Friday, July 25, 2014

የጥቁር ሽብር ሂደት እና የጋዜጠኛ አብይ አፈወርቅ መልዕክት

July24/2014
(ኢ.ኤም.ኤፍ) ለዛሬው ወደ እስር ቤት አካባቢ እንወስዳችኋለን። መቼም በኢትዮጵያ የሚገኙ እስር ቤቶች ሰውን ለማረም ሳይሆን፤ በአመለካከት የተለየን ሰው ለማሰቃየት ተብለው የተሰሩ ነው የሚመስለው። በአሁኑ ወቅት ሰርቆ እና ሰው ገድሎ እስር ቤት ከገባ ሰው ይልቅ ኢህአዴግን ወቅሶ የጻፈ እና የተናገረ ሰው ብዙ ስቃይ እንደሚደርስበት ምንም መጠያየቅ ወይም መረጃ መቀያየር አያስፈልግም። በጣም የሚያሳዝነው ደግሞ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የሚደረጉት በህግ ሽፋን ነው። የህጉም አንቀጽ “ሽብርተኝነት” መሆኑ በግልጽ ተደንግጎ በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ወጥቷል። ይህ መንግስት በህዝቡ ላይ የሚያደርሰው ጥቃት “ጥቁር ሽብር” የሚል ስያሜን አግኝቷል። እናም የሰሞኑ የጥቁር ሽብር ሰለባዎችን ጉዳይ እናስነብባችሁ እና በመጨረሻም አንድ ቅንብር እንጋብዛችኋለን።
በቅድሚያ አቤት ያደረሰንን አዲሰ መረጃ እናካፍላችሁ። በቅርቡ የታሰሩትን የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች አስመልክቶ እንዲህ ይላል።
ወያኔ በህገ ወጥ እስር በማእከላዊ እያሰቃያቸው የሚገኙት የሺዋሰ አሰፋ፣ አብርሃ ደስታ፣ ሃብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ በተለያዩ ጨለማ ክፍሎች ከየብቻ ታስረው እንደሚገኙና ሌሊት ሌሊት ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሚገኝ ለእስር ቤቱ ቅርብ ከሆኑ ምንጮች ያገኘኋቸው መረጃዎች አረጋግጠውልኛል፡፡ እነዚህ ሰላማዊ ታጋዮች በየቀኑ በሚደረግባቸው ድብደባ እና ስቃይ ምክንያት የሰውነታቸው ክብደት በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ የሙስሊሙ ድምጽ የሆነው ቢ.ቢ.ኤን “መንግስት በኮሚቴዎቻችን ቤተ ሰቦች ላይ የተለያየ ጥቃት እና በደል እያደረሰ ነው፡ በማለት
በጥይት የተመታው የኡስታዝ ያሲን ኑሩ ወንድም ወደ ማእከላዊ የተወሰደ መሆኑን እንዲህ ሲል መረጃውን ለቋል።
ጁምዓ ሐምሌ 11 ቀን 2006 የመንግስት ሃይሎች በአንዋር መስጂድ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን ሊያሰማ የተሰባሰበው ህዝበ ሙስሊም ላይ በወሰዱት ኢ-ሰብኣዊ የ‹‹ጥቁር ሽብር›› የሃይል እርምጃ በጥይት የተመታው የኡስታዝ ያሲን ኑሩ ወንድም ወደ ማእከላዊ ተወሰደ::
BBN ቢቢኤን የናንተው ድምፅ
በመጨረሻም የሙያ ባልደረባችን የሆነው ጋዜጠኛ አብይ አፈወርቅ ዛሬ ከአውስትራልያ የላከልን መልእክት በኢትዮጵያ ውስጥ እየደረሰ ያለውን ጥቁር ሽብር በዝርዝር ገልጿል።
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙ አሰቃቂ የማሰቃያ (torture) አይነቶችን በሚመለከት የተጠናቀረውን ልዩ ዝግጅት ጋዜጠኛ አቢይ አፈወርቅ (አውስትራሊያ -ሲድኒ) እንዲህ ያቀርበዋል።

No comments: