Thursday, April 11, 2013

ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የ አማራ ተወላጆችን አሁንም ለተጨማሪ ጥፋት እያዘጋጀ መሆኑ ታወቀ

ለረጂም ዘመናት ከ አካባቢው ህብረተሰብ ጋር ተዋደውና ተግባብተው ይኖሩ የነበሩ የ አማራ ተወላጆችን ኢ ሰብ ዊ በሆነ መንገድ እንዲፈናቀሉና በሰላምም ይኖሩበት ከነበረው ህበተስብ ጋር ግጭትና እንዲፈጥሩ ያደረገው ዘረኛ አገዛዝ እነኝህን ተፈናቃዮች እንደገና በመመለሱ ለሌላ ጥፋት እየተዘጋጀ መሆኑን ዘጋቢያችን ከባህር ዳር በላከልን ዘገባ አመለከተ።
ቁጥራቸው ከ5 ሺ በላይ የሚጠጉ ከፍኖተሰላም ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እንዲመለሱ የተደረጉት የአማራ ተወላጆች በሚመለሱበት ቦታ የደህንነት ዋስትና እንደሌላቸው እየገለጡ ሲሆን መሰሪው አገዛዝ በበኩሉ ስህተት መፈጠሩን በማመን ችግሩን የፈጠሩት ታች ያሉ ባለስልጣናት ነው የሚል አሳፋሪ መልስ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ተያይዞ የደረሰን ዘገባ አመልክቷል ።
ከትናንት በስቲያና፣ በትናንትናው እለት መኪኖች ተፈናቃዮችን ከአቅማቸው በላይ በመጫን ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ማቅናታቸውን የገለተው ዘጋቢያችን የክልሉ ሆድ አደር ባለስልጣናት ተፈናቃዮች እንዲወጡ የተደረገው በስህተት መሆኑን ተናግረው ይቅርታ ጠይቀዋል ብሏል። የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት ተብየውም የዞንና የወረዳ አመራሮችን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ እርምጃ እንደሚወሰድባቸውም መዛቱ ታውቋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት እንደዘገበው “እርምጃ ይወሰድባቸዋል የተባሉት የከማሸ ዞን አስተዳዳሪ እና የያሶ ወረዳ አስተዳዳሪ” መሸፈታቸውን የሚገልጥ መረጃ የደረሰው መሆኑን አመልክቷል። ባለስልጣኖቹ ” የአካባቢውን ተወላጆች አማራ ወረራችሁ ተነሱ እያሉና እየሰበኩ ወደጫካ መግባታቸውን የደረሰው መረጃ ያመለክታል ያለው ኢ ሳት የፌደራል ፖሊሶችም የሸፈቱትን ባለስልጣናት በመፈለግ ላይ መሆናቸውን አክሎ ገልጧል።
በከማሺ ዞን በአንድ የግብርና ኢንቨስትመንት ስራ ውስጥ ተቀጥረው እስካሁን ያልተፈናቀሉ የአማራ ተወላጅ እንደገለጹት በክልሉ እየተነዛ ያለው ወሬ አደገኛ በመሆኑ ተፈናቃዮች ሲመለሱ ችግር ሊደርስባቸው እንደሚችል ስጋታቸውን መግለጻቸውን ኢሳት አክሎ ዘግቧል።

No comments: