀን እናውቀዋለን፤ ዋስትና እሰጣለሁ ማለቱ ማታለያ ነው፡፡ በግሌ የሙያ አጋሮቼ ሀገር ቤት ሆነው የሚወዱትን ሙያ ቢሰሩ ደስ እሰኛለሁ፡፡ ሆኖም ግን ይህን መንግስት ማመን ከባድ ነው›› ብሏል፡፡

በተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የሚገኙ ጋዜጠኞችና ጦማርያን ለእስር የተዳረጉት ሀሳብን በነጻነት ከመግለጽ መብት ጋር በተያያዘ መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል ያለው ጋዜጠኛ ውብሸት፣ የተሰደዱት ጋዜጠኞች ዋስትና አግኝተናል ብለው ቢመለሱ እንኳ የሙያ አጋሮቻቸው በእስር ለምን ይማቅቃሉ ብለው መጠየቅ እንደሚኖርባቸው አስተያየቱን ገልጹዋል፡፡

‹‹ኢህአዴግ የተሰደዱትን ዋስትና እሰጣለሁ ሲል አንድ ቁማር መጫወት ፈልጎ ነው፡፡ ይህም የተሰደዱትን አልከሰስሁም በማለት እናንተ ወንጀል አልሰራችሁም፤ በተለያዩ እስር ቤቶች ያሰርኳቸው ግን ወንጀል ስለፈጸሙ ነው የሚለውን ማስረገጥ በመፈለግ ነው፡፡ እኛ ወንጀል ሰርተን አይደለም የታሰርነው፡፡ ርዕዮት ዓለሙ ህክምና እንኳ እያገኘች አይደለም፡፡ ታዲያ መንግስት ዋስትና እሰጣለሁ ሲል ይህን ሁሉ ግፍ ይዘነጉታል ብሎ ነው እንዴ?›› ሲል ጠይቋል፡፡

እንዲሁ እንደ ቀላል ነገር ለተሰደዱ ጋዜጠኞች ዋስትና እሰጣለሁ ማለት ሌላ በተግባር እየተፈጸመ ያለውን ግፍ አይደብቅም ያለው ጋዜጠኛ ውብሸት፣ መንግስት ተራ ጨዋታውን ትቶ ወደልቦናው እንዲመለስ ጠይቋል፡፡ ‹‹ስርዓቱን 23 ዓመት አውቀነዋል፡፡ መታለል አይኖርብንም›› ብሏል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ ከቃሊቲ፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ

No comments: