Monday, January 20, 2014

ጡት የሚያሳይ፣ በሕዝብ ገንዘብ የተሰራ ሃዉልት !

January20/2014
የኦሮሚያ ክልል የቱሪዝምና ባህል ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሞሃመድ ጂሊ፣ የአኖሌ ሃዉልት እንደተሰራና በመሰራቱም ትልቅ ኩራት እንደሚሰማቸው፣ ገዛ ተጋሩ በተባለ የፕላቶክ ክፍል ቀርበው ገለጹ።
የአጼ ሚኒሊክ ወታደሮች በአርሲ የሴቶችን ጡት ቆርጠዋል የሚባለዉ ወሬ፣ የቀድሞ የሕወሃት ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አቶ ተስፋዬ ገብረ አብ በጻፉት መጽሃፍ ከመጻፉና በአንዳድን አክራሪ የኦሮሞ ድህረ ገጾች ላይ ከመዉጣቱ መቀር፣ በታሪክ ባለሞያዎች የተደገፈ፣ ተፈጸመ የተባለውን መፈጸሙን የሚይሳይ መረጃ እስከአሁን አልቀረበብም።
ሆኖም የኦሮሚያ ክልል መንግስት፣ ዉሸት ሊሆን የሚችል ወሬን ተመርኩዞ ፣ በትክክል በተረጋገጠዉ በበደኖ እና አርባ ጉጉ፣ በተፈጸመ ግፍና ጭካኔ ዙሪያ ማስታወሻ ሃዉልቶች ሳይሰሩ፣ በሕዝብና በሕዝብ መካከል ጥላቻ ሊያሰፍን የሚችል፣ የሴት ልጅን ጡቱ የሚያሳይ ሃዉልት በአርሲ መሰራቱ ፣ ብዙዎችን እያነጋገረ ነዉ። በበደኖ በኦነግ ታጣቂቶች ነፍሰ ጦር ሴቶች ሁሉ ሳይቀሩ፣ በሕይወት አይኖቻቸውን ተሸፍነዉ የጠልቀ ገድል ዉስጥ እንዲወረወሩ መደረጉ የሚታወቅ ነዉ። በተመሳሳይ ሁኔታ በኦህዴድ.ኢሕአዴግ ታጣቂዎች አቀነባባሪነት፣ በአርባ ጉጉ አርሲ በርካታ ዜጎች በተኙበት ቤታቸው እንዲቃጠል ተደርጎ አልቀዋል።
አንዳንድ የኢሕአዴግ ደግፊዎች፣ «የኦሮሚያ ክልል ራሱን በራሱ የሚያስተዳደር ነዉ። ፌደራል መንግስት እዚህ ዉስጥ ጣልቃ አይገባም። ነበገሩም የለበትም። ክልሉ እንጂ» በማላት ሃላፊነት ላለመዉሰድ እየሞከሩ ነዉ።
«በተለይም የአርሲን ሕዝብ ጨምሮ፣ መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከድህነት ጋር እየታገለ ባለበት ወቅት፣ በሚሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ፣ ከሕዝብ ካዝና ተሰብስቦ፣ ይህ ሃዉልት መሰራቱ፣ ኢሕአዴግ/ኦሕደድ ምን ያህል ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌለ፣ ወደፊት ከመሄድ ይልቅ ዜጎችንም ወደኋላ እየጎተተ እንደሆነ የሚይሳይ ነዉ» ሲሉ የገለጹት አንድ የፖለቲካ ተንታኝ፣ ኢትዮጵያዉያን በተለይም ኦሮሞ ነን የሚሉ ከበስተጀርባ ያለዉን ተንኮል እንዲያስተዉሉ መክረዋል።
ኦሕደድ እና በዉጭ እየጮሑ ያሉ አክራሪዎች፣ ኦሮሞዉ በተቀረዉ ሕዝብ እንዲጠላ እያደረጉት ነዉ » ያሉት እኝህ ተንታኝ፣ የኦሮሞዉ ማህበረሰብ በአካባቢዉና አብረዉት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ጋር እድሉ የተሳሰረ እንደይሆኑ፣ የሚያፋቅርና የሚያሰባስብን አጀንዳ የሚያራምዱትን እንጂ፣ አካራሪዎች ማስተናጋድ እንደሌለበት ይናገራሉ።
በአርሲ፣ በሕዝብ ገንዘብ የተሰራዉን ጡት የሚያሳይ ሃዉልት ይመልከ 

No comments: