Wednesday, July 9, 2014

ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ የጀመረው እስር የ2007ን ምርጫ ጠቅልሎ ለመውሰድ ያደረገው መጀመሪያው ርምጃ ነው!!! (አንድነት ፓርቲ )

July9/2014
የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌው እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እናሳስባለን!!!

ከአንድነት ፓርቲ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በቅርቡ ለህዝቡና ጋዜጠኞች ይፋ እንዳደረግነው ሕወሓት/ኢህአዴግ  ለአለፉት 23 ዓመታት ወደር የሌለው የዴሞክራሲያዊ መብት ገፈፋና የሰብአዊ መብት ረገጣ በዜጎች ላይ ሲፈጽም መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው እውነ ታመሆኑን፤በአሁኑ ወቅት ይህ የሰብአዊ መብት ረገጣና ድፍጠጣበእጅጉተባብሶወደመንግሥታዊየውንብድናናጥቃትመቀየሩን፤ ዜጎችመንግሥትእንዳሰማራቸው የምንጠረጥራቸው የደህንነት ኃይሎች ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በጅምላ መታሰራቸውን፣ መደብደባቸውንና በስውር እስር ቤቶችተወርውረውደብዛቸውእንዲጠፋመደረጉን ገልፀን ነበር፡፡ እንደዚህ አይነቱ ውንብድና ደግሞ ምርጫ ሲቃረብና የፖለቲካ ፓርቲዎች መሰባሰብ ብሎም መዋሃድ ሲገለፅ ተጠና ክሮ የሚቀጥል እንደሆነ ከዚህ በፊት በውዱ ታጋያችን አንዱአለም አራጌ እና ሌሎችም ያስተዋልነው የገዥው ፓቲ ድርጊት ነው፡፡

ለባለፉት 23 ዓመታት ሲያደርገው እንደነበረው ሁሉ ምርጫ ሲደርስ የሚጨነቀው ገዢ ፓርቲ አባሎቻችንን መደብደብና ማሳደዱ አልበቃ ብሎት በምርጫው ዋዜማ በተለመደውና አሰልቺ ፍረጃው ተደግፎ አመራሮቻችንን ማሰር ጀምሯል፡፡ ፓርቲያችን እንደሚረዳው ይሄው በዛሬው ዕለት እንደገና የተጀመረው የአንድነት የስራ አስፈፃሚ አባልና የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ሀብታሙ አያሌውን እና የምክር ቤት አባልና የድርጅት ጉዳይ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺን በማሰር እና በርካታ አባሎቻችን ላይ አፈና በማካሄድ የምርጫ ዘመቻውን ይፋ አድርጓል፡፡ ፀረ-ውህደት አቋሙን አንፀባርቋል፡፡

ይሄው እስር እንደተለመደው የተቀነባበረ የስርዓቱ ድራማ ከመሆኑም በተጨማሪ የ2007ን ሀገራቀፍ ምርጫ በተለመደው ማሸማቀቅና ማወናበድ ለመውሰድ የተጀመረ የመጀመሪያ ርምጃ ነው ብለን እናምናለን፡፡ የተቀነባበረ ድራማም በሚቆጣጠራቸው ስማቸው የህዝብ ተግባራቸው ግን የፓርቲ መገልገያ በሆኑ ሚዲያዎች ማቅረቡንም እንደሚቀጥልም እናውቃለን፡፡ ይህ ሁሉ ግፍና ድራማ የሚከናወነው ከአፍ ባለፈ መተግበር ያልቻለውን ዴሞክራሲያዊ ስርኣት ለማስመሰያነት ለመጠቀምና የቀጣዩን ዓመት ምርጫ በለመደው ሁኔታ ከቻለ አስሮና አደናግሮ ካልተጫለ ጉልበቱን ተጠቅሞ ለመጠቅለል ነው፡፡

ፓቲያችንአንድነት አባላትንና አመራሮቻችን በማሰቃየትና በማሸማቀቅ፣ በመደብደብ የአካል ማጉደል ጉዳት በማድረስ የሚያደርገውን አስነዋሪ ተግባር እያወገዘ የፓርቲያችን ከፍተኛ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌው፤ አቶ ዳንኤል ሺበሺና ሌሎችም በፖለቲካ አመለካከታቸውና እምነታቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እናሳስባለን፡፡ በተጨማሪም በተቃውሞ ጎራ የተሰለፉ ፓርቲዎችም ይህን ህገ ወጥ እስር በማውገዝ እንዲሁም ኢ-ፍትሀዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚደረገውን ሩጫ በመቃወም እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንቆም እየጠየቅን ይህንን ህገ-ወጥነት በህዝባዊ ንቅናቄ ለማሸነፍ በምናደርገው ትግል በጋራ እንድንሰራ ሀገራዊና ወቅታዊ ጥሪ እናቀርባለባለን፡፡ የሲቪክ ተቀቋማት፤ ነፃው ሚዲያና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶችም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን መንግስታዊ ግፍና በደል በዓለማቀፍ ደረጃ በማጋለጥ ግዴታችሁን እንድትወጡ እናሳስባለን፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ስለሰብዓዊ መብት መከበርና ዴሞክራሲ መረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ተግል በመደገፍ የአምባገነኖችን ውድቀት እንዲያፋጥን ሀገራቀፍ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

                                              ትግላችን እስከ ነፃነት ይቀጥላል!!!  
                                            አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)
                                                       ሐምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም

No comments: