Sunday, July 27, 2014

የ53 አመቱ አባት የጥቁር ሽብር ሰለባ አስገራሚ ክስተት

July 27/2014
ቢቢኤን ራድዮ እንዳቀረበው፦
መንግስት ሀምሌ 11 በወሰደው የጭካኔ ተግባር ወጣቱ ወንዱ ሴቱ ህጻናቱ አዛውንቱ የጥቁር ሽብሩ ሰለባ ሁነዋል፡፡ የዚህ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል የ53 አዛውንት ሰው ይገኙበታል፡፡ ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የርሳቸውን በከፍተኛ ድብደባ የቆሰለ ሰውነት ነው፡፡
የ53 አመቱ ሰው ከቢቢኤን ሬድዪ ጋር የደረሰባቸውን ነገር አስመልክቶ ቆይታ አድረግዋል፡፡ ሙሉዉን ቆይታ ከራሳቸው አንደበት የምትሰሙት ይሆንና በመጠኑ ቀንጭበን በጽሁፍ እናካፍላችሁ፡፡
Muslim abat
የጁምአን ሶላት በአንዋር መስጅድ ለመስገድ ዘግየት ብለው ስለደረሱ ውጭ አስባልት ላይ ነበር መስገጃ ካኪ ያነጠፉት፡፡ ምንም ተቃውሞ ባልተጀመረበት ሶላትም ባልተሰገደበት ሁኔታ ፖሊሶች መስግጃውን አንሱ በማለት ትንኮሳ ጀመሩ ይላሉ ግለሰቡ፡፡ እርሳቸውም ከእድሚያቸው አንጻር ሁኔታዎቹን ለማረጋገት ይሞከራሉ፡፡ በዚህ ሰአት ግን የፖሊሶቹ ምላሽ ያልጠበቁት ነበር ፡፡ በያዙት ዱላ ለሶላት የተሰበሰበውን ምእምናን መደበደብ ጀመሩ፡፡ እኚህ አባትን በርካታ ፖሊሶች ከበው ይደብድቡዋቸው ጀመር፡፡
የዱላ ውርጅብኝ የበዛባቸው አባትም ወደ መዲና ህንጻ ሩጠው ይገባሉ፡፡ ፖሊሶች ተከትለው ከገቡ በሁላ እየጎተቱ መሬት ላይ በመዘርጋት ዘግናኝ ድብደባ እንደፈጸሙባቸው ይናገራሉ፡፡ በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ ከእድሜያቸው አንጻር በዚሁ እንኩዋን አልተዋቸውም፡፡ በጾመኛ አንጀታችው እየደበደቡ ወደ ልኩዋንዳ ፈጥኖ ፖሊስ ማሰልጠኛ ወሰዱዋቸው፡፡
ልኩዋንዳ ሲደርሱ እሳት እየነደደ ነበር ይላሉ፡፡ ከዛም የሴቶችን ጅልባብ ሀይማኖታዊ አልባሳት የሳቸውም ኮፍያ ጭምር በሳት ተቃጠለ፡፡ ወደ ሰፊ ሜዳ ከወሰዱዋቸው በሙሉ በግራና በቀኝ ዙርያውን ፖሊሶች ተደርድረው በመሃል እየቀጠቀጡ ከፍተኛ ድብደባ ተፈጸመባቸው፡፡ በ120 በ90 ሜትር የሚሆነውን ሜዳ እያዞሩ ቀጠቀጡን ሲሉ ይናገራሉ አዛውንቱከድብደባውም ሌላ ኮፍያቸው ጫማቸው ተቃጥልዋል፡፡ አጸያፊ ስድብም ተሰድበዋል፡፡ ዱላቸው ተሰባብሮ ሲያልቅ እሳት ረመጡን እንዲረግጡ አድረገዋቸው፡፡ እስከ ሌሊቱ 9 ሰአት ይህ ሁሉ ሲፈጸምባቸው ጾመኛ ነበሩ፡፡
ዘጠኝ ሰአት ላይ አውጥተው ጣልዋቸው፡፡ ሌሊት ለተሃጁድ ሶላት የሚሄዱ ሰዎች ሲያገኙዋቸው አለቀሱ፡፡ የ53 አመቱ አባት ጀርባቸው በምስሉ እንደሚታየው ቆስሉዋል:: ራሳቸው ተፈርክስዋል፡፡
በመጨረሻም ምን ይላሉ ሲል የቢቢኤን ጋዜጠኛ አብዱረሂም ላቀረበላቸው ጥያቄ አዛውንቱ አስገራሚ ምላሽ ሰጡ፡፡ እንዲህም አሉ ”የደረሰብኝ ነገር የሰው ልጅ በወገኑ ላይ የሚፈጸመው ተግባር አይደለም፡፡ ይህም ሁኖ ግን ሰላማዊነታችንን በፍጹም መተ ው የለብንም፡፡ ድምጻችን ይሰማ ጁምአ ቢጠራ ሰባራ እጄን ወንድሞቼ ጋር እሰለፋሉ የምንፈልጋት ሰላማዊ ትግል ውጤት እስክትመጣ ሌላ ምን አደረጋለሁ፡፡ ለሙስሊሙ የማስተላልፈው ሰላማዊ ትግላችን መቀጠል አለበት፡፡ ይህን ስል ሁሉም ይደብደብ ማለቴ ሳይሆን እውነተኛ ነጻነታችን የምትከበርባት ሀገር እስክትመጣ መታገል አለብን፡፡ አንድነታችን ይዘን ጥያቄያችን እስኪመለስ እነሱ ይግደሉን እነሱ ይጨፍጭፉን እኛ በሰላማዊ ትግል አሻራችንን እናሳረፍ፡፡ በኔ የደረሰው ኢምንት ነው በጥይትም የተመቱ አሉ እንበርታ ይላሉ የ53 አመቱ አባት፡:
ለመስማት ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ
http://goo.gl/pYP0hD
በጣም አነስተኛ መጠን ያለው ሊንክ
http://goo.gl/NBc1Kx

No comments: