Tuesday, January 14, 2014

የመከላከያ መኮንኖች በአዲስ አበባ ፖሊስ የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው ተመደቡ:: ‪‬

January14/2014
"የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ እንደሚደረግ ምንም ጥርጥር የለውም "::
በአዲስ አበባ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት ተቀየሩ :: በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስሩ ክፍለ ከተሞች የመከላከያ መኮንኖች ተዛውረው መመደባቸውን ታማኝ የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የሕወሐት አባላት የሆኑትና ከመቶ አለቃ እስከ ሻለቃ ደረጃ ያላቸው የመከላከያ መኮንኖች የአዲስ አበባን ፖሊስ በበላይነት እንዲቆጣጠሩ በአስሩም ክፍለ ከቶሞች የመምሪያ ሃላፊ ተደርገው መሾማቸውን ምንጮቹ አስታውቀዋል።ከዚሁ ጎን ለጎን በአዲስ አበባ በሚገኙ ወረዳዎች “ኮሚኒቲ ፖሊስ” በሚል አዳዲስ የፌደራል ፖሊሶች እንደመተደቡ ምንጮቹ አያይዘው ገለፀዋል።
 በአዲስ አበባ ፖሊስ ሃይል እምነት ያጣው ገዢው ፓርቲ ሕወሐት/ኢህአዴግ ታማኝ በሚላቸው መኮንኖችና የፌደራል ፖሊሶች እየተካና አፈናውን እያጠናከረ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም አሁን በተጀመረው የክልሉን ፖሊስ የማፍረስ ተግባር በቅርብ ጊዜ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከጨዋታ ውጭ እንደሚደረግ ምንም ጥርጥር የለውም ብለዋል። 
ገዢው ፓርቲ ራሱ በደነገገው ሕገ-መንግስት ላይ ፖሊስ ፀጥታውን እንደሚቆጣጠር እንዲሁም መከላከያ ገለልተኛ ሆኖ የአገሩን ሉአላዊነት እንደሚጠብቅና ከማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት ነፃ ሆኖ እንደሚቆም አዋጁ የሚገልፅ ቢሆንም ነገር ግን ራሱ ላወጣው ሕገ መንግስት ተገዢ መሆን እንዳልቻለ የሕወሐት መኮንኖች ከመከላከያ ተዛውረው የአዲስ አበባን ፖሊስ በበላይነት እንዲመሩና እንዲቆጣጠሩ መመደባቸው የህግ ጥሰት እያካሄደ እንደሆነ በቂ ማስረጃ ነው ብለዋል ምንጮቹ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ ለጤና አገልግሎት የተሰሩ ክሊኒኮች ወደ እስር ቤትነት እየተቀየሩ መሆኑን ምንጮች አጋልጠዋል። በአዲስ አበባ የካና አራዳ ክፍለ ከተሞች “ኬርና ፕላን” በተባሉ ግብረሰናይ ድርጅቶች የተሰሩት ጤና ጣቢያዎች ወደ ፖሊስ ጣቢያነት ተቀይረው እስረኞች እየታሰሩባቸው መሆኑን አረጋግጠዋል። በየካ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 06/07 ቤላ፣ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ቀበሌ 11 እንዲሁም ጃንሜዳ ቀበሌ 05 የሚገኙ ጤና ጣቢያዎች በከፊል እንደሚጠቀሱ ያስታወቁት ምንጮቹ በተጠቀሱት ቦታዎች እስረኞች በብዛት ታስረው እንደሚገኙ አያይዘው ገልፀዋል።

No comments: