Thursday, January 2, 2014

ሄንከን የቴዲ አፍሮን ኮንሰርት መሰረዙ ተሰማ

January2/2014


መሳይ መኮንን (ጋዜጠኛ)
አሁን የደረሰኝ መረጃ ነው። የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለሄንከን ኩባንያ የጸጥታ ዋስትና እንደማይሰጠው በመግለጹና ቀጥተኛ ጫና ከመንግስት በመምጣቱ ሄንከን የፍቅር ጉዞ ኮንሰርትን መሰረዙን ለማወቅ ተችሏል። ባለኝ መረጃ መሰረት ቦይ ኮት በደሌ ዘመቻ ያልፈታው ሄንከን በመንግስት ማስፈራሪያ ኮንሰርቱን ለመሰረዝ ተገዷል። የጃዋር ዘመቻ ተሳክቷል ማለት የሚቻል አይመስለኝም። ምክንያቱም ኦህዴድ በቀጥታ እጁን ማስገባቱን የሚያሳዩ በርካታ መረጃዎች አሉ። በአንድ ሀገር መንግስት እያለ የጸጥታ ዋስትና አልሰጥም ብሎ ከማስፈራራት በላይ ምን ክልከላ አለ? ለእኔ ከእነጃዋር ዘመቻ ይልቅ የመንግስት ማስፈራሪያ ለኮንሰርቱ መሰረዝ ብቸኛው ሰበብ ምክንያት ሆኖ ይታየኛል::

No comments: