Wednesday, July 9, 2014

ወጣቱ ፖለቲከኛ የአረና አመራር አብርሃ ደስታ በወያኔ ታጣቂዎች እየተደበደበ ወዳልታወቀ እስር ቤት መወሰዱ ተሰማ

July 8/ 2014
ገዛኸኝ አበበ
አንባገነኑ የወያኔ መንግስት አሁንም የሃገር ቤት ተቃዋሚ አመራሮችን ማሰርንን ተያይዞታል :: በዛሬው ቀንም ታዋቂውና የወያኔን ብልሹ የፖለቲካ አካሄድ በግልጽ በተለያዩ ሚዲያዎችና በማህበራዊ ድህረ ገጾች ሳይቀር በድፍረት በመቃወም የሚታወቀውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብዙ ኢትዮጵያኖች ዘንድ ተወዳጅነትን እያተረፈ የመጣው ታዋቂው  የዓረና ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ወጣቱ ፖለቲከኛ  አብርሃ ደስታ በወያኔ ታጣቂዎች እየተደበደበ ወዳልታወቀ እስር ቤት መወሰዱ ተሰማ::

አብረሃ ደስታ ዛሬ ከሰሃት በዋላ ከሚኖርበት መቀሌ ከተማ በፌደራል ፖሊሶች ወዳልታወቀ ቦታ መወሰዱን ምንጮች ጠቁመዋል::  ውጥረቱ በተለያየ አቅጣጫ እየጨመረ ከመምጣቱ የተነሳ የወያኔ ባለስልጣኖች የተደናገጡ ይመስላል   በዛሬው ቀን  በቻ ወደ አራት የሚሆኑ የተቃዋሚ ኣመራሮች በወንበዴ መንግስት መያዛቸው ይታወቃል በዛሬው ቀን የሰማያዊ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆነው አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ የአንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የህዝብ ግኑኝነት ኃላፊ የሆነውና በቅርቡ ሐገርና ፖለቲካ የሚል መጽሐፍ ለንባብ ያበቃው ወጣቱ ፖለቲከኛ አቶ ሐብታሙ አያሌው ታስረዋል። የፖለቲካ ታጋዮችን በማሰር ትግሉን ማኮላሸት አይቻልም፡፡ነጻነት የናፈቀን ኢትዮጵያኖች በምንችለው መንገድ ሁሉ ወያኔዎችን እረፍት መንሳትን እንቀጥል የ ሃያ ሶስት ዓመት የጭቆና አገዛዝ ይበቃል::  የወያኔ መንግስት እጅግ ወደ ለየለት ውንብድና የገባ ይመስላል ሁኔታው በጣም አሳሳቢ ከመሆኑ የተነሳ ከጣዩን ነገር እጃችንን አጣምረን ከመጠበቅ ይልቅ ወደ ቀጥተኛ ትግል በተባበረ ክንድ መነሳትና የወንበዴ መንግስትን መጣል አለብን።

No comments: