Saturday, July 12, 2014

‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር ነው? ጽዮን ግርማ

July12/2014
‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር ነው? ጽዮን ግርማtsiongir@gmail.comኢትዮጵያ በፓርቲ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባህል ውስጥ የገባችው የ1960ዎቹን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ርዮተ ዓለሞች ተፋጭተው ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ይመሰረትባታል በሚል ተስፋ ቢጣልም የድርጅቶቹ የኋላ ታሪክ እንደሚያስረዳው ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ለውጥ ከማምጣት ይልቅ እርስ በእርስ የመጨራረስ ባህል እንደነበራቸው ነው፡፡ ከበርካታ ንፁሃን ዜጎች ደም መፍሰስና እልቂት በኋላ ህወሓት ኢሕአዴግን መሥርቶ ወደ ሥልጣን ሲመጣም ከሻዕቢያ በስተቀር ሌሎቹ ድርጅቶች እስከ አመራሮቻቸው ደብዛቸው ጠፍቶ ነበር።ኢህአዲግ የሥልጣን ወንበሩን ከጨበጠ በኋላ በሽግግር መንግሥት ምስረታ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ይፋዊ ጥሪ በማስተላለፍ በፓርላማ መቀመጫ እንዲያገኙ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የተመሰረተ ለማስመሰል ጥረት ቢያደርግም በተለያየ ምክንያት አባሮ መልሶ ለመበታተን ጊዜ አልወሰደበትም ነበር ፡፡ ለዓመታት በዘለቀ ቆይታውም ሀገሪቷ ዴሞክራሲያዊ የመኾን ተስፋዋ አንዴ ሲፈግግ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጭርሱኑ ሲደበዝዝ ቆይቶ የምርጫ ታሪክ በተነሳ ቁጥር ምንግዜም ተጠቃሽ የኾነው ሦስተኛውና ታሪካዊው የ1997 ዓ.ም  ሀገራዊ ምርጫ ተስተናገደ፡፡ በድህረ ምርጫውም ሀገሪቱ ሲቪልና ፖለቲካ መብቶችን በማክበር በኩል የበጎ ምግባር ምስክርነትን ማግኘት ጀምራ ነበር፡፡ ነገር ግን በሕዝቦች መራጭነት ዴሞክራሲያዊ የኾነ መንግሥት የሚያስተዳድራት ኢትዮጵያ ልትፈጠር ነው የሚለው የተስፋና የደስታ ስሜት ብዙም ሳይዘልቅ በአንድ ጊዜ ተንኮታክቶ ሀገሪቷን ወደ ሌላ እልቂትና የመከራ አረንቋ ውስጥ ከተታት፡፡ ፍጻሜውም ብዙዎችን ለሞት፣አካል ጉዳት፣እስራት ለስደት ዳረጋቸው፡፡ ሌሎቹን ደግሞ ፍርሃት ውስጥ  ከተታቸው፡፡ ሀገሪቱም የተናፈቀው የመድብለ ፓርቲው ሥርዐት ግንባታው ቀርቶባት ላለፉት በአውራ ፓርቲ ሥርዐት ሥር ወደቀች፡፡  ዐንድ ዓመት የቀረውን ምርጫ ከፊቱ አስቀድሞ ያለፉት ዘጠኝ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ገዢው ፓርቲ፤ [ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የሰፈነባት፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማካሄድ መብት የተረጋገጠባት፣ የመምረጥና የመመረጥ፣የመናገርና የመጻፍ ነጻነት የተከበረባት፣የመድብለ ፓርቲ ሥርዐት የሰፈነባት፣የዜጎች በፈለጋቸው ቦታ ሠርቶ ሀብት የማፍራትና ሠርቶ የመኖር መብት የተረጋገጠበት፣የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣የብሔርና ብሔረሰቦች መብት የተከበረባት] በአጠቃላይ ለሰው ልጅ የሚያስፈልጉ መብቶች ኹሉ የተከበረባት ‹‹የተቀደሰች ሀገር›› መኾኗን ጠዋት ማታ ለሕዝቡ በማስታወስ በሕግ ከተደነገጉት መብቶቹ ውጪ በመጠቀም ይህችን ‹‹ቅድስት›› ሀገርና ሕዝቦቿን ለማተራመስ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ሰው ‹‹ቀዩን መስመር›› እንዳለፈ ተቆጥሮ እርምጃ እንደሚወሰድበት፣በዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ጨዋታ የማይረገጠውን ''ቀይ መስመር'' የረገጠ አካል ለሀገርና ለሕዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል በሕግ እንደሚጠየቅ እንደ ‹‹ፈንጂ ወረዳና ዐሥራ አንደኛው ሰዓት›› የመሳሰሉ ተጨማሪ ዐረፍተ ነገሮች እየታከሉበት ከአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ ጀምሮ ሲሰጥ የቆየ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን ከያዙ በኋላም ቢኾን እርሳቸውና ሌሎች ባለሥልጣናት ባገኙትና ኾን ብለው በሚፈጥሩት አጋጣሚ፤ከምድራዊ ችግሮች ኹሉ የጸዳች፣ ሕዝቦቿ ከድህነት ወጥተው፣በዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ታጅበው በሰላም የሚኖሩባት ኢትዮጵያ የምትተዳደርበትን ሕገ-መንግስታዊ ሥርዐት ለመናድ የሚንቀሳቀሱ ሓይሎች ‹‹ቀዩን መስመር›› እያለፉ መኾናቸውን ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ የአገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣በውጭ ሀገር የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ ሐይማኖታዊ መብት ጠያቂዎች፣ጋዜጠኞችና ጸሐፊዎች፣ተማሪዎችና የሰብዓዊ መብት ጠያቂዎች በተለያየ ጊዜ እየተሰበሰቡ ወደ እስር ቤት ሲላኩም  አገሪቱን ለማተራመስ ‹‹ቀዩን መስመር›› አልፈው በመገኘታቸው እንደኾነ ከዶክመንተሪ ፊልም ጋራ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡ የአገር ውስጥ የፓርቲ አመራሮችና አባላትገዢው ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የሰፈነባት፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማካሄድ ፣የመምረጥና የመመረጥ መብትና ሌሎችም ሰብዓዊና ዴሞክርሲያዊ መብቶች የተረጋገጡባት ሀገር መኾኗን በሚሰብክላት ኢትዮጵያ  ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመት ውስጥ፤ የአገር ውስጥ የፓርቲ አመራሮችና አባላት የራሳቸው ውስጥ ችግር እንደተጠበቀ ኾኖ በገዢው ፓርቲ በኩል የሚገጥማቸውን ድብደባ፣ማንገላታትና ክልከላ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይሰማሉ፡፡ ከዚህ ባስ ሲልም የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱአለም አራጌ፣ የኦፌዴን ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች አመራሮች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም እየታሰሩ የሚፈቱ፣የሚደበደቡ፣ሰልፍ የሚከለከሉ የፓርቲ አመራርና አባላት በየጊዜው ከሚሰጡት መግለጫ ይሰማል፡፡ ባሳለፍነው ማክሰኞ ከአንድነት ፓርቲ ሓላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ ከሰማያዊው ፓርቲ ደግሞ አቶ የሺዋስ አሰፋ ታስረዋል፡፡ በውጭ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትመንግሥት በውጭ ሀገር የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ ድርጅቶች፣ አመራሩንና አባላቱን በሚመለከት የጸረ ሽብር ዐዋጁን ካጸደቀ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 7፣ አልቃይዳ፣ አልሸባብ፣ ኦነግና ኦብነግን  በአሸባሪነት እንዲፈረጁ አድርጓል፡፡በዚህም መሠረት ከኢትዮጵያ ውጪ እየኖሩ ሓሳባቸውን በተለያየ መንገድ የሚገልጹ ጋዜጠኞችን፣ግለሰቦችንና ድርጅቶችን በሌሉበት በአሸባሪነት ክስ በመመስረት የእስር ውሳኔ የሚያወጣባቸው ሲኾን አገር ውስጥ ኾነው ከእነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋራ ተገናኝተዋል በሚል ታስረው የተፈረደባቸው ሰዎች ቁጥር እጅግ በርካታ ነው፡፡ በአሸባሪነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራር አባላት፤‹‹አገር ውስጥ ካሉ ተባባሪዎቻቸው ጋራ በመኾን በህቡዕ ተደራጅተው ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን በሓይል ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል›› በሚል ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣አቶ አሳምነው ጽጌ፣ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሀገር ውስጥ የሚገኙት ጄኔራል ተፈራ ማሞና አሳምነው ጽጌ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ሲወስን፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሞት እንዲቀጡ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ሰሞኑን በአገር ውስጥና በውጭ ሀገር መነጋገሪያ ኾነው የሰነበቱት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከዱባይ ወደ አስመራ በመጓዝ የመን ውስጥ ሰንዓ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለትራንዚት ሲወርዱ ታግተው መቆየታቸውና  ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው መሰጠታቸው፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥትም ተላልፈው አልተሰጡኝም›› ሲል ቆይቶ በመጨረሻም እጃቸው ከተያዘበት ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ጠቅሶ በምስል ጭምር አሳይቷቸዋል፡፡ በአኹኑ ሰዓትም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ሐይማኖታዊ መብት ጠያቂዎችመንግሥት ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲወጣና መሪዎቻቸውን በራሳቸው መንገድ እንዲመርጡ ባነሱት የመብት ጥያቄ ሙስሊሞች ተቃውሞ ተጋግሎ በመጨረሻም የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሑራን፣ ጋዜጠኞች፣መጽሐፍ ጸሐፊዎች፣ ነጋዴዎችና ወጣቶች በገፍ እየተለቀሙ ታስረዋል፡፡ በሌላም በኩል ከተመሰረተ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረው በክርስትና እምነት ተከታዮች የተቋቋመው ‹‹ማኅበረ ቅዱሳ››ን ‹‹በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጥብጥና ትርምስ ለመፍጠር ይንቀሳቀሳል ›› የሚል ተቀጥላ ተለጥፎለት ማኅበሩ በመፍረስ አመራሮቹም በመታሰር ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡  ጋዜጠኞችና ጸሐፊዎችእንደ ገዢው ፓርቲ ተደጋጋሚ አነጋገር ከኾነ ሀገሪቱ የመጻፍና የመናገር መብትና ነጻነት ተከብሮባታል፡፡ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬና ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ ሐሳቦቻቸውን ሲገልጹ የቆዩት በእነዚህ መብቶቻቸው ተጠቅመው ነበር፡፡ ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችና ሦስት ጋዜጠኞች በኢሕአዴግ አነጋገር ከተከበረው መብታቸው ሽራፊዋን ብቻ ቆርሰው ሐሳባቸውን በጹሑፍ ሲገልጹ የነበሩ ምሑራን ወጣቶች ናቸው፡፡ አብርሃ ደስታ  ሐሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱን በመጠቀምና የሌሎችን የመናገር ነጻነት በማክበር በማኅበራዊ ድረ ግጽ ላይ የውይይት ባህል እንዲዳብር በመታገል የሚታወቅ ወጣት ነው፡፡ እንዚህ ኹሉ ጸሐፊዎች ‹‹ቀዩን መስመር›› አልፋችኋል በሚል በተለያየ ጊዜ ተይዘው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡    ‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር ነው? በሞያቸውና በፖለቲካ እምነታቸው ምክንያት አኹን በእስር ላይ የሚገኙትም ኾነ ያልታሰሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ያነሷቸውና የሚያነሷቸው ጥያቄዎች፤መልካም አስተዳደር፣የሕግ የበላይነት፣የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች፣ የፀረ-ሽብር ዐዋጁ መደፍጠጥ እንደሌለበት፣ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል፣የሥራ እጥነት እንዲቀር፣ የመሬት ጥያቄ፣ የኑሮ ውድነትና የመሳሰሉ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበሩ የሚሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ኢህአዴግ እነዚህን መብቶች እንዳከበረ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ይሰማል፡፡ ጥያቄው የሚነሳው ችግሩ ኖሮ ሳይኾን ጥያቄውን የሚያነሱት ግለሰቦች፤ከውጭ ሓይል ገንዘብ ተቀብለው ሀገሪቱን ለማተራመስ የሚሠሩ ናቸው በሚል በሀገር ከሀዲነት ይፈርጃቸዋል፡፡ አሸባሪ፣ አክራሪና ተላላኪ የሚሉ ስሞችን በመለጠፍ ‹‹ቀዩን መስመር አለፋችሁ››በማለት ወደ እስር ቤት ይወረውራቸዋል፡፡ የመብት ጥያቄን የሚያነሳን አካል እጅ በመጠምዘዝ በአገሪቱ የሚከናወን ማንኛውም ጥያቄ በገዢው ፓርቲ መልካም ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ እንዲኾን ያደርጋል፡፡ ከእዛ ውጭ ያለው ግን ለሀገሩ የማያስብ አፍራሽ አድርጎ ይስለዋል፡፡ ነገር ግን በየጊዜው የሚነሱት እነዚህ ጥያቄዎች በአገሪቱ ውስጥ ተከብሯል በሚባሉት መብቶች ሥር የሚጠቃለሉ ሊኾኑ ይገባቸው ነበር፡፡ እነዚህ መብቶች የተረጋገጡ ከኾኑ ጥያቄዎቹም ‹‹ቀዩን መስመር›› ያለፉ የሽብር ዓላማን ያነገቡ አይባሉም ነበር፡፡ጥያቄዎቹን የሚያነሱት ግለሰቦችም በሀገሪቱ ውስጥ በሰላም የመኖር መብታቸው ሊከበርላቸው የሚገባ እንጂ ‹‹አሸባሪዎች›› ተብለው ሊታሰሩና ሰብዓዊ መብታቸው ሊረገጥ አይገባውም ነበር፡፡ መብታቸውን በተግባር ለመተግበር የሚሞክሩና ጥያቄዎቻቸውን በተለያየ መንገድ የሚያሰሙ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚታሰሩ ከኾነ ቢያንስ ከዚህ በኋላ በጸረ ሽብር ዐዋጁ ተከልሎ የተሰመረው ‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር እንዳለ ግልጽ ሊደረግ ይገባል፡፡ በፊት ለፊት ዴሞክራሲያዊነት እየሰበኩ በጎን በኩል ሰው አፍንጫ ስር መልሶ ከማስመር መጀመሪያዉ ‹‹ቀዩ መስመር›› የት እንዳለ ግልጽ ቢደረግ ለጥንቃቄም ይረዳል፡፡
ኢትዮጵያ በፓርቲ ላይ የተመሰረተ ፖለቲካ ባህል ውስጥ የገባችው የ1960ዎቹን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የተለያዩ ርዮተ ዓለሞች ተፋጭተው ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ይመሰረትባታል በሚል ተስፋ ቢጣልም የድርጅቶቹ የኋላ ታሪክ እንደሚያስረዳው ለሀገርና ለሕዝብ የሚጠቅም ለውጥ ከማምጣት ይልቅ እርስ በእርስ የመጨራረስ ባህል እንደነበራቸው ነው፡፡ ከበርካታ ንፁሃን ዜጎች ደም መፍሰስና እልቂት በኋላ ህወሓት ኢሕአዴግን መሥርቶ ወደ ሥልጣን ሲመጣም ከሻዕቢያ በስተቀር ሌሎቹ ድርጅቶች እስከ አመራሮቻቸው ደብዛቸው ጠፍቶ ነበር።ኢህአዲግ የሥልጣን ወንበሩን ከጨበጠ በኋላ በሽግግር መንግሥት ምስረታ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ይፋዊ ጥሪ በማስተላለፍ በፓርላማ መቀመጫ እንዲያገኙ በማድረግ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የተመሰረተ ለማስመሰል ጥረት ቢያደርግም በተለያየ ምክንያት አባሮ መልሶ ለመበታተን ጊዜ አልወሰደበትም ነበር ፡፡

ለዓመታት በዘለቀ ቆይታውም ሀገሪቷ ዴሞክራሲያዊ የመኾን ተስፋዋ አንዴ ሲፈግግ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጭርሱኑ ሲደበዝዝ ቆይቶ የምርጫ ታሪክ በተነሳ ቁጥር ምንግዜም ተጠቃሽ የኾነው ሦስተኛውና ታሪካዊው የ1997 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ተስተናገደ፡፡ በድህረ ምርጫውም ሀገሪቱ ሲቪልና ፖለቲካ መብቶችን በማክበር በኩል የበጎ ምግባር ምስክርነትን ማግኘት ጀምራ ነበር፡፡ ነገር ግን በሕዝቦች መራጭነት ዴሞክራሲያዊ የኾነ መንግሥት የሚያስተዳድራት ኢትዮጵያ ልትፈጠር ነው የሚለው የተስፋና የደስታ ስሜት ብዙም ሳይዘልቅ በአንድ ጊዜ ተንኮታክቶ ሀገሪቷን ወደ ሌላ እልቂትና የመከራ አረንቋ ውስጥ ከተታት፡፡ ፍጻሜውም ብዙዎችን ለሞት፣አካል ጉዳት፣እስራት ለስደት ዳረጋቸው፡፡ ሌሎቹን ደግሞ ፍርሃት ውስጥ ከተታቸው፡፡ ሀገሪቱም የተናፈቀው የመድብለ ፓርቲው ሥርዐት ግንባታው ቀርቶባት ላለፉት በአውራ ፓርቲ ሥርዐት ሥር ወደቀች፡፡

ዐንድ ዓመት የቀረውን ምርጫ ከፊቱ አስቀድሞ ያለፉት ዘጠኝ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ገዢው ፓርቲ፤ [ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የሰፈነባት፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማካሄድ መብት የተረጋገጠባት፣ የመምረጥና የመመረጥ፣የመናገርና የመጻፍ ነጻነት የተከበረባት፣የመድብለ ፓርቲ ሥርዐት የሰፈነባት፣የዜጎች በፈለጋቸው ቦታ ሠርቶ ሀብት የማፍራትና ሠርቶ የመኖር መብት የተረጋገጠበት፣የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣የብሔርና ብሔረሰቦች መብት የተከበረባት] በአጠቃላይ ለሰው ልጅ የሚያስፈልጉ መብቶች ኹሉ የተከበረባት ‹‹የተቀደሰች ሀገር›› መኾኗን ጠዋት ማታ ለሕዝቡ በማስታወስ በሕግ ከተደነገጉት መብቶቹ ውጪ በመጠቀም ይህችን ‹‹ቅድስት›› ሀገርና ሕዝቦቿን ለማተራመስ የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ሰው ‹‹ቀዩን መስመር›› እንዳለፈ ተቆጥሮ እርምጃ እንደሚወሰድበት፣በዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ጨዋታ የማይረገጠውን ''ቀይ መስመር'' የረገጠ አካል ለሀገርና ለሕዝብ ሰላምና ደህንነት ሲባል በሕግ እንደሚጠየቅ እንደ ‹‹ፈንጂ ወረዳና ዐሥራ አንደኛው ሰዓት›› የመሳሰሉ ተጨማሪ ዐረፍተ ነገሮች እየታከሉበት ከአቶ መለስ ዜናዊ አገዛዝ ጀምሮ ሲሰጥ የቆየ ማስጠንቀቂያ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን ከያዙ በኋላም ቢኾን እርሳቸውና ሌሎች ባለሥልጣናት ባገኙትና ኾን ብለው በሚፈጥሩት አጋጣሚ፤ከምድራዊ ችግሮች ኹሉ የጸዳች፣ ሕዝቦቿ ከድህነት ወጥተው፣በዴሞክራሲያዊ ሥርዐት ታጅበው በሰላም የሚኖሩባት ኢትዮጵያ የምትተዳደርበትን ሕገ-መንግስታዊ ሥርዐት ለመናድ የሚንቀሳቀሱ ሓይሎች ‹‹ቀዩን መስመር›› እያለፉ መኾናቸውን ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ የአገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣በውጭ ሀገር የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ ሐይማኖታዊ መብት ጠያቂዎች፣ጋዜጠኞችና ጸሐፊዎች፣ተማሪዎችና የሰብዓዊ መብት ጠያቂዎች በተለያየ ጊዜ እየተሰበሰቡ ወደ እስር ቤት ሲላኩም አገሪቱን ለማተራመስ ‹‹ቀዩን መስመር›› አልፈው በመገኘታቸው እንደኾነ ከዶክመንተሪ ፊልም ጋራ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፡፡

የአገር ውስጥ የፓርቲ አመራሮችና አባላት

ገዢው ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዐት የሰፈነባት፣ ሰላማዊ ሰልፍ የማካሄድ ፣የመምረጥና የመመረጥ መብትና ሌሎችም ሰብዓዊና ዴሞክርሲያዊ መብቶች የተረጋገጡባት ሀገር መኾኗን በሚሰብክላት ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለትና ሦስት ዓመት ውስጥ፤ የአገር ውስጥ የፓርቲ አመራሮችና አባላት የራሳቸው ውስጥ ችግር እንደተጠበቀ ኾኖ በገዢው ፓርቲ በኩል የሚገጥማቸውን ድብደባ፣ማንገላታትና ክልከላ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይሰማሉ፡፡ ከዚህ ባስ ሲልም የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አንዱአለም አራጌ፣ የኦፌዴን ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች አመራሮች በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም እየታሰሩ የሚፈቱ፣የሚደበደቡ፣ሰልፍ የሚከለከሉ የፓርቲ አመራርና አባላት በየጊዜው ከሚሰጡት መግለጫ ይሰማል፡፡ ባሳለፍነው ማክሰኞ ከአንድነት ፓርቲ ሓላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሽበሺ፣ ከሰማያዊው ፓርቲ ደግሞ አቶ የሺዋስ አሰፋ ታስረዋል፡፡

በውጭ የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት

መንግሥት በውጭ ሀገር የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ ድርጅቶች፣ አመራሩንና አባላቱን በሚመለከት የጸረ ሽብር ዐዋጁን ካጸደቀ በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ግንቦት 7፣ አልቃይዳ፣ አልሸባብ፣ ኦነግና ኦብነግን በአሸባሪነት እንዲፈረጁ አድርጓል፡፡በዚህም መሠረት ከኢትዮጵያ ውጪ እየኖሩ ሓሳባቸውን በተለያየ መንገድ የሚገልጹ ጋዜጠኞችን፣ግለሰቦችንና ድርጅቶችን በሌሉበት በአሸባሪነት ክስ በመመስረት የእስር ውሳኔ የሚያወጣባቸው ሲኾን አገር ውስጥ ኾነው ከእነዚህ ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋራ ተገናኝተዋል በሚል ታስረው የተፈረደባቸው ሰዎች ቁጥር እጅግ በርካታ ነው፡፡

በአሸባሪነት የተፈረጀው የግንቦት ሰባት ድርጅት አመራር አባላት፤‹‹አገር ውስጥ ካሉ ተባባሪዎቻቸው ጋራ በመኾን በህቡዕ ተደራጅተው ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱን በሓይል ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል›› በሚል ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣አቶ አሳምነው ጽጌ፣ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሀገር ውስጥ የሚገኙት ጄኔራል ተፈራ ማሞና አሳምነው ጽጌ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ሲወስን፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሞት እንዲቀጡ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ሰሞኑን በአገር ውስጥና በውጭ ሀገር መነጋገሪያ ኾነው የሰነበቱት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከዱባይ ወደ አስመራ በመጓዝ የመን ውስጥ ሰንዓ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለትራንዚት ሲወርዱ ታግተው መቆየታቸውና ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው መሰጠታቸው፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥትም ተላልፈው አልተሰጡኝም›› ሲል ቆይቶ በመጨረሻም እጃቸው ከተያዘበት ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ጠቅሶ በምስል ጭምር አሳይቷቸዋል፡፡ በአኹኑ ሰዓትም በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

ሐይማኖታዊ መብት ጠያቂዎች

መንግሥት ከሃይማኖት ጣልቃ ገብነት እንዲወጣና መሪዎቻቸውን በራሳቸው መንገድ እንዲመርጡ ባነሱት የመብት ጥያቄ ሙስሊሞች ተቃውሞ ተጋግሎ በመጨረሻም የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሑራን፣ ጋዜጠኞች፣መጽሐፍ ጸሐፊዎች፣ ነጋዴዎችና ወጣቶች በገፍ እየተለቀሙ ታስረዋል፡፡ በሌላም በኩል ከተመሰረተ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረው በክርስትና እምነት ተከታዮች የተቋቋመው ‹‹ማኅበረ ቅዱሳ››ን ‹‹በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብጥብጥና ትርምስ ለመፍጠር ይንቀሳቀሳል ›› የሚል ተቀጥላ ተለጥፎለት ማኅበሩ በመፍረስ አመራሮቹም በመታሰር ስጋት ውስጥ ናቸው፡፡

ጋዜጠኞችና ጸሐፊዎች

እንደ ገዢው ፓርቲ ተደጋጋሚ አነጋገር ከኾነ ሀገሪቱ የመጻፍና የመናገር መብትና ነጻነት ተከብሮባታል፡፡ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬና ጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ ሐሳቦቻቸውን ሲገልጹ የቆዩት በእነዚህ መብቶቻቸው ተጠቅመው ነበር፡፡ ስድስት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችና ሦስት ጋዜጠኞች በኢሕአዴግ አነጋገር ከተከበረው መብታቸው ሽራፊዋን ብቻ ቆርሰው ሐሳባቸውን በጹሑፍ ሲገልጹ የነበሩ ምሑራን ወጣቶች ናቸው፡፡ አብርሃ ደስታ ሐሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱን በመጠቀምና የሌሎችን የመናገር ነጻነት በማክበር በማኅበራዊ ድረ ግጽ ላይ የውይይት ባህል እንዲዳብር በመታገል የሚታወቅ ወጣት ነው፡፡ እንዚህ ኹሉ ጸሐፊዎች ‹‹ቀዩን መስመር›› አልፋችኋል በሚል በተለያየ ጊዜ ተይዘው በእስር ላይ ይገኛሉ፡፡

‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር ነው?

በሞያቸውና በፖለቲካ እምነታቸው ምክንያት አኹን በእስር ላይ የሚገኙትም ኾነ ያልታሰሩ ግለሰቦችና ድርጅቶች ያነሷቸውና የሚያነሷቸው ጥያቄዎች፤መልካም አስተዳደር፣የሕግ የበላይነት፣የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ ጥያቄዎች፣ የፀረ-ሽብር ዐዋጁ መደፍጠጥ እንደሌለበት፣ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ፣ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል፣የሥራ እጥነት እንዲቀር፣ የመሬት ጥያቄ፣ የኑሮ ውድነትና የመሳሰሉ የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ይከበሩ የሚሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡

ኢህአዴግ እነዚህን መብቶች እንዳከበረ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ይሰማል፡፡ ጥያቄው የሚነሳው ችግሩ ኖሮ ሳይኾን ጥያቄውን የሚያነሱት ግለሰቦች፤ከውጭ ሓይል ገንዘብ ተቀብለው ሀገሪቱን ለማተራመስ የሚሠሩ ናቸው በሚል በሀገር ከሀዲነት ይፈርጃቸዋል፡፡ አሸባሪ፣ አክራሪና ተላላኪ የሚሉ ስሞችን በመለጠፍ ‹‹ቀዩን መስመር አለፋችሁ››በማለት ወደ እስር ቤት ይወረውራቸዋል፡፡

የመብት ጥያቄን የሚያነሳን አካል እጅ በመጠምዘዝ በአገሪቱ የሚከናወን ማንኛውም ጥያቄ በገዢው ፓርቲ መልካም ፈቃድ ላይ ብቻ የተመሰረተ እንዲኾን ያደርጋል፡፡ ከእዛ ውጭ ያለው ግን ለሀገሩ የማያስብ አፍራሽ አድርጎ ይስለዋል፡፡ ነገር ግን በየጊዜው የሚነሱት እነዚህ ጥያቄዎች በአገሪቱ ውስጥ ተከብሯል በሚባሉት መብቶች ሥር የሚጠቃለሉ ሊኾኑ ይገባቸው ነበር፡፡ እነዚህ መብቶች የተረጋገጡ ከኾኑ ጥያቄዎቹም ‹‹ቀዩን መስመር›› ያለፉ የሽብር ዓላማን ያነገቡ አይባሉም ነበር፡፡ጥያቄዎቹን የሚያነሱት ግለሰቦችም በሀገሪቱ ውስጥ በሰላም የመኖር መብታቸው ሊከበርላቸው የሚገባ እንጂ ‹‹አሸባሪዎች›› ተብለው ሊታሰሩና ሰብዓዊ መብታቸው ሊረገጥ አይገባውም ነበር፡፡

መብታቸውን በተግባር ለመተግበር የሚሞክሩና ጥያቄዎቻቸውን በተለያየ መንገድ የሚያሰሙ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚታሰሩ ከኾነ ቢያንስ ከዚህ በኋላ በጸረ ሽብር ዐዋጁ ተከልሎ የተሰመረው ‹‹ቀዩ መስመር›› የቱ ጋር እንዳለ ግልጽ ሊደረግ ይገባል፡፡ በፊት ለፊት ዴሞክራሲያዊነት እየሰበኩ በጎን በኩል ሰው አፍንጫ ስር መልሶ ከማስመር መጀመሪያዉ ‹‹ቀዩ መስመር›› የት እንዳለ ግልጽ ቢደረግ ለጥንቃቄም ይረዳል፡፡

No comments: