Wednesday, September 3, 2014

የወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ላይ

September 2, 2014 
ወያኔ በለስ ቀንቶት የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ከተቆጣጠረ ጊዜ አንስቶ ከጫካ አዝሎት የመጣውን አብዮታዊ ዲሞክራሲና የአንድን ጎሳ ሁለንተናዊ የበላይነት የማስፈን ዓላማ ለማሳካት ባለው አቅም ሁሉ ሲሰራ ኖሯል።
ዘረኛው ወያኔ የትግሬ ጎሳን በመሣሪያነት ለመጠቀም ሲል ጎሳውን በሞራል፤ በኢኮኖሚ፤ በጤናና በትምሕርት ከሌላው የላቀ ደረጃ ላይ ማድረስ በሚለው መርሁ መሠረት የሃገሪቱን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ወታደራዊና የደህንነቱን ዘርፍ ሁሉ በትግሬዎች ቁጥጥር ሥር እንዲውል በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓትን ዘርግቶ ይገኛል።
ይህ ብቻም አይደለም የወያኔ አገዛዝ መሣሪያ ይሆነኛል ከሚለው ከትግሬ ህዝብና ከትግራይ ክልል በዘለለ ኢትዮጵያ ስለምትባል ሃገርም ሆነ ኢትዮጵያዊ ስለሚባል ሕዝብ ዘለቄታዊ ጥቅምና ጉዳት ባለማሰብ የሥልጣን ዘመኑን ዘለዓለማዊ ለማድረግ ያስችለኛል በሚለው ጊዚያዊ ጥቅም ላይ ብቻ በማተኮር የሃገሪቱን መሬትና ዳር ድንበር ሳይቀር ለባዕዳን አሳልፎ በመስጠት የጊዚያዊ ፖለቲካና የንዋይ ጥቅም ማጋበሻው እያደረገው ይገኛል።
ሌላው ቀርቶ የሃይማኖት ተቋሙ እንኳ ከትግሬ ጎሳ የበላይነትና ቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን ወያኔ ገና ሥልጣን ላይ ከመውጣቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ የነበሩትን አቡነ መርቆሪዎስን ከመንበራቸው አሽቀንጥሮ በመወርወር በብዙ ሺህ ኪሎሜትር ተጉዞ ባህር ማዶ ድረስ በመሻገር በሃይማኖት ህንጸጽ ተወግዘው በመሰደድ ከኦርቶዶክስ እምነት ይልቅ ወደ ካቶሊኩ እምነት አዘንብለው የነበሩትን አባ ጳውሎስን ትግሬ በመሆናቸው ብቻ መርጦ ፓትርያርክ አድርጎ ሊሾማቸው ችሏል።
ከዛም በኋላ ኢትዮጵያን በምታክል ታላቅ ሃገር የሥልጣን እርከን ላይ ለ20 ዓመታት ያህል ቆይቶ እንኳ ከዚህ ከጠባብ የጎጥ አስተሳሰቡ መላቀቅ ባለመቻሉ ትግሬ በመሆናቸው መርጦ ፓትሪያርክ ያደረጋቸውን አቡነ ጳውሎስ ሞት ሲወስዳቸው አሁንም ከ85 ሚሊዮን በላይ የሆነውን የአማራውን፤ የኦሮሞው፤ የደቡቡን ሕዝብ፤ ጋምቤላውን፤ የቤንሻንጉሉን ሕዝብ ሳይሆን አንድ ትግሬ ፍለጋ ወጪ ሃገር ድረስ በመሄድ እንደገና አቡነ ማትያስ የተባሉ ሌላ ትግሬ ከእየሩሳሌም በማምጣት ፓትሪያርክ አድርጎ ሾሟቸው ይገኛል።
ይህና ይህንን የመሳሰሉ የኢትዮጵያዊነት ስጋና ደም አለው የሚባል ሰው ይፈጽመዋል የማይባል አይን ያወጣ ይሉኝታ ቢስነትና ጋጠ ወጥ የወያኔ የዘረኝነት ተግባር፤ ዛሬ ሥርዓቱን ብቻ ሳይሆን ጎሳውንም ጭምር ምንም ዓይነት ሃፍረትና ይሉኝታ የሚባል ያልፈጠረባቸው ናቸው እያስባለ ይገኛል።
ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ደግሞ የወያኔ አገዛዝ እጁን በማስረዘም በዲያስፖራ የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ እንኳ ከዘረኛው አገዛዝ ነጻ ሆኖ በሰላምና በነጻነት እንዳይኖር ስደተኛውን ኢትዮጵያዊ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በጎሳ አፓርታይድ ሥርዓቱ ቁጥጥር ሥር ለማዋል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል።
ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ በሃገሩ የተነፈገውን ነጻነት፤ ፍትህና እኩልነት በዲያስፖራ ኑሮው የተጎናጸፈ ቢሆንም፤ ነገር ግን ሃገሬንና ሕዝቤን አልረሳም በማለት ሃገሩ ውስጥ በወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት ሥር ለሚገኘው ወገኑ በመቆርቆር፤ ሥለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ከመጮህና ድምጹን ከማሰማት ታቅቦ አያውቅም።
ይህንን ድምፁ ለታፈነው ሕዝብ ድምጽ የሆነውን ኢትዮጵያዊ የዲያስፖራ ኃይል ወያኔ በጠላትነት የሚያየው በመሆኑ ይህንን ኃይል ለማዳከምና ለመከፋፈል አያሌ ጥረቶችን ሲያደርግ ኖሯል።
ከእነዚህም ጥረቶቹ ውስጥ ተጠቃሽ የሚሆነው ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ እንኳንስ እትብቱ የተቀበረበት ሃገሩ በአሁኑ ዘመን በማንኛውም ነፃነትና ዲሞክራሲ በሰፈነባቸው የባዕድ ሃገራት ሁሉ እንደ ልብ የመግባትና የመውጣት፤ ከዛም ባሻገር ቤት የመስራትም ሆነ ንብረት ማፍራት ሰብዓዊ መብቱ ሆኖ ሳለ፤ የወያኔ አገዛዝ ግን ይህንን መብት ለዜጎች ፈቃጅና በችሮታ ሰጪ መስሎ በመቅረብ፤ የተለያዩ የመሬት ምሪት፤ የቤተ መሥራትና የኢንቨስትመንት በሮች ለዲያስፖራው ተከፍቷል የሚል የማታለያ ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት ስጦታ ሰጪና ነፋጊ ሆኖ እየቀረበ ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ የውጪ ምንዛሪ ምንጭ በማድረግና የሰዎችን ዳታ ማግኛ ዘዴ አድርጎ ሲጠቀምበት ኖሯል።
ከዛም በመቀጠል ንብረት ያፈራና ቤት የሰራ የዲያስፖራ ኗሪን ዳታ በመጠቀም የሥርዓቱ ደጋፊ እንዲሆኑ ለመቀስቀስና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ተጠቅሞበታል።
አሁን፤ አሁን ደግሞ ንብረት ያለህና እንደልብህ ኢትዮጵያ የምትገባና የምትወጣ ሁሉ በወያኔ ላይ ተቃውሞ ብታነሳ በንብረትህ ላይ ወይም የፈቀድኩልክን የመግባትና የመውጣት መብት አግደዋለው ወይም አሸባሪ ብዬ ዘብጥያ አወርድሃለው እያለ በተቀጣሪዎቹ አማካኝነት ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ እያስፈራራ ይገኛል።
በእርግጥ የወያኔ አገዛዝ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚያደርገው ሁሉ ዲያስፖራውንም ለመቆጣጠር የሚያስችል የሚዲያም ሆን የሶሻል ሚድያ ቁጥጥር፤ እንዲሁም የፌደራል ፖሊስ፤ የመከላከያና የደህንነት ኃይል የሌለው ሲሆን ሆኖም ግን በተለያየ ዘዴ ዲያስፖራውን በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተቋማትን ለማደራጀት ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ከእነዚህ የወያኔ አገዛዝ በውጪ ሃገራት ካተኮረባቸው ተቋማት ውስጥም በውጪ ሃገራት የተቋቋሙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት በአንደኛ ደረጃ ተጠቃሽ ናቸው።
እነዚህን ከፍተኛ ተከታይ ያላቸውን በውጪ የተመሠረቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናትን በቁጥጥር ሥር በማዋል ወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓቱን በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ውስጥ ለማስፈን ለሚያደርገው ጥረት አንዱ ምሳሌ የሚሆነውም፤ መንበሩ ለንደን ላይ አድርጎ እንዲቋቋም የተደረገው የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ነው።
የዚህ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በማድረግ የወያኔ አገዛዝ ሹሞ የላካቸው አቡነ እንጦስ የሚባሉ ትግሬ ሲሆኑ የሃገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ የተደረገውም መጋቢ አዕላፍ ተወልደ ገብሩ የተባለውም እንዲሁ ትግሬ ነው።
ይህ ብቻም አይደለም ሃገረ ስብከት በተባለው ሰበካ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙት አብዛኞቹ በጎሳ የተሰባሰቡ ትግሬዎች ናቸው።
ሌላው የደቡብ አውሮፓ ሃገረ ስብከት ተብሎ ጣሊያን ሮም ላይ የተቋቋመውን በሊቀ ጳጳስነት እንዲመሩ የተደረጉት ደግሞ አቡነ ሙሴ የተባሉ እንዲሁ ትግሬ ናቸው።
እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2005 ምርጫ 97ን ተከትሎ ወያኔ ሕዝብን በግፍ በጨፈጨፈበት ወቅት የለንደኗ ቤተ ክርስቲያን በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያኖች ፀሎት ለማድረግ ስትዘጋጅ፤ የወያኔ አገዛዝ ለሞቱት ሰዎች አብያተ ክርስቲያናት ጸሎት እንዳያደርሱ በአቡነ ጳውሎስ አማካኝነት መመሪያ አስተላልፎ ስለነበር የወያኔ ወኪሎችና ደጋፊዎች የሆኑ ካህናት ቤተ ክርስቲያኗ ለተገደሉት ሰዎች ጸሎት ማድረግ የለባትም በማለታቸው ይህ በሕዝቡ ውስጥ እንደተሰማ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣን አስነስቶ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት አቡነ ጳውሎስን በማውገዝ ከአሁን በኋላ ቤተ ክርስቲያኗ የአቡነ ጳውሎስ ስም ቅዱስ ብላ በጸሎት ላይ እንዳትጠራ ውሳኔ በማስተላለፍ በግፍ ለተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሙሉ ጸሎት እንዲካሄድ አደረጉ።
በዚህ ወቅት ለቤተ ክርስቲያኗም ሆነ ለሃገሩ እንግዳ የነበሩት አቡነ ሙሴ በአጭር ጊዜ ቆይታቸው ሕዝበ ክርስቲያኑ ተክለ ሰውነታቸውንና ጭምተኝነታቸውን በማየት እግዚአብሔር ያመጣልን ቅዱስ ሰው በማለት አክብሮ የተቀበላቸው ቢሆንም እሳቸው ግን የወያኔ መመሪያ ሲጣስና ወያኔ ሲወገዝ ወያኔነታቸው ገንፍሎ ወጥቶ በመናደድ “ደንቆሮ ሁሉ!!” በማለት ሕዝብን በመሳደብ ሕዝብንና ቤተ ክርስቲያንን ረግጠው ሊወጡ ችለዋል።
በዚህ ምክንያት ከለንደኗ ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከተለዩ በኋላ የመንደር ልጆቻቸው የሆኑትን ትግሬዎች አሰባስበው ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን መሠረቱ።
በመጀመሪያ የጎሳው አባላት ብቻ የተከተሏቸው በመሆኑ ቅዳሴው በትግርኛ ቋንቋ እንዲሆን ጭምር የተጠየቀ ሲሆን ቀጥሎ ግን የዋሁና የጎሳ ፓለቲካው የማይገባው ምስኪኑ ሕዝበ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን እስከተከፈተ ድረስ ወደ ቀረበኝ እሄዳለሁ በሚል የዋህነት ስሜት የጎሳ ፖለቲከኞች ወደሚመሩት ቤተ ክርስቲያን በመሄድ መገልገል በመጀመሩ በብዛት የሚመጣውን ሕዝብ ገንዘብና ጉልበት ላለማጣት ሲሉ የቅዳሴው ቋንቋ ሳይለወጥ እንዲቀጥል ሊያደርጉት ችለዋል።
አቡነ መሴ የለንደኗን ማርያም ቤተ ክርስቲያን በጎሳ ከከፈሉ በኋላ ከለንደን ወደ ኢትዮጵያ በመሔድ የአቡነ ጳውሎስ ታማኝ ባለሟል ሆነው በመቆየት ከዛ የወያኔ አገዛዝ በውጪ ሃገራት የሚያደርገውን የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት ለማስፋፋት ወደ ጣልያን ሃገር በመላክ የደቡብ አውሮፓን ሃገረ ስብከት እንዲያቋቁሙ ተደርገዋል።
በጣሊያን ሃገር ካሉት አብያተ ክርስቲያናት የሚሰበሰበው ገቢ ዝቅተኛ በመሆኑና የወያኔን ዓላማ ለማሳካት የሚችል ሆኖ ባለመገኘቱ አቡነ ሙሴ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ወደ ሚገኝበትና ከፍተኛ ገቢ ሊሰበሰብ ወደሚችልበት ወደ ጀርመን ሃገር በመሄድ መንበራቸውን በጀርመን ሃገር እንዲያደርጉ ተደረገ።
የወያኔ አገዛዝ አቡነ ሙሴን ፍራንክ ፈርት ወደሚገኘው የማሪያም ቤተ ክርስቲያን ሲልክ አስተዳዳሪ ከሆኑት አባ ሲራክ ከሚባሉ ሌላ ትግሬ ጋር በመመሳጠር ስለነበር ጀርመን ሃገር ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን በመምራት የሚታወቁትን እንደ እነ ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርሀዊ ተበጀም ሆኑ አጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ ምንም ነገር ሳይነገረው አቡነ ሙሴ ታቦት በመያዝ ጀርመን የደረሱት በድንገት በታቦት ንግሥ ቀን ነበር።
በዚህም ዕለት አቡነ ሙሴ ከአሁን ጀምሮ መንበሬ በጀርመን ሃገር ፍራንክፈርት በምትገኘው ማርያም ቤተ ክርስቲያን ነው ብለው በማወጃቸው በሕዝቡ ውስጥ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ አስነስቶ ጳጳሱንም ሆነ ሊያቋቁሙት ያሰቡትን ሃገረ ስብከት ሕዝቡ ባለመቀበሉ ጉዳዩ ሲያከራክር ቆይቶ በመጨረሻ በግብጾች ገዳም ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገው ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው መሄዳቸው ታውቋል።
ይህ ከሆነ በኋላ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ውስጥ ውስጡን ተንኮል ሲሸረብ ቆይቶ ሊቀ ካህናት ዶ/ር መርሃዊ ተበጀን ጭምር በማለሳለስ አቡነ ሙሴ ተመልሰው ወደ ጀርመን በመምጣት እንደለመዱት ሕዝቡን በጎሳ በመከፋፈል የወያኔን የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት ቅርንጫፍ ሃገረ ስብከት መልሰው ለማቋቋም በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
በጀርመን የሚገኝ ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሁሉ ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊዘረጋ የታሰበው የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት ሰለባ ከመሆኑ በፊት ነቅቶ መጠበቅና መከላከል ይገባዋል።
በወያኔ የጎሳ ፖለቲካ መዋቅር መሠረት እንዲመሠረቱ የተደረጉት እነዚህ ሁለቱ ሀገረ ስብከቶች ዓላማ ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ በውጪ ሃገራት የመሠረታቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናት በስደተኛው ሲኖዶስ ሥር በመሆንና ገለልተኛ ነን በማለት ነጻ ሆነው ዘረኛውን የወያኔ አገዛዝ የሚጻረር ድምጽ ከማሰማት እንዳታቀቡ በማድረግ ተግባራቸው ሁሉ የአገዛዙን ሥራ በማወደስና ድጋፍ በመስጠት ብቻ ተወስኖ ለሃገረ ስብከትና ቤተ ክህነት ፈሰስ አድርጉ በማለት የውጪ ምንዛሪ መሰብሰቢያ እንዲሆኑ ታስቦ ነው።
በእንግሊዝ ሃገር የምትገኘው የርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በመጀመሪያ በአቡነ ሙሴ ተጠንስሶ በአቡነ እንጦስ ለንደን ላይ የተመሠረተውን የወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ቅጥያ ሃገረ ስብከት ሳትቀበል ከአገዛዙ የቀጥታም ሆነ የተዘዋዋሪ ተጽዕኖ ነጻ በመሆን በሃብትና በአደረጃጀት ራሷን ችላ ትተዳደር ነበር።
ሆኖም ግን ሕዝቡ ሃብትና ጉልበቱን አስተባብሮ ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ከገዛ በኋላ አምኖ መርጦ የሾመው አባ ግርማ ከበደ (የለንደኑ ዲያቢሎስ) የተባለው መነኩሴና ግብረ አበሮቹ የቤተ ክርስቲያኑን አባላት በመክዳት ለወያኔ ኤምባሲ ሄደው እጅ በመስጠታቸው ምክንያት በአሁኑ ወቅት ይህ ወያኔ ከጎሳው አባላት መርጦ ያቋቋመው ሃገረ ስብከት ከነ አባ ግርማ ጋር ግንባር በመፍጠር ቤተ ክርስቲያኗን ከአባላቱ ነጥቆ ለመቆጣጠር በማድረግ ላይ ያለውን ጥረት የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ተቋቁመው በመታገል ከፍተኛ ትንቅንቅ ላይ ይገኛሉ።
አባ ግርማ ከበደ (የለንደኑ ዳቢሎስ)
ሌላው በአሁኑ ወቅት ይፋ እየሆነ የመጣው ወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓቱን በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ላይ ለማስፈን በመሣሪያነት ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ውስጥ በገንዘብና በጥቅማ ጥቅም ቀጥሮ የሚያሰማራቸው የስድብና የፕሮፓጋንዳ ወኪሎቹ ጉዳይ ሲሆን እነዚህ ቅጥረኛ ባንዳዎች የወያኔ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ሰራተኛ በመሆን አሉ የሚባሉ ኢትዮጵያዊ ግለሰቦችን ድርጅቶችንና ልዩ ልዩ የዲያስፖራው ተቋማት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ በማካሄድ የሃሰት ውንጀላዎችን በማሰራጨት ዲያስፖራውን በታትነው በወያኔ ጫማ ስር ለማስገባት ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ወያኔ ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ለመቆጣጠር በሃይማኖት ተቋማት ውስጥ እንዴት ሰርጎ እንደሚገባ ከሚያስገነዝቡት ውስጥ አሁንም በለንደኗ ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸመው ለሌሎች እንደ ትምሕርት ሊሆን የሚችል ጉዳይ ቀጥሎ የተመለከተው ነው።
የቤተ ከርስቲያኗ አባላት ቤተ ክርስቲያናቸውን ከወያኔ ዘረኛ አገዛዝ የሃገረ ስብከት ሹመኞች ጠብቀው ለማኖር ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ወገንና ደጋፊ በመምሰል ዲያቆን ነኝ የሚል አንድ ግለሰብ ወደ ቤተ ክርስቲያኗ ይጠጋል። በመቀጠልም ይኸው ሰው ወደ ፊት ተጠግቶ ካህናቱ ከሚቆሙበት ተርታ ካህን መስሎ በመቆም ይቀላቀላል። ሆኖም ግን ይህ ሰው ከካህናቱ ተርታ ከመቆሙ በስተቀር አንድም ቀን የድቁናም ሆነ የክህነት ተግባር ሲያከናውን ስለማይታይ ጉዳዩ ሰውን ሁሉ የሚያነጋግር ጉዳይ ሆኖ ቢከርምም ጉዳዩን ትኩረት ሰጥቶ ያጣራ ሳይኖር እንዲሁ ይኖራል።
ከጊዜ በኋላም ይህ ሰው የኮሚቴዎች ስብሰባ ሲኖር የካህናቱ ጉባኤ አባል ነው እየተባለ በጉባኤዎች ላይ መገኘት ይጀምራል።
በመጨረሻ ግን የዚህን ሰው ትክክለኛ ማንነት ማንም ሰው ሳያጣራና ሳይመረምር ሰውዬው ራሱን በራሱ ሊያጋልጥ ቻለ።
ይህ ሰው ስሙ መንገሻ መልኬ የሚባል ሲሆን ግለሰቡ ኢትዮጵያ ውስጥ በቤተ ክህነትና በአብያተ ክርስቲያናት አካባቢ በጸሐፊ ረዳትነትና በተላላኪነት ተጠግቶ ከመስራቱ በስተቀር ለድንቁና ቀርቶ ለጽዋኅኆህነት (የቤተ ክርስቲያን በር ከፋች) የሚያበቃ ሃይማኖታዊ እውቀት የሌለውና ከፍተኛ የባህሪ ችግር ያለበት ሰው መሆኑ ሊረጋገጥ ተችሏል።
የመንገሻ መልኬ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መጠጋት ዓላማም ወገን መስሎ በመቅረብ፤ ወደ ካህናቱና ወደ ቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደር በመጠጋት የአቡነ እንጦስ (የወያኔ ሃገረ ስብከት) ስውር ሰላይ (Under Cover Agent) በመሆን አስፈላጊውን የስለላ ተግባር ለማከናወን ነበር።
በዚህም መሠረት በሰላሙ ጊዜ የቤተ ክርስቲያኗን መረጃዎች ሁሉ ቤተ ክርስቲያኗን በቁጥጥራቸው ሥር ለማዋል ቀን ከሌሊት ለሚጥሩት ለአቡነ እንጦስ በስውር ሲያቀብል ከኖረ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአስተዳዳሪውና በአባላቱ መካከል ግጭት ሲነሳ ደግሞ ተልኮውን ለማሳካት ግንባር ቀደም የፀቡ አባባሽና አራጋቢ በመሆን የስውር ስራውን በይፋ ወጥቶ ማካሄድ ቀጠለ።
በዚህ ዓይነት የተሸፈነበትን ጭንብል ካወለቀ በኋላ ከለንደኑ ዲያብሎስ መነኩሴ ጋር በመሆን ቤተ ክርስቲያኗን ከአባላቷ ነጥቆ የወያኔው አገዛዝ ሹመኞች እንዲቆጣጠሯት ለማድረግ በተደረገው ጥረት ውስጥ ግንባር ቀደም ተዋናኝ ሆኖ ቀጠለ።
ቤተ ክርስቲያኗን ከአባላቷ ነጥቀው በቁጥጥራቸው ሥር ያስገቡ የመሰላቸው አቡነ እንጦስም ስውር ሰላያቸው የነበረው መንገሻ መልኬን ውለታ ለመክፈልና በሥራው እንዲገፋበት ለማበረታታት “መጋቢ ጥበብ” የሚል ማዕረግ በመስጠት በአሁኑ ወቅት የሃገረ ስብከቱ ዋና ጸሐፊ አድርገው ሾመውት ይገኛሉ ።
(መንገሻ መልኬን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያውቁት የቅርብ ጓደኞቹ፤ “በቀን ጎንደሬ በማታ ደግሞ ትግሬ” ነኝ በማለት በምላሱና በአድር ባይነቱ የሚኖር ሰው መሆኑን ማስረጃ ጠቅሰው ይገልጻሉ።)
ይህንን ባህሪ በመላበስ ነው ወደ ለንደኗ የስደተኞች ቤተ ክርስቲያን በመጠጋት የቅጥረኛ ባንዳነት ሥራ ሲሰራ የቆየው።መንገሻ መልኬ በዚህ ስራው የተሰጠውን ሹመት ሰው አላውቅለት ያለ ስለመሰለውም ይመስላል በቅርቡ በተሰራጨ የYouTube ቪድዮ ላይ የሃገረ ስብከቱ ጸሐፊ ነኝ በማለት ራሱን በራሱ ሲያስተዋውቅ ተስተዉሏል።
በቀን ጎንደሬ፤ በማታ ደግሞ ትግሬ ነኝ ባይ መንገሻ መልኬ።
የቪዲዮው አቀነባባሪና አቅራቢ ደግሞ ሌላው የወያኔ የስድብና የፕሮፓጋንዳ ቅጥረኛ ባንዳ የሆነው እንዳለ ወንዳፍራሽ (Endex) ሲሆን “ግመል ሰርቆ አጎንብሶ” እንደሚባለው የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ መሆኑን ሕዝብ እያወቀው፤ እሱ ግን ራሱን የደበቀ መስሎት ራሱን በኮፊያ፤ ፊቱን ደግሞ በጥቁር መነጽር በመሸፈን ሁሌ ሲቸገር ይታያል።
ይህ ብቻም አይደለም ይኸው የወያኔ ቅጥረኛ በሚያሰራጨው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ቪዲዮ ላይ ሁሉ ምስሉን ደብቆ በድምጹ ብቻ የሚናገር ሲሆን በዚህም ቪዲዮ ላይ በድምጹ ብቻ ጥያቄ የሚያቀርበው ይኸው እንዳለ ወንዳፍራሽ የተባለው የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ ነው።
እንዳለ ወንዳፍራሽ (Endex)
ከእንዳለና ከመንገሻ በተጨማሪ ቄስ አባተ ጎበና እና መሪጌታ ሄኖክ የሚባሉ ሁለት ካህናት በቪዲዮው ቃለ ምልልስ ላይ የተሳተፉ ሲሆን እነዚህ ሁለት ካህናት ለወያኔው የጎሳ አባርታይድ አገዛዝ ሹመኛ ለአቡነ እንጦስና ለነ ተወልደ ገብሩ በማደር የቤተ ክርስቲያኑን አባላት አባረው ቤተ ክርስቲያኗን ለሀገረ ስብከት ተብዬው በማስረከብ ሹመት ሽልማትንና ጥቅማ ጥቅምን ለመቃረም የክህደት ተግባር በመፈጸም ላይ የሚገኙ ናቸው።
“…. ያለበት ዝላይ አይችለም” እንደሚባለው በንግግራቸው ጣልቃ “ወያኔ አይደለንም፤ ወያኔ ማለት አይደለም” እያሉ ሲወተውቱ ይደመጣሉ፤ (ይህቺ የተበላች እቁብ መሆኗን አልተረዱምና ሕዝብን ያታለሉ መስሏቸው ነው)
በርግጥ በዛው ወያኔ አይደለንም ባሉበት አፋቸው ደግሞ ጥቂት ቆይተው ዓለም ያወቀውንና ፀሐይ የሞቀውን የወያኔ አገዛዝ በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ የመግባትን ከፍተኛ ችግር በመካድ ማስተባበያ ይሰጣሉ።
በተለይ ቄስ አባተ ጎበና የተባለው ካህን በቀኝ እጁ የያዘው የክርስቶስ መስቀል ሳያስፈራው ሰውንም ሆነ ፈጣሪን በመዳፈር “በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም፤ ገብቶም አያውቅም” በማለት በድፍረት በመዋሸት ከወያኔ ባለሥልጣናት የላቀ የሃሰት ማስተባበያ ያቀርባል።
ሙሉውን ቪድዮ ለማየት ቀጥሎ ያለውን ሊንክ ይጫኑ።
(ሙሉ ቪድዮውን ለማየት ረጅም ሰዓታትን ስለሚወስድ በተለይ መንገሻ መልኬ የተባለው የባንዳነት ሹመቱን የሚያረጋግጥበትን በ52፡ 38 ደቂቃ ላይ፤ የቄስ አባተን የወያኔ መንግሥት ጠበቃነት ደግሞ በ 1:4.16 ላይ መመልከት ይችላሉ።)
እንዳለ ወንዳፍራሽ ወደተባለው የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ ስንመለስም፤ የሱ የቅጥረኝነት ተግባር በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በፖለቲካውም ዙሪያ ዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ለሃገሩና ለወገኑ ድጋፍ ሰጪ እንዳይሆን ለማዳከም ወያኔ በሚሰጠው መመሪያና ትዕዛዝ መሠረት ግለሰቦችንና ድርጅቶችን የመሳደብና የማዋረድ ተግባርን የሙሉ ሰዓት ሥራው አድርጎት ይገኛል።
ይህ ግለሰብ ወያኔ በኤምባሲ ሽፋንና በስደተኝነት ስም በውጪ ሃገራት ካሰማራቸው ስላዮች ጋር በመመተባበር በቅርብ ጊዚ እንኳ በYou tube፣ viber text እና በሌሎች የSocial media ላይ ካሰራጫቸው የፕሮፓጋንዳ መልዕክቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙባቸዋል።
በተለይ እድሜውን በሙሉ ለሃገሩ ኢትዮጵያና ለሕዝቧ ሲታገል የኖረው አንዳርጋቸው ጽጌ በዘረኞች ተይዞ ወደ ሰቆቃ የእስር ቦታቸው ሲወሰድ ያዘነው፤ የተቆጨውና የተቆጣው የግንቦት 7 አባል ወይም ደጋፊ ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ስደተኛ ኢትዮጵያዊ ቢሆንም በአንጻሩ ግን የአንዳርጋቸው በወያኔ እጅ መግባት ዘረኛ ወያኔዎችንና ደጋፊዎቻቸውን እንዳስደሰተ ደግሞ የማይታበል ነው።
ቀጥሎም ወያኔ አንዳርጋቸውን በኢ.ቲ.ቪ. ላይ ምስሉን አቅርቦ መቶ ቦታ የተከታተፈ ቪዲዮ አሳየ። የቪዲዮው ዓላማም ጀግናችን የምትሉት አንዳርጋቸው ጀግና ሳይሆን ፈሪና የማይረባ ሰው ነው ብሎ በማዋረድ ሰውንም ሆነ ትግሉን ተስፋ ለማስቆረጥ የሚቻለውን ሁሉ አደረገ።
ይህ የወያኔ ድርጊት የሚጠበቅ የወራዳ ባህሪው መግለጫ ሲሆን ነገር ግን ሌላው የሚያስገርመው እንዳለ ወንዳፍራሽን የመሰለ ቅጥረኛ ባንዳ ወያኔን በማስደሰት የሚጥልለትን ፍርፋሪ ለመልቀም ሲል የወያኔን ፕሮፓጋንዳ መሠረት በማድረግ አንዳርጋቸውን ያዋርዳል ብሎ የሚያስበውን የፕሮፓጋንዳ ጽሑፍ እያዘጋጀ በfree Viber text ሌት ተቀን በመልቀቅ ድያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ለማደናቆር መሞከሩ ነው።
እንዳለ ወንዳፍራሽ (Endex) የአንዳርጋቸውን መያዝ አስመልክቶ ከሚያስተላልፈው የወያኔ ፕሮፓጋንዳ ውስጥ አንዳርጋቸውን በፈሪነት በመፈረጅ ሌሎችም ስደተኞች ግንቦት 7 እና OLF እየተባሉ በወያኔ እየተለቀሙ እንደሚጋዙ የሚያስፈራራበት የፕሮፓጋንዳ የViber text ውስጥ አንዱ ቀጥሎ የተመለከተው ነበር።
“Andargachew vs Gen Fanta Belay!! Coward vs brave heart! General Fanta Belay was a graduate from sandhurst military academy the best Britain can offer, him n his top rated generals wanted to get rid off the derg junta, unfortunately the coup de tat was compromised and they caught him whilst escaping, they put him in TV to humiliate him but that brave man was still in my mind that he stood for his conviction n never shopped his collaboration, he died in bravery but Andy with in a month he drop names and their alleged involvement in terrorism!! For our church safety and for the pride of religion we thank ful for exposing names that are directly involved in the smear campaign against our church’s integrity, systematic theft and organised criminality of individuals!! But for those members of G7 n OLF elements u got a lesson of cowardice 101! The same will happen here in uk every one of u will shop each other!! N will have our peace and tranquility!! God save Ethiopia!!”
ከቦታ ቦታ በነጻነት የመንቀሳቀስ የዓለም አቀፍ ሕግ ተጥሶ የአንዳርጋቸው ጽጌ በየመን መታፈንና ለወያኔ አገዛዝ ሰቆቃና ግድያ አሳልፎ መሰጠት አስቆጥቶት አንዳርጋቸው ባስቸኳይ ይፈታና ሕጋዊ የዜግነት መብቱ ይጠበቅለት ዘንድ የእንግሊዝ መንግሥት ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤትን ለመጠየቅ በእንግሊዝ ሃገር ኗሪ የሆኑት በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሰላማዊ ሰልፍ ሲወጡ፤ የወያኔ ቅጥረኛ ባንዳ የሆነው እንዳለ ወንዳፍራሽ ግን በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ መካከል እየኖረ ቀጥሎ የተመለከተውን የወያኔ ፕሮፓጋንዳ በ viber text ያሰራጭ ነበር።
በዚህም ቴክስ ላይ ሰላማዊ ሰልፉን የሚያስተባብሩና ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ሲሉ ቀን ከለሊት በመድከም የሚታወቁትንና ሰልፉን ሲያስተባብሩ የነበሩትን እነ ዶ/ር ወንድሙ መኮንንና አቶ ዘላለም ተሰማን ለማዋረድ ይሞክራል። እንደውም የአንዳርጋቸው መታፈን ቀደም ሲል ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ግፍና በደል ሲፈጸምባቸው ኢትዮጵያዊው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥቶ መቃወሙ ያመጣው መዘዝ ነው በማለት ኢትዮጵያውያኑን ይከሳል።
===============================================================================================
“ I was soo eager to see the video, the Free Andy outside the foreign office! No video, no emotional rant! No burning of flags? But I saw an article from the infamous woizero minitis usually lamenting and blaming every one that is labelled woyaney but herself n her ranting brigade! Last year ZT and her foot soldiers went outside the Saudi embassy showing off their anger by breaking all norms of communication! As invincible entities they released all their clips as if their view and anger would not yield tit for tat retaliation! In less than a year they lost Andy for rendition! For the lasts four years he was traveling through Yemen there were no interception or threat of rendition but because of these emotionally corrupted men of no morale and ethical principles, they brought the jungel rule on themselves, now after realising the legal cautions and possible liabilities they are hiding behind ill composed n unworthy article of woizero Wobdimu and few piX of the usual faces of protestors!!”
==============================================================
ከዚህ በተጨማሪ አንዳርጋቸው ጽጌን በተመለከተ ወያኔ ሌላ ድራማ አዘጋጅቶ በቴሌቪዥን ሊያቀርብ እንደሚችል በመገመት ሕዝቡን አስቀድሞ ለማስገንዘብ ታማኝ በየነ፤ ሲሳይ አጌና፤ ወንድም አገኝና ኤርሚያስ በኢሳት ቲቭ ላይ ያቀረቡትን ትንታኔ በተመለከተ ደግሞ የወያኔው ቅጥረኛ እንዳለ ወንዳፍራሽ በተለይ ለሃገሩም ሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ስሙ ሁሉ ምን ግዜም ታማኝ ሆኖ የኖረውን ታማኝ በየነን ለማዋረድና ለማቃለል ሲል ቀጥሎ የተመለከተውን የviber text አሰራጭቷል።
“Essat commentators such as once who was the toy boy for shek Al mudddeee, the tycoon billionaire and the twat who rained down from helicopter on His wedding day, in the early years of 2004 when the woyaney regime n the tycoon rejected him he was a paid promoter of the political elites, now he is gliding on the fame n glory hunting, a typical character if Narcist he has became the eye sore self promoted political analysit if our country, he is nine other than the reformed woyaney Tamage Beyene! With two other woyaney left overs recently have told us that woyaney is producing a documentary on Andy!! We have got the scoop now!! The star in that documentary is shaleqa Mamo!! Especially his adventure with £100,000 in Ethiopia, the time he wrote his book n got his honey trap wifey! He went to Ethiopia with £100,000 to set up clandestine networks for purpose of political agenda for the political elites of the diaspora; but he consumed the money for his own needs such as throwing a wedding”
ከላይ የተመለከተው የviber text መልዕክት የቅጥረኛ ባንዳው የእንዳለ ወንዳፍራሽ ሲሆን ለማራጋገጫነትም የviber text ኦርጂናል ኮፒ (Screen shot) በገጹ መጨረሻ ላይ መመልከት ይቻላል።
በመጨረሻም
እንዳለ ወንዳፍራሽና ሌሎች የወያኔ ቅጥረኞ ባንዳዎች፤ ለወያኔ ካደሩ ካህናት ጋር በማበር ጨርሶ እውነትነት የሌለውን ነገር እውነት አስመስለው በማሰራጨት በተለይ ወጣት ኢትዮጵያውያንን ለሃይማኖታችሁና ለቤተ ክርስቲያናችሁ ቁሙ! ካህናት ሲዋረዱ ዝም ብላችሁ አትዩ! በዕድሜ የገፋው ሰው ሁሉ ወንጀለኛና ከደርግ፤ ከኢህአፓ፤ ከኦነግና ከመሳሰሉት የጥንት ድርጅቶች የተረፈ ነው እያሉ በማሳሳት ለሃገርና ለሕዝብ በቆሙ ግለሰቦችና ተቋሞች ላይ እንዲነሱ በማድረግ የወያኔ መጠቀሚያ መሣሪያ እያደረጓቸው ይገኛሉ።
ከእነዚህ ወጣቶች ውስጥም የተነገራቸውን በማመን ለትክክለኛ ነገር የቆሙ መስሏቸው ሕግን የተላለፈ ድርጊት ውስጥ በመግባት በወንጀለኛነት እየተመዘገቡ ለመማርም ሆነ ተምሮም ጥሩ ስራ ለመያዝ መስናክል የሚሆን ነገር ውስጥ በማስገባት የወደፊት ዕድላቸ እንዲጨልምባቸው እያደረጓቸው ይገኛሉ።
ይህን ወያኔ በዲያስፖራው ውስጥ በማስፋፋት ላይ ያለውን ሽብርና ምስቅልቅል ለመታደግ፤ “ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው፤ አስቀድሞ መክላት አሾክሿኪውን ነው” እንደተባለው እነዚህ ዲያስፖራው ኢትዮጵያዊን እርስ በርሱ ከፋፍለው በወያኔ ጫማ ሥር እንዲረገጥ ለማድረግ የሚጥሩ ቅጥረኛ ባንዳዎችንና ከሃዲዎችን አውቆና ተገንዝቦ ለይቶ በማወቅ የሚሰሩትን እኩይ ስራ ማምከን ይኖርበታል።
ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኑር!!
አስፋ ምን ተስኖት

No comments: