Thursday, January 2, 2014

የአንድን ህብረተሰብ ችግር የመረዳትና መፍትሄ የመፈለግ ጉዳይ (ከፈቃዱ በቀለ)

January2/2014

መግቢያ
በመጀመሪያ ደረጃ ውድ አቶ ካሳሁን ነገዎ ታዋቂ ሰዎችን ወይም ምሁሮችን ለቃለ-መጠይቅ እያቀረበ አስተያየታቸውንና አመለካከታቸውን እንድናዳምጥና ትምህርት እንድንቀምስ የሚያደርገው ጥረት የሚያስመሰግነው ነው። 

በዚህም መሰረት በአ.አ በ23.12.2013 ዓ.ም ዶክተር ብርሃኑ ነጋን በቅርቡ ለዕትመትና ለንባብ ባበቃው፣ „ዲሞክራሲና 
ሁለንታዊ ልማት“ በተባለው መጽሀፉ ዙሪያ ምን ማለቱ እንደሆነ ለቃለ-መጠይቅ ጋብዞት አንዳንዶቻችን ለማዳመጥ 
ችለናል። የቃለ-መጠይቁን ምልልስ በጥሞና ላዳመጠ የዶክተር ብርሃኑ ነጋ መልስ ግልጽና ብዙም የሚያከራክር ጉዳይ 
አይደለም። 

 እንደ ዕውነቱ ከሆነ አዲሱን የዶክተር ብርሃኑ ነጋን መጽሀፍ ለማግኘት ስላልቻልኩና ስላላነበብኩት ስለመጽሀፉ 
ጥሩና መስተካከል ይገባቸዋል ብዬ በማምነው ላይ ገንቢ ትችት መስጠት አልቻልኩም። መጽሀፉን አግኝቼ ከአነበብኩት 
በኋላ አስተያየቴን ለመስጠት እሞክራለሁ። ወደ ቃለ-መጠይቁና ምልልሱ ጋ ስንመጣ ከጠያቂው በቀረበለት ጥያቄ ዙሪያ 
የህብረተሰብአችንን ችግሮች በአጠቃላይ ሲዳስስ፣ መጽሀፉን በመመርኮዝ በተለይም በሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ 
እንዳተኮረ ተናግሯል። እነዚህም፣ 1ኛ) የፖለቲካ ችግሮች፣ 2ኛ) የኢኮኖሚ ችግሮችና፣ 3ኛ) የአካባቢ ችግሮች በሚሉት 
ዙሪያዎች ሰፊ ማብራሪያ ለመስጠት ሞክሯል። በተለይም ለቃለ-መጠይቁ ክብደት የሰጠው የፖለቲካው ላይ ስለሆነ በዚህ 
ላይ እሱ በሚመስለው መንገድ ለማብራራት ጥሯል። በእርግጥ ዶክተር ብርሃኑ በትክክል እንዳስቀመጠውና እኛም መቀበል ያለብን፣ እሱ ለንባብ ያቀረበው መጽሀፍ ለውይይት የቀረበና፣ ሰፋ ያሉትን የህብረተሰብአችንን ችግሮች በውይይትና በሂደት ለመፍታት በማመን ብቻ ነው። በእርግጥም የሚያስመሰግነው ነው ።

No comments: