Thursday, June 19, 2014

የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ጥናት ኢትዮጵያን ከዓለማችን ደሃ ሀገራት ከመጨረሻው ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡

June19/2014
 Multidimensional Poverty Index (MPI) የተባለውና የዓለማችንን 108 በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን የድህነት ደረጃ የፈተሸው የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲው ጥናት ኢትዮጵያን ከ108ቱ ሀገራት ከኒጀር ብቻ በልጣ ከመጨረሻው ሁለተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡ ደረጃው በትምህርት፣ ጤና እና የኑሮ ሁኔታ ላይ የሚያጠነጥኑ 10 መስፈርቶች ሲኖሩት ከ10ሩ መስፈርቶች አንድ ሦስተኛውን እንኳ ያላገኘን ደረጃው ዘርፈብዙ ደሃ (Multi-dimensionally poor)ሲለው፣ ከመስፈርቱ ዝርዝር ውስጥ አንድ ሦስተኛው ያህል የተሟላለትን ደግሞ ለኑሮ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉለት (Destitute) ይለዋል፡፡ በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ አጠቃላይ ህዝብ 87.3% ያህሉ ዘርፈብዙ ደሃ በሚለው ክልል ውስጥ ሲገኝ 58.1%ቱ ደግሞ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉለት (Destitute) በሚለው ክልል ውስጥ እንደሚገኝ የጥናት ውጤቱ ያስረዳል፡፡ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ውስጥ መሰረታዊው ነገር ያልተሟሉላቸው (Destitute) ዜጎቿን ቁጥር በመቀነስ ረገድ ጥሩ ውጤት ብታስመዘግብም ኢትዮጵያ አሁንም የ76 ሚሊየን ዘርፈብዙ ደሃ ህዝብ ሀገር ናት ይላል የጥናት ውጤቱ፡፡ ይህም ቁጥር በዓለማችን ካሉ መሰል በርካታ እጅግ ደሀ ሕዝብ ከያዙ ሀገራት ማለትም ከህንድ፣ ቻይና፣ ባንግላዴሽ እና ፓኪስታን በመቀጠል ኢትዮጵያ በ5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ የደረጃው ዝርዝር የገጠሪቱን ኢትዮጵያ አስመልክቶ 96.3% የገጠሪቱ ኢትዮጵያ ህዝብ በድህነት ውስጥ እንደሚገኝ ሲገልጽ በአንጻሩ ከከተማ ነዋሪው 46.4 %ቱ በድህነት ውስጥ እንዳለ ያስረዳል፡፡ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የሚስተዋለውን የድህነት ደረጃ አስመልክቶም በሶማሊያ 93% በኦሮሚያ 91.2% በአፋር 90.9 % በአማራ 90.1 % በትግራይ 85.4 % ህዝብ በድህነት ውስጥ እንዳለ ይገልጻል፡፡ ከተሞችንም በተመለከተ አዲስ አበባ ከሌሎች ከተሞች ይልቅ አነስተኛ ደሃ (20%)ያለባት ስትሆን ድሬዳዋና ሐረር ደግሞ አነስተኛ ደሃ በመያዝ በ54.9% እና በ57.9% ይከተላሉ፡፡

http://www.diretube.com/articles/read-ethiopia-ranks-second-poorest-country-in-the-world-%E2%80%93-oxford-university-study_5513.html#.U6Kj2_l_tSQ

Ethiopia ranks second poorest country in the world – Oxford University Study


No comments: