Sunday, July 13, 2014

በኖርዌ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በሚል ታላቅ ሕዝባዊ ውይይት አደረጉ

July 13/2014


ቅዳሜ ጁለይ 12/2014 በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አዘጋጅነት ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን በሚል አላማ በኖርዌ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የደንነት ሀይሎች መታፈንና ለአምባገነኑ የወያኔ መንግስት ታላልፈው መሰጠታቸውን በተመለከተ ወደ ፊት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከተለያዩ ከተሞች በመሰባሰብ በኖርዌ ኦስሎ ለአምስት ሰዓታት የፈጀ ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል::
ሕዝባዊ ውይይቱ ከቀኑ 15: 00 ሰአት ላይ የተጀመረ ሲሆን ቁጥራቸው በርከት ያሉ ኢትዮጵያኖች የአቶ እንዳርጋቸው ምስል ያለበትና ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን የሚል ጹሁፍ የተጻፉበትን ቲሸርት በመልበስ ለስብሰባው ድምቀት የሰጡት ሲሆን ለአቶ አንዳርጋቸው ያላቸውንም የትግል አጋርነት አስማስክራዋል እነዚህን ቲሸርቶች የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርንጫፍ በራሳቸው አነሳሽነት የሰሩ ሲሆን የድጋፍ ድርጅታችን ወጪውን በመሸፈን ለተሰብሳቢው በነጻ ኣድሏል።
ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሕዝብ ግንኙነት አላፊ አቶ አቢ አማራ በሃያ ሶስት አመታት በወያኔ ጨካኝ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉትና በግፍ ለሚሰቃይዩ ወገኖቻችን የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማስደረግ አስጀምረውታል በመቀጠልም አቶ ዮሀንስ አለሙ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር በስብሰባው ላይ የተገኛውን ሕዝብ እንኮን ደህና መጣችሁ በማለትና በማመስገን ፐሮግራሙን በንግግር የከፈቱት ሲሆን አቶ ዮሀንስ በንግግራቸው የወያኔ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ባደረሰው አፈና ግንቦት 7 የክተት አዋጅ ማስተላለፉን ጠቅሰው አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በአሁን ሰአት በሀገር ቤት በሰላማዊ ትግል እየታገሉ ባሉ ታጋዮች ላይ ሳይቀር እስር እያደረሰባቸው እንዳለ በማመልከት ሰሞንኑን እንኮን የሰመያዊ፣ የአንድነት፣ የአራና የፖለቲካ ድርጅት ከፍተኛ አመራሮች ለስር ተዳርገዋል ብለዋል::
ስለሆነም ህዝባችንን ለእስር እያደረገ ያለውን አገዛዝ ለመቃወም ሁሉም በአንድነት መሰባሰብ እንዳለበት አጠንክረው በመናገር በአሁን ሰአት የአቶ አንዳርጋቸው በወያኔ መታፈንና መታሰር መላውን ኢትዮጵያ ዳር እስከ ዳር እያንቀሳቀሰውና ሕዝቡም እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ በማለት በስፋት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ጠቅሰው በአሁን ሰአት ትግሉ የግንቦት 7 ብቻ አይደለም ይህን ትግል በዚሁ አንድ ሆነን መቀጠል እለብን ብለዋል::
በመቀጠል አቶ ደባስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባል የአቶ አንዳርጋቸውን ከወጣት እድሜያቸው ጀምሮ ያለውን የፖለቲካ አካሄድ አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ማን ነው ? በሚል ርእስ የአቶ አንዳርጋቸውን የትግል ጉዞ የሚዳስስ ዘገባ ሰፋ ባለ ትንታኔ በጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በስብሰባው ላይ የኢሀፓ ፣ የአርበኞች ግንባር፣ የሸንጎ ፣የስደተኛው ማህበር ተወካዮች እና ሌሎችም ሰዎች በየተራ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የየድርጅቷቹም ተወካዮች የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ መታፈንና ለእስር መዳረግን በተመለከተ የድርጅታቸውን አቋም ለተሰብሳቤው ያስረዱ ሲሆን የሁሉም ፖርቲ ተወካይች በአቶ አንዳርጋቸው መታፈንና ለእስር መደረግ ማዘናቸውን ገልጸው ሁሉም በአንድነት በመተባበር በማንኛውም የትግል እንቅስቃሴ የወያኔንን መንግስት ማስወገድ እንዳለባቸው አጽንኦት በመስጠት ተናግረዋል::
በየፕሮግራሞቹ መሀል ግጥሞችና ሌሏችም ፕሮግራሞች ቀርበው የመጀመሪያው ዞር ተጠናቋል::ከ30 ደቂቃ የእረፍት የሻይ እና የቡና ፕሮግራም በኋላ የሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ፕሮግራም በተያዘለት ጊዜ ተጀምሮ የፕሮግራሙን ተሳታፊዎች ያሰተፈ ፕሮግራም በአቶ አብዱ የሱፍ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ስታቫንገር ቅርንጫፍ ምክትል ሊቀመንበር ከግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የተሰጠ ልዩ መግለጫና ተግባሪዊ የመጀመሪያ እርከን የትግል ጥሪን ካብራሩ በኋላ ለተሰብሳቢው ለውይይት በማቅረብ በኖርዌ የምንኖር ኢትዮጵያኖች ይህን የትግል ጥሪ ለማስፈጸም ምን እናድርግ በማለት ለውይይት አቅርበው የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በአቶ ዮሀንስ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሊቀመንበር አወያይ አማካኝነት በስፋት ተወያይተውበታል ::
ተሰብሳቢውም በብዙ ነገሮች ከተወያዩ በኋላ ይሄ ግንቦት 7 ያወጣውን የመጀመሪያ እንከን የትግል ጥሪ ተግባራዊ በየቦታው አለም አቀፍ ታክስ ፎርሶች እየተቋቋሙ እንዳለና በኖርዌይም ይህንኑ ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ የሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቷች ያካተተ ታክስ ፎርስ እንዲቋቋም ተወስኖል:: በመቀጠልም በተሰብሰቢዎች በተመረጡ ሰዎች የተጻፋ ባለ ስድስት አሃዝ የተሰብሳቢው የአቋም መግለጫ ለጉባሄው በጹሁፍ ቀረቦል:: ተሰብሳቢው ያወጣው የአቋም መግለጫ
1. ሁላችንም አንዳርጋቸው ወይም አንድ አርጊያቸው ነን ስንል ለነፃነት፣ ለእኩልነት፣ ለፍትህና ለዲሞክራሲ በሐገራችን ኢትዮጵያ ለማስፈን የሚከፈለውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል ዝግጁዎች ነን ማለታችን ነው።
2. የተለያዩ የፖለቲካና ሲቪክ ማህበራት የሚያደርጉትን መጠላለፍ እንዲቀርና በጋራ ወይም አንድ በመሆን እንዲሰሩ ግፊት እናደርጋለን።
3. ለሚቀርብልን ሐገርን የማዳን ጥሪ ዝግጁ መሆናችንን እንገልፃለን።
4. የየመን መንግስት ከአለም አቀፍ ህግ ጋራ የሚፃረር ስራ በመስራት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለወያኔ አሳልፎ በመስጠት የሰራውን ወንጀል ለዓለም አቀፍ ህግ የማቅረብ ስራ በጋራ እንደምንሰራ።
5. የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ መታፈን ትግሉን የበለጠ እንደሚያጠናክረውና ወደ ውጤት እንዲያመራ የበኩላችንን አስተዋፅኦ እናደርጋለን።
6. ወያኔ የተለያየ ምክንያት በመፍጠር ኢትዮጵያውያንን እስርቤት ማስገባቱን እንዲቀርና የታሰሩትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ እንጠይቃለን በማለት የአቋም መግለጫ አውጥተዋል ።
በመጨረሻም አቶ ዳንሄል አበበ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ምክትል ሰብሳቢ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የአቋም መግለጫ ለተሰብሳቢው በጹሁፍ ያሰሙ ሲሆን በንግግራቸውም አቶ እንዳርጋቸው ጽጌ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት የቋሙ የነጻነት ታጋይ ናቸው እኔም እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ የምንል ሁሉ ለሃያ ሶስት አመታት ህዝብን በዘረኝነት የከፋፈለውን ወያኔን በቃ ልንለው ይገባል ካሉ በኋላ በኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በላይ አፈና፣ ግድያው፣ እስራቱ መጨመሩን በመናገር ይኼን ጨቋኝና አፋኝ ስርአት ለማስወገድ እንነሳ በማለት ጥሪ ያስተላለፉ ሲሆን በመጨረሻ እኔ እንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ እናንተስ በማለት የፕሮግራሙን ተሳታፊ በመጠየቅ ፕሮግራሙ በተያዘለት ሰዓት ከምሽቱ 20:00 ተጠናቋል ::
እኛ ሁላችንም እንዳርጋቸው ጽጌዎች ነን!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ


No comments: