Saturday, June 28, 2014

የሙስሊሙን ትግል ለማኮላሸት የታቀደ ስብሰባ በሽመልስ ከማል ቢሮ ተካሄደ።

June 27/2014
ምንሊክ ሳልሳዊ
የቀድሞዋ አልቁድስ አዘጋጆችም ከአቶ ሽመልስ ከማል ጋር መፈራረማቸውን ለማወቅ ተችልዋል፡፡
የሙስሊሙን ትግል አስመልክቶ በኮሚኒኬሽን ሚኒስትሩ አቶ ሽመልስ ከማል ቢሮ በትላንትናው እለት ደህንነቶች የመጅሊስ ሰዎች : የሱመያ ጋዜጣ አዘጋጆች የተመለመሉ ወጣቶች ስብሰባ አድረገው እንደነበር ምንጮቻችን ለቢቢኤን ገለጹ፡፡ በዛሬው የጁምአ ተቃውሞ ለማሰር አቅደውት የነበረውም ዝናብ በመጣሉ ምክኒያት እንደተኮላሸባቸው ታወቀ፡፡
በትናንትናው እለት ምሽት በአቶ ሽመልስ ከማል ቢሮ ውስጥ በነበረው ስብሰባ በሙስሊሙ ማህበረሰብ ትግል ላይ ውዥንበር ለመፍጠር ታቅዶ በቀድሞው አልቁድስ ጋዜጣ አዘጋጆች የተዘጋጀችው በድር ጋዜጣ ተብሎ ታትሞ አጀንዳው ስለታወቀ ስምዋን የቀየረችውን አሁን ሱመያ በሚል መታተሙዋ ተገልጸዋል፡፡ የሙስሊሙ ትግል ደጋፊ በመምሰል ክፍተት ለመፍጠር ከመንግስት በጀት የተመደበላቸው የቀድሞዋ አልቁድስ አዘጋጆችም ከአቶ ሽመልስ ከማል ጋር መፈራረማቸውን ለማወቅ ተችልዋል፡፡
በአዲስ አበባ ያለው ሙስሊም ማህበረሰብ በድር ጋዜጣም ሆነ ሱመያ ጋዜጣ ትግሉ ለማዳከም የተዘጋጀ መሆኑን ስላወቀ ተቀባይነት እንደሌለው የተረዱት የመንግስት ባለስልጣናትና አዘጋጆቹ ጋዜጣዋን ወደ ክፍለ ሀገራት ለመበተን እንዳቀዱም በዚሁ ስብሰባ ላይ አውሰተዋል፡፡ ጋዜጣዋን ክፍለ ሀገር ሂዶ ለማከፋፈል ለሚፈልጉ ወጣቶችም ስልጠና እንደሚሰጣቸውና ዳጎስ ያለ አበልም እንደሚተሳብላቸው በዚሁ ስብሰባ ላይ ተግልጽዋል
ተቃውሞው በምንም ተአምር መቀጠል የለበትም ለዚህ ሁላችንም ርብርብ ማድረግ አለብን ሲሉ አሳስበዋል አቶ ሽመልስ ከማል፡፡ ስልጠና ከወሰዱ በሁላ ጥለው የወጡት ወጣቶች እንደገና ተጠርተው ሰዎችን በማሳሰር በደህንነት መሰማራት እንዳለባቸውም ተገልጽዋል፡፡

ቢቢኤን የናንተው ድምፅ ሌሎችንም የዚህን ስብሰባ ተጨማሪ መረጃ ለመስማት ቀጣዩን ሊንክ ይክፈቱ -http://goo.gl/VwQJzy
http://goo.gl/VwQJzy

No comments: