Friday, November 1, 2013

ወያኔ አሁንስ ቅጥ አጣ

  November 1/2013

ወያኔ አሁንስ ቅጥ አጣ የወያኔ መንግስት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው በደል አይን ያወጣ እና አሳፋሪ መሆኑን እንደቀጠለ መሆኑን ከየስፍራው ይሚደርሱን ከህዝብ የሚመጡት መልክቶች ያስረዳሉ ሰሙኑን በባህር ዳር ከተማ ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሄደ ነው::

ይህን ተከትሎ የዛው ከተማ ነዋሪ የሆነ ሰው በፊስ ቡክ በውስጥ መልክት እንዲህ አለኝ ሰላም ወንድሜ  ባህር ዳር ከተማ ውስጥ ፍተሻ እንደበዛ ፖሰት ያደረከውን አየሁ በሰሞኑ ፍተሻ እኔ የገጠመኝን ልንገርህ  ቀኑ አርብ ማታ ማለትም 24-02-06 ከሆስፒታል ፋሲሎ በባጃጅ ተሳፍረን እየሄድን እያለ ቁሙ እንኮን ሳንባል ያለንበትን ባጃጅ /ቦታው አባ ገነሜ የህዝብ ቤተ መፀሃፍት ስንደርስ/ ተኩሰው አስቁመውን /ጥይቱ የባጃጁዋን ሸራ በስቶታል እኛን ባይመታም/ ምን ስህትት እንደሰራን ብንጠይቅ ውረዱ ተብልን በፖሊስ ተዋክበን ሹፌሩን አንድ ቀን አስረው ለቀውታል ፡፡

ቆይ እኛ ብንሞት ከዛሬ በፊት እንደተገደሉት 16 ሰዎች ከንፈር ብቻ ነበር የሚመጠጥልን ፡፡ ይኼ መንግስት ግን ቅጥ አጣ ቆይ እስኪ መሃል ከተማ ላይ ሰላማዊ ሰዎች ላይ መተኮስ ምንድን ነው; ይህን ሁኔታ ከጓዋደኞቼ ጋር ፍርድ ቤት ለመክሰስ ብንነጋገርም ካለው ፍትህ ሁኔታ ጋር በማነፃፀር ሳንስማማ የቀረን ሲሆን ስማችን ጠቅሰን ሁኔታውን በሙሉ በማህበራዊ ድህረ ገፃች ፖስት ልናደርግ ብናስብም ለአንድ ጓዋደናችን ደህንነት ስንል ተውነው ፡፡ ጓደኛው ለደህንነቱ ሲል የሚሰጋበትን ነገር አጫውቶኛል:: ይኼ ቅጥ ያጣውን የወያኔን ድፍረት ልናወግዘው በቃ ልንለው ይገባል::

               ከዘ ቮይስ ኦፍ ፍሪደም

No comments: