Friday, April 19, 2013

የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በዋልድባ አካባቢ ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ

ሚያዚያ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ድርጅቱ ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ልዩ ስሙ ሰቋር እና አምቦ ጠበል በተባለ ቦታ በተከታታይ ሁለት ቀናት ከመንግስት የፈጥኖ ደራሽ ጋር ባደረገው የፊት ለፊት ውጊያ ወታደራዊ የበላይነትን አግኝቷል።

አርበኞች ግንባር በሚያዚያ 8፣ 2005 ዓ.ም በመንግስት የፈጥኖ ደራሽ ሀይል ላይ በከፈተው የማጥቃት እርምጃ 21 የመንግስት ወታደሮችን በመግደል 25 ማቁሰሉን፣ በተመሳሳይ በሚያዚያ 9፣ 2005 ዓ.ም በዋልድባ ልዩ ስሙ አምቦ ጠበል በተባለው ቦታ ውጊያአድርጎ 25 የመንግስት ወታደሮችን ገድሎ 39 በማቁሰል ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን ገልጿል። በዚሁ አውደ-ውጊያ ላይም የተለያዩ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችንም ከመሰል ጥይቶቻቸው ጋር መማረኩን አስታውቋል።

ግንባሩ አገኘሁ ባለው ድል ላይ የኢትዮጵያ መንግስትን አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። አርበኞች ግንባር የህወሀት/ ኢህአዴግን መንግስት በትጥቅ ትግል ለማውረድ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው።

No comments: