Sunday, November 17, 2013

የጂዳ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት ባልታወቀ ሁኔታ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘጋ

November 17/2013
የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት በጂዳ ስራውን ማቆሙን እና ላልተወሰነ ጊዜ መዘጋቱን መንግስት አሳወቀ ።የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፖብሊክ ቆንጽላ እንደገለጸው ከሆነ ምንም በማይያውቁት ሁኔታ በጂዳ የሚገኘውን መስሪያቤት መዝጋቱን ያሳወቀ ሲሆን በጂዳ የምትገኙት ኢትዮጵያኖች ፣ጉዳአችሁን እራሳችሁ ተወጡት እኔ ለእናንተ አገልግሎት ብቃት የመስጠቱ ብቃት የለኝም ሲል ማግለሉን እንድታውቁት የግርግዳ ላይ ወረቀት ለጥፎላችኋል ::
embassy letter
በሌላም በኩል አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም በሳኡዲ አረቢያ የሚገኙትን ዜጎቻችንን ለመርዳት ስንል የጂዳውን ቆንጽላ እንድንዘጋው ተገደናል ሲሉ በመገናኛ ብዙሃኖች ገልጸዋል ።ሆኖም ግን አጋዥ ሃይል ከተገኘ ከኢትዮጵያ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ሊላኩ የሚገባ የኢምባሲ ሰራተኞች መላክ የሚቻል እና 24/7 አገልግሎት እየሰጡ ወገኖቻቸውን ለማዳን ፈጣን የሆነ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ መሆኑን ሳንገልጽ አናልፍም ።
ኤልሳቤጥ ተስፋዬ ከሜሪላንድ እንዲህ ብላናለች »»»"እሁዳችንን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አስጀምረውናል! አሪፍ ቁርስ ናት ጎበዝ¡ ለነገሩ ክፍት ቢሆንስ ምን ይጠቅማል። በዱላ ከሚመልሱን በር ዘግተው ቢገላግሉን ይሻለል። ክፍት ሆኖም ዝግ ነበረ እኮ! ዝግ ጭንቅላት ተቀምጦበት በሩ ክፍት ቢሆን ከተዘጋ በር ምን ይለየዋል? እኔ የምለው ቆይ የትኛው ከሳውዲ ጋር ያላቸው ወዳጅነት ነው የወገኖቻችንን ደም እያስከፈለን ያለው? አቤት ወላድ ለጉድ ፈጥሮሽ በምን ቀን ነው ልጆችሽን ወደዛች ሀገር የሰደድሽው?
እባካችሁ ይሄን ያህል ብር ተመድቦ ይሄን ያህል ሰው በቀን እየገባ ነው ብላችሁ ኮመንት አድርጋችሁ ይባስ እንዳታሳምሙኝ። ትላንት ከአንድ ወዳጄ ጋር ስንጫወት "እየተደረገ ያለው ወደ ሀገር የመመለሱ ሂደት አባይን በጭልፋ እንደማለት ነው" ብሎኝ ነበር እውነቱን ነው። ጭልፋው እየጨለፈ,,,, እየጨለፈ,,,, ዝሎ ይወድቃል እንጂ ውሃውን ጨልፎ አይጨርሰውም፣ ዝሎ ባይወድቅ እንኳን ምን ያህል ጊዜና ምን ያህል አቅም ያስፈልገው ይሆን?! መንግስት ከብዛታቸው ጋር የሚመጣጠን አቅም ከሌለው ወይ በሰላም ወይ በተቃውሞ ለምን አይፈታውም? ወይም ሌላ መንግስት በመንግስትነቱ ለዜጎቹ ማድረግ ያለበትን ነገር ለምን አያደርግም? መንግስት ያለው ህዝብ እኮ በህይወት ነው ሀገሩ መግባት ያለበት። እየተደረገ ያለው እርዳታ እኮ እንኳን ለህይወታቸው ለአስከሬናቸውም መድረሱ ያጠራጥራል።
ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የሳውዲው ቆንፅላ በሩን ዘገቶ ከጉዳዩ ራሱን ቢያገል ምን ይደንቃል የገዛ መንግስታችን በፌደራል አስጠብቆ አስከብሮት የልብ ልብ እንዲሰማው አድርጎታል። ወይ ጉድ ጭራሽ በር ዘግተው የእህት ወንድሞቻችንን አስከሬን በበሩ ቀዳዳ አጮልቀው ይቆጥሩ ጀመር አይ የኢትዮጵያ አምላክ ከመንበርህ የለህማ!" አብርሃ ደስታ ከመቀሌ ደግሞ ይህንን አክሎአል "እነ ዶ/ር ቴድሮስ አድሐኖም የኢትዮዽያ ቆንስላ (በጅዳ) አገልግሎት እንዳይሰጥ የተዘጋው የቆንስላው ሰራተኞች ስደተኞቹን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንዲያግዙ ስለተፈለገ ነው ይላሉ። ከሆነ ጥሩ ነው። ሰራተኞቹ ስደተኞቹን ሲተባበሩ ኢትዮዽያዊ ዜግነታቸው መሰረት አድርገው እንጂ በፖለቲካ አመለካከታቸው እንደማይመዝኗቸው ተስፋ አደርጋለሁ።
ግን.... ስደተኞችን ለመርዳት ቆንስላ መዝጋት??? እንዴት ነው ነገሩ? ስደተኞችን ለመርዳት ቆንስላው በሙሉ ዓቅሙ (እስከ ሃያ አራት ሰዓት ድረስ) ክፍት መሆን አለበት። የቆንስላው ሰራተኞች ስደተኞቹ ወደ ሚገኙበት ቦታ ተንቀሳቅሰው ዜጎችን እየረዱ ከሆነ ቆንስላው እየሰራ ነው ይባላል እንጂ ዝግ ነው አይባልም። በማስታወቅያውም ቢሆን ቆንስላው የተዘጋበት ምክንያት አይጠቅስም። የቆንስላው ሰራተኞች ስተደኞችን እየረዱ ከሆነ ስለ ቆንስላ መዘጋት ማስታወቅያ መለጠፍ አስፈላጊ አልነበረም ብዬ አስባለሁ። ለማኛውም ጥረት ከተደረገ መልካም ነው።
It is so!!!"

No comments: