Friday, June 6, 2014

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በጨለማ ክፍል መታሰራቸው ተሰማ

June 6/2014
በአቡ ዳውድ ኡስማን -
(ድምጻችን ይሰማ እንደዘገበው)

በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በሃሰት በሽብርተኝነት ተወንጅለው በእስር የሚገኙት ኮሚቴዎቻችንን የማረሚያ ቤቱ አስተዳር ሆን ብሎየማሸማቀቅ እና የማዋከብ ተግባር እየፈፀመባቸው እንደሚገኝ መዘገባችን ይታወቃል:: በማረሚያ ቤቱ ከሚገኙ ህግ ታራሚዎች እና እስረኞች በተለየ መልኩ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በኮሚቴዎቻችን አመራሮች እና አብረዋቸው በታሰሩት ወንድሞች ላይ ትኩረት በማድረግ አቃቂር የ መፈለግ እና ባገኙትም ነገር ጉዳዩን በማግነን ለማሸማቀቅ እና ለማንገላታት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አቶ አምባዬ እና የደህንነት ሃላፊ አቶ ኤርሚያስ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸወየተገለፀ ሲሆን ሲዝቱባቸው በነበረው መሰረትም የህዝበ ሙስሊሙን መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ኡስታዝአቡበከር አህመድን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በኮሚቴዎቻን እና በወንድሞቻችን ላይ ልዩ ክትትል በማድረግ በጨለማ ክፍ ውስጥ እንዲሰቃዩ ለማድረግ ከበላይ የደህንንትአካላቶች ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ድንገተኛ ፍተሸ በማድረግ ማንኛው እስረኛ ጠያቂዎች ሊሰጡት የሚችሉትን ገንዘብ ይዛችሁ ተገኝታቹሃል በሚል ኡስታዝ አቡበከር አህመድን እና ሼህ መከተ ሞሄን የማስፈራራት እና ቃላቸውን እንዲሰጡ የማድረግ እንቅስቃሴ ሲየደርጉባቸው ቆይተዋል፡፡በትላንትናው ዕለት ሃሙስም ኡስታዝ አቡበከር አህመድን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰር ማድረገቻውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ከሌላ እስረኞች በተለየ ሁኔታ ኮሚቴውን የማዋከቡ እና በጨለማ ቤት ለመቅጣት የማስፈራቱ ድርጊታቸው ህገ ወጥ መሆኑን ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ለማረሚያ ቤቱ ደህንነት ሃላፊዎች ሲያሳስቡ ቢቆዩም የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ግን ኡታስዝ አቡበከርን በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዲታሰር ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከህግ እና ክፍርድ ቤቱ ተዕዛዝ ሁሉ የበላይ በሆኑ የደህንነት ሃይሎች በኮሚቴዎቻችን አመራሮች ላይ እና በተወሰኑ ወንድሞች ላይ እየተደረገ ባለው ጥብቅ ክትትል እና የዚህ መሰሉ የጨለማ ቤት ቅጣት የሚፈፀም ከሆነ ኮሚቴዎቸችን ለፍርድ ቤቱ እያቀረቡ የሚገኙትን የመከላከያ ምስክር እስከማቆም ሊደርሱ እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ ህግ ተፅፎ ባለበት ሃገር ህጉ እየተጣሰ ንፁሃን እንዲንገላቱ መደረጉ የፍርድ ቤቱን ሚና ከቁብ የማያስገባ መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ በችሎቱ የመቀጠሉ ሁኔታ አጠያያቂ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡

ሼህ መከተ ሞሄ እና ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ላይ በጨለማ ክፍል አስገብተው እንደሚቀጧቸው የማረሚያ ቤቱ ሃላፊዎች ሲዝቱባቸው የቆዩ ሲሆን ዛቻቸውን በተግባር በመለወጥ በጨለማ ክፍል ውስጥ እንዳስገቧቸው ታውቋል፡፡
ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እየተፈጸመባቸው የሚገኘውን ህገ ወጥ ተግባር ለፍርድ ቤቱ ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ኡስታዞቻችንን እና ወንድሞቻንን አላህ ይጠብቅልን!!!

No comments: