Saturday, June 14, 2014

የሕዝብ ሃብቶች በመንግስት ወጪዎች ሰበብ ያለርሕራሔ በወያኔ ባለስልጣናት እየተዘረፉ ነው።

June14/2014
ሓገራችን በጥቂት አደገኛ የገዢው ፓርቲ ዘራፊዎች እጅ ወድቃለች።

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ የወያኔ መራሹ ጁንታ ያዋቀራቸውና በተቋምነት የሚታወቁ መስሪያቤቶች ውስጥ እየተፈጸመ ያለው አግባብ ያልሆነ ስልጣንን መከታ በማድረግ በትእዛዝ ብቻ ካለማረጋገጫዎች እና ካለምንም ቅድመ ዝግጅት በመስፋፋቱ ከፍተኛ ዘረፋ እየተካሄደ ነው።በየተቋማቱ የሚደረጉ የበጀት ምደባዎች፤ኮንትራቶች ፤የንብረት ግዢዎች፤ ጨረታዎች ፡የውጪ ምንዛሬ እንቅስቃሲዎች እና የተለያዩ ወጪዎች አገሪቷ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት በማስከተል የኑሮ ውድነት እንዲስፋፋ እያደረጉ ነው።ይህ ዘረፋ ተቆጣጣሪ አካላት ማጣት የዘመድ አዝማድ የውስጥ አሰራር እና ግንኙነት በፓርቲ ባለስልጣናት መካከል የተፈጠረ አለመተማመን እና መፈራራት አገሪቷ በጥቂት አደገኛ ዘራፊዎች እጅ እንድትወድቅ ሆኗል።
የወያኔው መንግስት በተለያዩ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር በማድረግ በግብር እና በቀረጥ ስም እየበዘበዛቸው ቢሆንም የመንግስት በጀት ተብሎ የተመደበ ሲባክን አገልግሎት ላይ ሳይውል ሲቀር አላስፈላጊ ግዢዎች ተደርገው ብክነት ሲታይ ዝምታን በመምረጥ በሃገሪቱ ከፍተኛ የሙስና ተግባራቶች እንዲስፋፉ እድል ከፍቷል። ሙሰኞችን ጸረ ሙሰኞችም የተወሰኑ ባለስልጣናት በሆኑባት ኢትዮጵያ የሚደረገውን ብዝበዛ ለመሸፋፈን በተለያዩ የፖለቲካ ስውር እጆች ብክነት እና ብዝበዛን በማስፋፋት ህዝብ በኑሮ ውድነት እንዲደናቆር አድርገዋል።
ከስራ አፈጻጸም ጋር የማይዋሃዱ የማይገናኙ እና የማይመጣጠኑ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚመደቡ በጀቶች ውጤት አልባ ለሆኑ ጉዳዮች ከፍተኛ ውጪ በመመደብ - ለስብሰባ- ለነዳጅ-ለሆቴል-ለመኪና ግዢ-ለአልተፈለገ ድግስ- ለፊልድ አበል -ወዘተ እየተባለ አላስፈላጊ እና የማይመጥን ወጪ በማውጣት የወያኔ ባለስልጣናት የህዝብን ሃብት ካለመራራት እየበዘበዙት ይገኛሉ። ባለስልጣናቱ ወደ ባንኮች በመሄድ በመደወል በጥቅም በመተሳሰር ከተለያዩ የንግድ ድርት ባለቤቶች እና ከባንክ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር የውጪ ምንዛሬ በማውጣት የሃገሪቷን ካዝና በባዶ ለማስቀረት ሌት ከቀን እየሰሩ ሲሆን እንዲሁን ይህንን የዶላር ምንዛሬ ለማግኘት ለሚፈልጉ ነጋዴዎች በአንዱ ዶላር ሁለት ብር ጉቦ በማስከፈል ስልታናቸውን ለከፍተኛ ብዝበዛ እየተተቀሙበት ነው።
ስልጣናቸውን ያለአግባብ የሚጠቀሙት የወያኔ ሰዎች ከውጪ ሃገር በግዢ እንዲመጡ የሚወሰንባቸውን የተቋማት የሕዝብ ንብረቶች ጨረታዎች በሙሉ በከፍተኛ የሙስና ትሥሥር የሚፈጸሙ ናቸው። በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ከውጪ የተገዙ የተቋማት ንብረቶች ከሙስና የጸዱ እንዳልሆኑ እና በጥቅማጥቅም ውህደት በኮሚሽን የተገዙ እንደሆነ ማረጋገጫዎች በገሃድ እያየናቸው ነው፤ጨረታ የሚለውን ቃል እንደ ህጋዊነት በመጠቀም በመጠኑ አስደንጋጭ የሆነ ኮሚሽን በመያዝ የሃገር እና የህዝብ እየተበዘበዘ ሲሆን በዚሁ የኮሚሽን እና የጉቦ ትሥሥር ከተለያዩ አገሮች የሚገዙ ንብረቶች የተበላሹ እና የሚቀላልጡ ውጤት አልባ በመሆናቸው ምንም ሳይሰራባቸው በየቦታው እንደቆሙ እና እንደወዳደቁ ሲቀሩ ባለስልጣናቱ ሙስናቸውን በመቀጠል ተቆጣጣሪ አልባ ስለሆኑ ወደ ሌላኛው ብዝበዛቸው ይሻገራሉ። ይህ አደገኛ ዘረፋ በብዙ መልኩ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ዘረፋዎች እየተካሄዱ ነው በሂደት እያየነው እንሄዳለን ።

No comments: