Wednesday, July 30, 2014

6000 አዳዲስ የደህንነት አባላት ስልጠና እየተሰጣቸው ነው።

July 30/2014
ለብአዴን አባላት እድሉ አልተሰጣቸውም።
ምንሊክ ሳልሳዊ
በቀጣዩ ጊዜያት የግንቦት ሰባት የተባለው የተቃዋሚ ቡድን በሃገር ውስጥ ሰርጎ በመግባት ከፍተኛ የሆነ የከተማ ውስጥ መስፋፋት ይፈጥራል ጥቃት ያካሂድብናል በሚል ስጋት መነሾ ጭንቀት ያደረበት የወያኔው ጁንታ ከመቀሌ እና ከደቡብ እንዲሁም የተወሰኑ ከኦሮሚያ ክልል የተወጣጡ 6000 አዳዲስ የደህንነት አባላት በአዋሳ በደብረዘይት እና በአዲስ አበባ ለሶስት ተከፍለው ስልተና እየተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል።የኢሕአዴግ አንዱ ክፍል እንደሆነ ለሚትወቀው የብኣዴን አባላት እና ካድሬዎች በዚህ የደህንነት ስልጠን ላይ እንዲሳተፉ እድሉ አልተሰጣቸውም።

በቀጣይነት ግንቦት ሰባት እና ተባባሪዎቹ የሚወስዱት እርምጃ ስጋት የሆነበት ወያኔ የሚያሰለጥናቸውን የደህንነት አባላቱን በሃገር ውስጥ በሚገኙ የተመዘገቡ የተቃዋሚ ድርጅቶች መዋቅር ውስጥ እና በኢሕአዴግ የወረዳ መዋቅሮች ውስጥ በማቀናጀት እንደሚመድባቸው እና እንዲሁም በጎረቤት አገራት በድንበር ከተሞች እና በዋና ዋና ከተሞች እንደሚመደቡ የህብረተሰቡን እንቅስቃሴ እና የግንኙነት መረብ በማጥናት መረጃ በመሰብሰብ ሪፖርት እንደሚያደርጉ ታውቋል።

ከዚህ ቀደም በዚህ የደህንነት መዋቅር ስራ ላይ የተመደቡ የወያኔ አባላት ይህን ያህል የሚያረካ ውጤት እና መረጃ ካለማምጣታቸውም በላይ አሁን ከሚመደቡ ጋር በጋራ እንዲሰሩ እንደሚደረግ ታውቋል።

No comments: