Friday, January 10, 2014

አቶ ያረጋል አይሸሹምን ጨምሮ 6 ግለሰቦች ከ6 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራተ ተቀጡ

January 10/2014

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በጨረታ ሂደት የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው 6 ግለሰቦች ዛሬ ከ 6 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራተ ተቀጡ .

ተከሳሾቹ አቶ ያረጋል አይሸሹም የቀድሞ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ዳይሬክተር , የክልሉ የትምህርት ቢሮ ሃላፊና የክልሉ ምክር ቤቱ አፈጉባኤ የነበሩት አቶ ሀብታሙ ሂካ , አቶ ጌድዮን ደመቀ የጌድዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ባለቤትና ስራ አስኪያጅ , አቶ አሰፋ ገበየሁ የአቶ ጌድዮን አማካሪ , አቶ ገዛኧኝ አድገና አቶ መክብብ ሞገስ በስራ ተቋራጭነት የሚሰሩ ናቸው :: 

                          አቶ ያረጋል አይሸሹም

በ1997 ዓ . ም ከክልሉና ከፌደራል መንግስት በተገኘ የ 79 ሚለየን ብር በጀት የአሶሳ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ , የግልገል በለስ ማሰልጠኛ ኮሌጅና የጣና በለስ ሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት የማስፋፊያ ግንባታ ፕሮጀክት እንዲከናወን አቶ ያረጋል አይሸሹም የሚመሩት የክልሉ ካቢኔ ይወስናል ::

በግልፅ ጨረታ ወጥቶ ተጫራቾች ተወዳድረው ግንባታው መከናወን ሲገባው : ባልተገባ መንገድ 1 ኛ እና 2 ኛ ተከሳሽ በፈጠሩት የጥቅም ትስስር ; የጌድዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት እንዲያሸንፍ ይደረጋል ::

የክልሉ መንግስት የግዥ ስርዓት መመሪያ ከ 300 ሺህ ብር በላይ የሆነ ግዥ ሲፈፀም የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ማፅደቅ አለበት ይላል ::

ከተከሳሾቹ አቶ አቶ ያረጋል አይሸሹምና አቶ ሀብታሙ ሂካ ከባለሃበቶቹ ጋር በመመሳጠር ጌድዮን ደመቀ አማካሪ ድርጅት ያለግልፅ ጨረታ እንዲያሸንፍና ሶስቱንም ፕሮጀክቶች እንዲያሸንፍ ይደረጋል ::

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከ 5 ሚልየን ብር በላይ ተጨማሪ ክፍያ ተጫራቹ እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን : በ 13 ወራት ይጠናቀቃል ተብለው ውል የተገባባቸው ፕሮጀክቶች ከ 5 ዓመት በላይ አስቆጥረዋል ; ጨረታውን አሸነፈ የተባለው ድርጀትም በህገወጥ መንገድ እንዲያሸንፍ ከመደረጉም በላይ ደረጃው ፕሮጀክቶቹን ለመገንባት የሚያስችል አለመሆኑም በክስ መዝገቡ ተጠቅሷል ::

የፌደራል ስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግ አቶ ያረጋል አይሸሹምና አቶ ሀብታሙ ኢካን ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ሌሎች ባለሀብቶችን ደግሞ በመመሳጠር በዚህ ወንጀል በመሳተፋቸው ከሷቸዋል ::

እንዲከሰሱ ካስቻሏቸው ነጥቦች መካከል በ 13 ወራት ይጠናቀቃል ተብለው ውል የተገባባቸው ፕሮጀክቶች ከ 5 ዓመት በላይ መጋተታቸው , በተጨማሪ 7 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ለተቋራጩ መከፈሉ , እነዚህ ባላሀብቶች በተለያየ ጊዜያት ለአቶ አቶ ያረጋል አይሸሹምና አቶ ሀብታሙ ሂካ ጉቦ መስጠታቸው , የጨረታ መመሪያ ደንብ በመጣስና በሌሎች ተያያዥ ጭብጦች ናቸው ::

መዝገቡን ሲመረምር የቆየው የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15 ኛ ወንጀል ችሎት ባለፈው ህዳር November 2006 አቶ ያረጋል አይሸሹም , አቶ ገዛኧኝ አድገና አቶ መክብብ ሞገስን በአቃቤህግ ከተመሰረተባቸው ክሶች በአንድ ብቻ ጥፋተኛ ናቸው ሲል : አቶ ሀብታሙ ኢካ , ጌድዮን ደመቀና አቶ አሰፋ ገበየሁን በ 3 ክስች ነበር ጥፋተኛ ያላቸው ::

በዚህ መሰረት ዛሬ ከሰዓት ችሎቱ የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ ከግምት በማስገባት አቶ አቶ ያረጋል አይሸሹምን በ 7 በ 20 ሺህ ብር , አቶ ሀብታሙ ኢካን በ 15 በ 45 ሺህ ብር , አቶ አሰፋ ገበየሁን በ 15 ዓመት ፅኑ እስራትና 60 ሺህ ብር , አቶ ጌድዮን ደመቀን 14 ዓመት ፅኑ እስራትና 60 ሺህ ብር , አቶ ገዛኧኝ አድገና አቶ መክብብ ሞገስን እያንዳንዳቸው በ 6 ዓመት ፅኑ እስራትናመት ፅኑ እስራትና በ 25 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል ::

በመዝገቡ በ 7 ኛ ተራ ቁጥር ተጠቅሶ የነበረው የአቶ ሀብታሙ ኢካ ወንድም አቶ ሀብተገብርኤል ኢካ ህዳር 11, 2006 ዓ . ም በዋለው ችሎት በብይን በነፃ መለቀቁ ይታወሳል ::

No comments: