Friday, June 6, 2014

የደህንነት ኃይሎች በጋዜጣ አዙዋሪዎች ላይ እርምጃ መወሰድ ጀመሩ

June 6, 2014
 በቅርቡ ገዥው ፓርቲ የግሉን ሚዲያ ለማፈን እንዲያስችል ጋዜጣ አዙዋሪዎችና አከፋፋዮችን በጥቃቅንና አነስተኛ ለማደራጀት የሚያስችል አሰራር እንደጀመረ ታውቋል፡፡ በዚህ አሰራር መሰረት ገዥው ፓርቲን የሚተቹ ጋዜጦችና መጽሄቶች ከገበያ በማስወጣት በቀጣዩ ምርጫ የሚደርስበትን ጫና ለመቀነስ እንደፈለገም ሲነገር ቆይቷል፡፡
ይህ በአዙዋሪዎች ላይ ሊወሰድ የታቀደው እርምጃ ዛሬ አመሻሹ ላይ የጀመረ ሲሆን በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች ጋዜጣ አዙዋሪዎች በገዥው ፓርቲ የደህንነት ኃይሎች ታግተው አምሽተዋል፡፡ በእገታው ወቅት የደህንነት ኃይሎች ‹‹ለማዞር የተደራጃችሁበትንና ፈቃድ የተሰጣችሁበትን ወረቀት አምጡ›› በማለት ወደ ጣቢያ ሊወስዱዋቸው እንደነበርና አዙዋሪዎቹም ‹‹መደራጀት አይጠበቅብንም፣ ጣቢያም አንሄድም›› ብለው የደህንነቶቹን ትዕዛዝ መቃወማቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም መንግስት የሚተቹትን ጋዜጦችና መጽሄቶች እንዲያዞሩ እንደማይፈልግና እሱ በሚፈልገው እያደራጀ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ እርምጃው መጠነ ሰፊ መሆኑን የጠቆሙት ታጋቾቹ ‹‹መንግስት ይህንን ለመተግበርም በእኛ ብቻ ሳይሆን ጋዜጣ በምናስነብብባቸው ካፌዎች ላይም ጫና ተጀምሯል፡፡ ካፌዎቹ ለአንድ ሰው ከአንድ ጋዜጣ በላይ እንዳንሰጥና አንዳንዶቹም ጭራሹን እንዳናስነብብና እንዳንሸጥ እየከለከሉን ነው፡፡›› ያሉት አዙዋሪዎቹ እስካሁን ይወሰዳል የተባለው እርምጃ ዛሬ በግልጽ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡
Reading newspapers in Addis Ababa, Ethiopia

No comments: