Thursday, January 2, 2014

ሰበር ዜና፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአቶ መላኩ ፈንታ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አስተላለፈ

Janaury 2/2014

በሙስና ወንጀል የተከሰሱት አቶ መላኩ ፈንታን ክስ መመልከት ያለበትን ፍርድ ቤት በሚመለከት ዛሬ የተወያየው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክሱ መታየት ያለበት በጠቅላይ ፍርድ ቤት መሆኑን ለማሳየት ተከሳሹ የጠቀሱት የፌዴራል ፍርድ ቤቶ ችአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 8 ንኡስ አንቀጽ 1 ከሕገ መንግሥቱ ጋር የሚጣረስ በመሆኑ ከሕገ መንግሥቱ ጋር እንዲጣጣም ሆኖ እንዲስተካከል በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ውሳኔው ስምንት ተቃውሞና ሁለት ድምፀ ተአቅቦ ተመዝግቦበታል፡፡
የአዋጁ ንኡስ አንቀጾች እንደሚያስረዱት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በሥልጣን ላይ ሳሉ ከሥራቸው ጋር በተያያዘ በሚያጠፉት ጥፋት የሚጠየቁት በጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው፡፡ ነገር ግን ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያደረገው ውይይት ባለሥልጣናቱ በዚህ መልኩ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚጠየቁ ከሆነ ጥፋተኛ ወይም ነፃ ቢባሉ እነሱ ወይም መንግሥት ይግባኝ የሚሉበት ዕድል አይኖርም፡፡ ይህ ደግሞ ሁለቱንም ወገን የሚጎዳና የይግባኝ መብትን የሚፃረር ነው፡፡
ፌዴሬሽን ምክር ቤት ዛሬ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት የአቶ መላኩ ክስ በጠቅላይ ፍርድ ቤት የመታየት ዕድል አይኖረውም፡፡

No comments: